Get Mystery Box with random crypto!

✞ ተዋሕዶ ✞ 🇹 🇪 🇼 🇦 🇭 🇪 🇩 🇴

የቴሌግራም ቻናል አርማ tewahedo12 — ✞ ተዋሕዶ ✞ 🇹 🇪 🇼 🇦 🇭 🇪 🇩 🇴
የቴሌግራም ቻናል አርማ tewahedo12 — ✞ ተዋሕዶ ✞ 🇹 🇪 🇼 🇦 🇭 🇪 🇩 🇴
የሰርጥ አድራሻ: @tewahedo12
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 10.16K
የሰርጥ መግለጫ

"ሥርዓትን እማር ዘንድ ያስጨነከኝ መልካም ሆነልኝ"
መዝ 118 (119) ፥ 71
ይህ ቻናል የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ዶግማንና ቀኖናን ትውፊትን እንዲሁም አስተምሮን የጠበቁ የተለያዩ የሚያስተምሩ ነገሮች ይለቀቁበታ፡፡ ግሩፑ
http://t.me/OrthodoxTewahedo12
ይህ Channel #ሐምሌ 26/2010 ዓ.ም አ/ጀመረ
ለአስተያየት 📥 ➩ @Tewahedo12_bot

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2023-07-06 06:43:37 https://telegra.ph/ስንክሳር-ዘወርኀ-ሰኔ-06-28-9
532 views✞ ባሮክ ✞, 03:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-05 14:04:30 https://telegra.ph/ከሰይጣን-ጋር-የተደረገ-ቃለ-ምልልስ-ተዋስኦተ-ጳውሊ-ምስለ-ሰይጣን-05-11
737 views✞ ባሮክ ✞, 11:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-05 07:57:29

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ
           አሜን

"በበጎ ሥራ ሁሉ ፍሬ እያፈራችሁ በእግዚአብሔርም እውቀት እያደጋችሁ፥
ለጌታ እንደሚገባ ትመላለሱ ዘንድ እንለምናለን"
ቆላስይስ 1፥10-11

                    ቀናችንን በጸሎት እንጀምር

    ✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥          
"ክረምትን ለምን ፈራሁ?"
    ✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥

❖ በጋና ክረምትን እያፈራረቀ የሰውን ልጅ ሁሉ የሚመግብ እግዚአብሔር ነው፤ በክረምት ገበሬው ይዘራል፣ እግዚአብሔር ደግሞ ከሰማይ ጠሉን ይልክለታል።

❖ በክረምቱ ጊዜ ተዘርቶ ያደገው ሰብል እንዲበስል ፈጣሪው የበጋውን ፀሐይ ያወጣለታል፤ ትጉሁ ገብሬም የደረሰውን አዝመራ ሊሰበስብ በበጋው ማጭዱን ይዞ ይታያል፤ ክረምት ለገበሬው የሥራ ጊዜ ነው።

❖ ለእኔ ግን ክረምት ያስፈራኛል እንዳልጽፍ እጆቼ በብርዱ ቆፈን ይያዛሉ፣ እንዳላነብ አይኖቼ በእንቅልፍ ሽፋሽፍት ይፈዝዛሉ፤ ማልጄ በቤቴ መስኮት የማያት ፀሐይ በደመና ስትሸፈን ቀኑ የጀመረ ሌሊቱም የነጋ አይመስለኝ ከአልጋዬ ተነሥ ተነሥ አይለኝም ውጪው ሲጨልም ቤቴም ይደበዝዝብኛል፤ ወጥቼ ሥራዬን እንዳልሠራ፣ ከወዳጆቼ ጋር ተገናኝቼ እንዳላወጋ ዝናቡ አላላውስ ይለኛል።

❖ ለእኔ ክረምት ያስፈራኛል ግን ለምን ክረምትን ፈራሁት? እንደ ገበሬው የዝናብን በረከት ማየት ስላቃተኝ ይሆን? ወይስ የምዘራው ዘር በእጄ ስለሌለ? እንዲጸድቅ የምፈልገው ተክል፣ ልምላሜውን ማየት የሚያጓጓኝ እጽ የለኝ ይሆን?

