Get Mystery Box with random crypto!

✞ ተዋሕዶ ✞ 🇹 🇪 🇼 🇦 🇭 🇪 🇩 🇴

የቴሌግራም ቻናል አርማ tewahedo12 — ✞ ተዋሕዶ ✞ 🇹 🇪 🇼 🇦 🇭 🇪 🇩 🇴
የቴሌግራም ቻናል አርማ tewahedo12 — ✞ ተዋሕዶ ✞ 🇹 🇪 🇼 🇦 🇭 🇪 🇩 🇴
የሰርጥ አድራሻ: @tewahedo12
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 10.16K
የሰርጥ መግለጫ

"ሥርዓትን እማር ዘንድ ያስጨነከኝ መልካም ሆነልኝ"
መዝ 118 (119) ፥ 71
ይህ ቻናል የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ዶግማንና ቀኖናን ትውፊትን እንዲሁም አስተምሮን የጠበቁ የተለያዩ የሚያስተምሩ ነገሮች ይለቀቁበታ፡፡ ግሩፑ
http://t.me/OrthodoxTewahedo12
ይህ Channel #ሐምሌ 26/2010 ዓ.ም አ/ጀመረ
ለአስተያየት 📥 ➩ @Tewahedo12_bot

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 132

2022-07-14 10:39:28 https://telegra.ph/የቅድስት-ሥላሴ-ዓመታዊ-በዓል-ድንቅ-ምሥጢር-07-14
1.1K views07:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 07:23:47 ✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥
"የሚሰማኝ ግን በእርጋታ ይቀመጣል ከመከራም ሥጋት ያርፋል"
ምሳ 1፥33
                        #ስንክሳር          
             ዘሐምሌ #ሰባት (፯)     
          ✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥ 
782 viewsedited  04:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 19:48:12 ✥•••••••••••••••••••●◉ ✞ ◉●•••••••••••••••••••✥

"ልብህን በእርጋታ አኑረው፤ የሁሉም መጨረሻ እና የሁሉም አገልጋይ ለመሆን በጣም ትጋ ለከንቱ ንግግር ዘገምተኛና ሰነፍ ሁን፤ ነገር ግን የቅዱሳት መጻህፍትን ቃል በማወቅ በመስማት ድኅነትን የሚሰጡ ናቸውና ብልህ ሁን"
ታላቁ ባስልዮስ ዘቂሳሪያ

በሐምሌ ወር #በጠዋትና በማታ #የሚነበቡ የእየለታት #የመጽሐፍ ቅዱስ #ክፍሎች

#ሐምሌ


“ስለዚህ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ ሰው ሁሉ ለመስማት የፈጠነ ለመናገርም የዘገየ ለቍጣም የዘገየ ይሁን”
ያዕቆብ 1፥19

መልካም ንባብ

✥•••••••••••••••••••●◉ ✞ ◉●•••••••••••••••••••✥

Share
🇹 🇪 🇼 🇦 🇭 🇪 🇩 🇴
✥••┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈••✥

@Tewahedo12

@OrthodoxTewahedo12

✥••┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈••✥
1.0K views16:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 19:47:55 https://telegra.ph/ስንክሳር-ዘወርኀ-ሐምሌ-07-07-7
989 views16:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 14:06:14 ❖ በነገር እንዳንደፍር እንዲህ ነው ከማለት እነሆ ዛሬ ተከለከልን ፤ የነገራችንም ሕፁፅነት እግዚአብሔርን ባሰብነው ጊዜ መፈራረጃ ይሆንብናል ፤ ሁልጊዜ እግዚአብሔርን ማሰብ መውደድን ግን ፤ ርሱን ማመስገንን በሚወዱ ዐዋቆች ዘንድ ይገኛል ።

❖ ነገር ግን ዘወትር በማሰብ ፤ በመንፈሳዊ ሥራ በመትጋት አንዱ ከአንዱ የሚበልጥ  አለ ማወቅ የሚገባው እንደ መሆኑ እግዚአብሔርን ወደ ማወቅ እንደደረሰ አድርጎ ራሱን ከሚያስት ይልቅ ማንም ደካማ የለም፡፡
መዝ 36(35)፥1-4 ፤
ዕብ 3፥12 ፤
ገላ 6፥4