❖ በሥራ እና በግል ጉዳዮቼ ተጠምጄ ከራቅኋቸው ከቤቸሰቦቼ ልብ ላይ የምዘራው ብዙ የፍቅር ዘርማ አለኝ፤ በሰዎች ሆታ እና ጩኸት ስከበብ የዘነጋሁት በመልካም ሰብእና እንዲጸድቅና እንዲለመልም የምፈልገው እኔነት አለኝ፤ ታዲያ ለራሴ የሚሆን በቂ ጊዜ አግኝቼ ውስጤን አርስ፣ እመረምርና አለሰልስ ዘንድ ክረምት የመጣው፣ ዝናቡስ የዘነበው ለእኔ ብሎ አይደል?

❖ ለካ የብርዱ ቆፈን የበረታብኝ፣ የአይኖቼ ሽፋሽፍት በእንቅልፍ የደከሙብኝ ክረምትን ስለማልወደው ሳይሆን የክረምትን በረከት ማስተዋል ስላልቻልኩ ነው፤ ለካስ ክረምቱ የደበተኝ "ደግሞ ሊመጣ ነው" ብዬ ቀድሜ ስላወገዝኩትና ራሴን ለሥራ ስላላዘጋጀሁ ነው።

❖ ሰማዩ ሲደምን እና ዝናቡ አላስወጣ ብሎ ሲዘንብ በእኔ ውስጥ ያለችውን ፀሐይ ፈልጌ እንድገልጣት እድል እየሰጠኝ ነው፤ ክረምት የደረቀው እጽ መልሶ የሚያቆጠቁጥበት ብቻ ሳይሆን ያረጀውና ሊወድቅ ያዘመመው ውስጤ የሚታደስበትና የሚጠገንበት ጊዜ ነው፤ ለካስ ክረምት ለገበሬ ብቻ የመሰለኝ ስህተት ነው። ክረምት ለእኔም ነው!

ክረምት ሲገባ እና ፀሐይ አዘውትራ መታየት ስታቆም ከዚህ ጋር ተያይዞ "Seasonal affective disorder" የተባለ ድባቴ ውስጥ ለሚገቡ ሁሉ መታሰቢያነት የተጻፈ

"የሚሰማኝ ግን በእርጋታ ይቀመጣል ከመከራም ሥጋት ያርፋል"
ምሳ 1፥33

ምንጭ
ዲያቆን አቤል ካሳሁን



ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ፤ እኔም ለእናንተ ከአዘጋጀው በኃዋላ በድካሜ ብዛት ሳይገባኝና ሳይገባኝ በምጽፈው ድርሳንወ ገድላት መጽሐፍት ላይ የቃላት (የፊደል) ሕፀፅ ቢገኝ በጎደለው እየሞላችሁ በጠመመው እያቃናችሁ አንብቡ በረከት ተካፈሉ እላለሁ ከምንም ጊዜ በላይ ለሀገራችንና ለዓለም ሰላም እንዲሁም ለደካማው ወንድማችሁ እንድበረታ (የተጣልሁ) እንዳልሆን ስለ እኔ ጸልዩ

"ልብህን በእርጋታ አኑረው፤ የሁሉም መጨረሻ እና የሁሉም አገልጋይ ለመሆን በጣም ትጋ ለከንቱ ንግግር ዘገምተኛና ሰነፍ ሁን፤ ነገር ግን የቅዱሳት መጻህፍትን ቃል በማወቅ በመስማት ድኅነትን የሚሰጡ ናቸውና ብልህ ሁን"
ታላቁ ባስልዮስ ዘቂሳሪያ

               ወስብሐት ለእግዚአብሔር
                              ይቆየን 

───────────
                    Channel
   
https://telegram.me/Tewahedo12

        FB Like Page (የፌስቡክ ፔጅ)
 
http://facebook.com/Tewahedo12  

        YouTube Subscribe (ሰብስክራይብ)
https://www.youtube.com/channel/UCvYxUdv1D-5juH_P6iE7XXw
 ───────────
693 views✞ ባሮክ ✞, 04:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-05 07:56:57               ✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥
"የሚሰማኝ ግን በእርጋታ ይቀመጣል ከመከራም ሥጋት ያርፋል"
ምሳ 1፥33
                       