❖ የተናገርሁትንስ ቢያውቅ መርምሮ 'ከማወቅ ደካማነቱን ሕፁፅነቱን ፈጽሞ ያውቃል፤ እንደዚሁም በዚያ ወራት አብርሃምና ሙሴ ሰው ሊያየው በማይቻለው አምሳል እግዚአብሔርን ማየት ማወቅ ቢቻላቸው ያን ጊዜ ከእነርሱ አንዱም አንዱም ከማወቅ ድካሙን ዐወቀ።

❖ አብርሃምም ራሱን ነቅፎ "ትቢያ አመድ ነኝ" አለ፤ ሙሴም እንደ እርሱ"እኔ  ድዳ ነኝ መናገርም አይቻለኝም" አለ፤ ሊመረምሩት የማይቻል ያየውን ጌትነቱን ዐውቆ።
ዘፀ 1፥10፤
ዕብ 12፥2፤
ሐዋ 7፥1

❖ ዛሬ ግን ዐዋቂ ሰው ሁሉ የእግዚአብሔርን ነገር ይሰማል፤ ከመስማትም አይሰለችም ዐዋቂ 'ሰሎሞን ዦሮ ከመስማት ፤ ዐይንም ከማየት አይሰለችም ብሎ እንደተናገረ።
መክ 1፥8
ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሣርያ

እግዚአብሔር የቅዱሳን ሃይማኖት በሆነች በቅድስት ተዋሕዶ እስከ ፍጻሜ ያጽናን

"የሚሰማኝ ግን በእርጋታ ይቀመጣል ከመከራም ሥጋት ያርፋል"
ምሳ 1፥33

  አዘጋጅ
  ዲ/ን ቡሩክ ይርጋ

ምንጭ
ፍኖተ ቅዱሳን



ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ፤ እኔም ለእናንተ ከአዘጋጀው በኃዋላ በድካሜ ብዛት ሳይገባኝና ሳይገባኝ በምጽፈው ድርሳንወ ገድላት መጽሐፍት ላይ የቃላት (የፊደል) ሕፀፅ ቢገኝ በጎደለው እየሞላችሁ በጠመመው እያቃናችሁ አንብቡ በረከት ተካፈሉ እላለሁ ከምንም ጊዜ በላይ ለሀገራችንና ለዓለም ሰላም እንዲሁም ለደካማው ወንድማችሁ እንድበረታ (የተጣልሁ) እንዳልሆን ስለ እኔ ጸልዩ
  
"አንተ ሰው ቃለ እግዚአብሔርን ተማር፤ ባትለወጥም ዝም ብለህ ተማር! ኹልጊዜ ተማር። ላትስተካከል ትችላለህ፤ ላትለወጥ ትችላለህ፤ ግን ተማር፤ ቢያንስ ቢያንስ ጥሩ ሰው እንኳን ባትኾን ራስህን ለመውቀስ የምትችልበት ዓቅም ታገኛለህ፤ ካልተማርክ ግን ራስህን እንኳን መውቀስ የምትችልበት ዓቅም አታገኝም፤ ስለዚህ ተማር ስትማር ቢያንስ ኃጢአት እንኳን ስትሠራ ራስህን እየወቀስክ ትሠራለና፤ ይህች የንስሐ በር ትኾንልሃለች፤ አንድ ቀን ወደ ንስሐም ትመራሃለች"
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

               ወስብሐት ለእግዚአብሔር
                            ይቆየን

ትምህርቱ እንዴት ነው......የእናተ አስተያየትና ጥያቄ ከዚህ የበለጠ ለመትጋት ይረዳልና መልእክት ይተውሉኝ፤ የተሳተውን፤ የተረሳው፤ የተገደፈውን፤ የነጠፈውን በቀና መንፈስ አቃንታቹ አንብቡት ቸሩ መድኃኔዓለም ማስተዋሉን ያድለን፤ በፀሎታቹ አስቡኝ አትርሱኝ የተለያየ ጽሁፍ ያላቹ፣ መተረክ እንችላለን የምትሉ እና ካርድ በመግዛት ቻናሉንና ግሩፑን በተለያየ አገልግሎት ማገዝ የምትፈልጉ በውስጥ መስመር አናግሩኝ።