#ስንክሳር          
               ዘሰኔ
#ሃያ ስምንት (፳፰)        
              ✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥
462 views✞ ባሮክ ✞, 04:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-05 07:56:26 ✥•••••••••••••••••••●◉ ✞ ◉●•••••••••••••••••••✥

"ልብህን በእርጋታ አኑረው፤ የሁሉም መጨረሻ እና የሁሉም አገልጋይ ለመሆን በጣም ትጋ ለከንቱ ንግግር ዘገምተኛና ሰነፍ ሁን፤ ነገር ግን የቅዱሳት መጻህፍትን ቃል በማወቅ በመስማት ድኅነትን የሚሰጡ ናቸውና ብልህ ሁን"
ታላቁ ባስልዮስ ዘቂሳሪያ

በሰኔ ወር
#በጠዋትና በማታ #የሚነበቡ የእየለታት #የመጽሐፍ ቅዱስ #ክፍሎች

#ሰኔ


“ስለዚህ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ ሰው ሁሉ ለመስማት የፈጠነ ለመናገርም የዘገየ ለቍጣም የዘገየ ይሁን”
ያዕቆብ 1፥19

መልካም ንባብ

✥•••••••••••••••••••●◉ ✞ ◉●•••••••••••••••••••✥

Share
🇹 🇪 🇼 🇦 🇭 🇪 🇩 🇴
✥••┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈••✥

@Tewahedo12

@OrthodoxTewahedo12

✥••┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈••✥
478 views✞ ባሮክ ✞, 04:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-05 07:56:15 https://telegra.ph/ስንክሳር-ዘወርኀ-ሰኔ-06-28-10
603 views✞ ባሮክ ✞, 04:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-04 16:30:57 https://telegra.ph/መጽሐፍ-ቅዱስን-እንዴት-ላንብብ-08-24
800 views✞ ባሮክ ✞, 13:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-12 14:17:14 https://telegra.ph/ነገረ-ማርያም-በብሉይና-በሐዲስ-ኪዳን-09-23
59 views✞ ባሮክ ✞, 11:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-12 09:56:48

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ
           አሜን

"በበጎ ሥራ ሁሉ ፍሬ እያፈራችሁ በእግዚአብሔርም እውቀት እያደጋችሁ፥
ለጌታ እንደሚገባ ትመላለሱ ዘንድ እንለምናለን"
ቆላስይስ 1፥10-11

                    ቀናችንን በጸሎት እንጀምር

    ✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥
          ጠቃሚ ምክር   
    ✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥

❖ በህይወት ጉዞ ላይ አንዳንድ ያላሰብካቸዉ ነገሮች ሊገጥሙ ይችላሉ፤ ቢያጋጥሙህም ግን እሩጫህን እንዲያደናቅፍብህ አትፈቀድላቸዉ፤ እንደዉም ሀይልና ብርታት እንደሚጨምርልህ አርገህ ቁጠረው።

❖ ምን ግዜም "ነገር ሁሉ ለበጎ ነዉ" የሚለዉን የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል አስብ፤ ይሄን እዉነት መተግበር ስጀምር ምንም አይነት ነገር በህይወትህ ላይ ቢገጥሙህ፤ የብረታት እንጂ ተስፋ የመቁረጥ ስሜትን ከህይወትህ ላይ ጠርገህ ታጠፋለህ፤ ስለዚህ ነገር ሁሉ ለበጎ ነዉ ብለህ አስብ።

❖ ራስህን አትጣል የሚያነሣህ የለምና፤ ጥንካሬህንና አቋምህን አስተካክል በዙሪያህ ዉድቀትህን የሚመኙ አይጠፉምና፤ ለራስህ ቦታ ስጠዉ ያንተዉ ነህና፤ ለራስህ ክብር ስሰጥ ነዉ የሌሎች ክብር የሚገባህ።

❖ በህይወትህ ዘመን ታላቅ ሠዉ መሆን ከፈለክ ሞራልህን ጠብቅ ሞራልህን ሊያሣጣህ የሚችሉትን የአሉታዊ ሰዎች ንግግር አታዳምጥ አንተ የምትወድቀዉ ገንዘብ ሣይኖርህ ሲቀር ሳይሆን ሞራልህ ሲወድቅ ነዉና ሞራልህን ሳታስነካ ጠብቅ፤ ሞራልህ የወደቀ ቀን ጉልበት ይከዳሀል ፣ማገናዘብ ይሳንሀል፣ መራመድ ያቅትሀል በመጨረሻም ትወድቃለህ።