Coment    @Tewahedo12_bot

 ───────────

                    Channel
    https://telegram.me/Tewahedo12

                    Group
  https://telegram.me/OrthodoxTewahedo12

      Facebook Like Page (የፌስቡክ ፔጅ)
  http://facebook.com/Tewahedo12

YouTube Subscribe (ሰብስክራይብ)
https://www.youtube.com/channel/UCvYxUdv1D-5juH_P6iE7XXw

 ───────────
1.1K viewsedited  11:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 14:06:13

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ
           አሜን  

"በበጎ ሥራ ሁሉ ፍሬ እያፈራችሁ በእግዚአብሔርም እውቀት እያደጋችሁ፤ለጌታ እንደሚገባ ትመላለሱ ዘንድ እንለምናለን"
ቆላስይስ 1፥10-11

ክፍል አስራ አምስት
        ✥••┈••●◉ ✞ ◉●••┈••✥
ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ንጽሕይት የቅዱሳን ሃይማኖት
        ✥••┈••●◉ ✞ ◉●••┈••✥ 

የቀጠለ....
❖ የሦስቱ አካላት መለኮት ፍጹም አንድነትን ልናውቅ ይገባናል፤ የእነርሱ የሚሆን አንድ መለኮትን አንድ በማድረግ እናዋሕድ፤ በአብ ወላዲነት አሥራፂነት መለኮት አንድ እንዲሆን "እንደሆነ" ሃይማኖትን እንመን፤ ወልድ ከአብ ተወልዶአልና መንፈስ ቅዱስም ከአብ [ከዘለዓለም] ተገኝቷልና፤ አብ ከወልድ ወልድም ከመንፈስ ቅዱስ ሳይቀድም ወልድ ከአብ በመወለዱ መንፈስ ቅዱስም ከአብ በመሥረፁ የፈጣሪያችን የሦስትነቱ መለኮት አንድ ይሆናል።

❖ የፈጣሪያችን የእግዚአብሔርን የባሕርዩን አንድነት በፍጹም ገጽ፤ በፍጹም መልክ የአካሉን ሦስትነት እንዲህ እንመን፤ መዠመሪያ በእግዚአብሔር አብ እናምናለን እንበል ዳግመኛም የእግዚአብሔር የባሕርይ ልጅ በሚሆን ተቀዳሚ ተከታይ በሌለው በእግዚአብሔር ወልድ እናምናለን እንበል፤ "ከዘለዓለም መቀዳደም ሳይኖር" ከአብ መገኘቱን ዐውቀን በመንፈስ ቅዱስም እናምናለን ማለትን እንዲህ ሦስተኛ አድርገን፤ በእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስም እናምናለን እንበል ሰው ሁሉ በቀናችው ሃይማኖት ጸንቶ ይኖር ዘንድ፡፡

❖ በዚህ ሦስቱን በማመን ጸንተን አካላት በየገጻቸው በየመልካቸው ልዩ መሆናቸውን ፈጽመን ዕንወቅ፤ በከበርንባቸው በእሊህ ስሞች በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ እንመን ሰው የሆነ ቃል ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ አዘዘን። ማቴ 28፥19፤
1ኛ ዮሐ 5፥1–33

❖ ይህን አንድ ወልድን ሁለት አካል ሁለት ባሕርይ አንለውም፤ መለኮት በገንዘቡ አካል በገንዘቡ ባሕርይ፤ ትስብእትም በገንዘቡ አካል በገንዘቡ' ባሕርይ ልዩ እንደሆነ አንናገርም፤ አንድ አካል አንድ ባሕርይ ነው እንላለን እንጂ፡፡
1ኛ ቆሮ 6፥6፤
2ኛ ቆሮ 5፥14

❖ ጴጥሮስም ሁለት አካል ሁለት ባሕርይ ብሎ አልተናገረም አንድ አካል አንድ ባሕርይ እንደሆነ አምኖ "ክርስቶስ ስለ እኛ በሥጋ የታመመ" አለ እንጂ፡፡
1ኛ ጴጥ 2፥21–25

❖ ዳግመኛም በሥጋ ስለተወለደ መልአክ ከብት ለሚጠብቁ ነገራቸው
" እነሆ መድኅን ዛሬ  ተወለደላችሁ" ብሎ ይኸውም የባሕርይ ገዥ ክርስቶስ ነው።
ሉቃ 2፥11