❖ አስተዉል አንዳንዴ ችግሮች ለመጣል ወይም ወድቀን እንድንቀር ብቻ ሳይሆን ያላየነዉን የስኬት ጉዞ ሊያሳየን፤ ከድክመት ይልቅ ጥንካሬን ሊያስተምሩን ነዉና ተስፋ ከመቁረጥ ይልቅ እራሣችንን አጠንክረን ወደ ፊት እንጓዝ።

❖ ፍፃሜህ እንዲያምር ራስህን አታመፃድቅ ሁሌም ከስህተትህ ለመማር ፍቃደኛ ሁን ጥፋትህን አሜን ብለህ መቀበልህ ክብርህን የሚጎዳብህ አይምሰልህ።

❖ ሰንደል ሲያቃጥሉት ነዉ የሚሸተዉ ስለዚህ አንተም እኔም አንቺም በችግር ብንፈተንም ያ ማለፊያችን ነዉና ታግሰን እናሳልፈዉ ከዛ ጥንካሪያችንን አጠንክረን ወደ ፊት እንጓዝ ያኔ ዕራያችን እዉን ይሆንና መአዛችን አለምን ያዉዳል።

❖ አስተዉል ህይወት እንዲ ነዉ፤ በቃ! ሁሉንም የኛ ልናደርግ አንችልም! ነፋስን አባሮ እንደ መያዝ ነዉና ሁሉም ነገር የራስህ እንዲሆን ከመድከም ይልቅ ባለህ ነገር ደስተኛ ለመሆን ሞክር፤ ከአንዱ ምዕራፍ ወደ ሌላዉ ምዕራፍ  እንደሚያሸጋግረህም ፈጣሪህም ታመን ከዛም በአምላክህ ደስ ይበልህ በእምነት ኑር።

እንድናስተውል ልዑል እግዚአብሔር ዓይነ ልቦናችን፤ ያብራልን

"የሚሰማኝ ግን በእርጋታ ይቀመጣል ከመከራም ሥጋት ያርፋል"
ምሳ 1፥33



ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ፤ እኔም ለእናንተ ከአዘጋጀው በኃዋላ በድካሜ ብዛት ሳይገባኝና ሳይገባኝ በምጽፈው ድርሳንወ ገድላት መጽሐፍት ላይ የቃላት (የፊደል) ሕፀፅ ቢገኝ በጎደለው እየሞላችሁ በጠመመው እያቃናችሁ አንብቡ በረከት ተካፈሉ እላለሁ ከምንም ጊዜ በላይ ለሀገራችንና ለዓለም ሰላም እንዲሁም ለደካማው ወንድማችሁ እንድበረታ (የተጣልሁ) እንዳልሆን ስለ እኔ ጸልዩ

"ልብህን በእርጋታ አኑረው፤ የሁሉም መጨረሻ እና የሁሉም አገልጋይ ለመሆን በጣም ትጋ ለከንቱ ንግግር ዘገምተኛና ሰነፍ ሁን፤ ነገር ግን የቅዱሳት መጻህፍትን ቃል በማወቅ በመስማት ድኅነትን የሚሰጡ ናቸውና ብልህ ሁን"
ታላቁ ባስልዮስ ዘቂሳሪያ

               ወስብሐት ለእግዚአብሔር
                              ይቆየን 

───────────
                    Channel
    https://telegram.me/Tewahedo12

        FB Like Page (የፌስቡክ ፔጅ)
  http://facebook.com/Tewahedo12  

        YouTube Subscribe (ሰብስክራይብ)
https://www.youtube.com/channel/UCvYxUdv1D-5juH_P6iE7XXw
 ───────────
262 views✞ ባሮክ ✞, 06:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-11 19:29:13 ✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥
"የሚሰማኝ ግን በእርጋታ ይቀመጣል ከመከራም ሥጋት ያርፋል"
ምሳ 1፥33
                       
#ስንክሳር          
             ዘሰኔ
#አምስት (፭)        
              ✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥
503 views✞ ባሮክ ✞, edited  16:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