❖ ዛሬ ተወለደ ማለቱም ለመገኘቱ ጥንቱ አይደለም ፤ ዓለም ሳይፈጠር የነበረ ነውና ፤ ቅድመ ዓለም የነበረ ወልድ ሰው ሆኖ ዛሬ እንደ ተወለደ በጎላ በተረዳ ይነገራል እንጂ ዳግመኛም በግብረ ሐዋርያት አይሁድ የሰቀሉት ይህ ነው አለ።
ዕብ 13፥8፤
ሐዋ 10፥36-40

❖ በመናፍቃን ዘንድ ግን የቃል መገኘቱ ከማርያም በተወለደ ጊዜ እንደሆነ ይነገራል፤ ከሰሎሞን ቃል "እግዚአብሔር ፈጠረኝ" የሚል ምክንያትን አግኝተው፤ ሰሎሞን ግን ስለተወለደው ልደት ይህንን ተናገረ።

❖ እንደ እነርሱስ አነጋገር ከሆነ እንደተወለደ ዳግመኛም ኢየሱስ እንደ ተባለ እርሱ እንደ ተሰቀለ የተነገረው ነገር ሁሉ ሐሰት መሆኑ ነው፤ ቅድመ ዓለም ስለነበረ ስለ እግዚአብሔር ቃል ባሕርይ ግን ነቢዩ ዳዊት "ጌታ ጌታዬን አለው" አለ።
መዝ 110[109]፥1

❖ ጳውሎስም ክርስቶስ የእግዚኣብሔር ኀይል "እግዚአብሔር" ነው፤ የእግዚአብሔር ቃል ነው አለ።
1ኛ ቆሮ 1፥24

❖ ነቢይ ሙሴም "ሰውን በእኛ መልክ በእኛ አምሳል እንፍጠር አለ እግዚአብሔር" አለ ፤ ዳግመኛም እግዚአብሔር አዳምን ፈጠረው፡፡ በእግዚኣብሔር አምሳልም ፈጠረው አለ።
ዘፍ 1፥26 ፤ 2፥7

❖ ዳግመኛም አዳም ከእኛ እንደ አንዱ ሆነ አለ፤ ዳግመኛም እግዚአብሔር ከእግዚአብሔርነቱ እሳትን አዘነመ ፤ ነቢይ ዳዊትም የአማልክት ልጆች ለእግዚአብሔር ምስጋና አቅርቡ አለ።
ዘፍ 3፥22 ፤19፥24 ፤
መዝ 29[28]፥1

❖ ወንጌላዊ ዮሐንስም "ያ ቃል በቅድምና የነበረ ነው ፤ ይህም ቃል በእግዚአብሔር አብ ህልውና ነው ፤ ያም ቃል እግዚአብሔር ነው፤ ያ ቃል በእግዚአብሔር አብ ህልው እንደሆነ በእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስም ህልው ነው፤ ሁሉ በርሱ ቃልነት ተፈጠረ ፤ ከተፈጠረው ፍጥረትም ያለርሱ ቃልነት ምንም ምን የተፈጠረ የለም አለ።
ዮሐ 1፥1-4

❖ ሐዋርያ ቶማስም ወልድን "ጌታዬ  ፈጣሪዬ" አለው።
ዮሐ 20፥24–29

❖ እኛ የተናገርነውን ይህንንም ነገር መናፍቃን ስለ ዓለም ስለ ፍጡራንም በእጅ ስለተሠሩ ጣዖታትም የተነገረው ነው ይሉታል ፤ እውነትኛውን ሃይማኖት ግን አያውቁም፡፡

❖ በእውነተኛው የባሕርይ አምላክ ሁሉን በፈጠረ በአብ ፤ በአንድ ልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ ፤ ማሕየዊ በሚሆን በመንፈስ ቅዱስም አያምኑም

❖ ለእኛ በጎ ነው በምግባር በሃይማኖት ጸንተን ሁልጊዜ እግዚአብሔርን ማሰብ ይገባናል ፈጽማ ፤ እግዚአብሔርን የምትወደው ሰውነት ፍቅሩን አትጠግበውምና።
ዘዳግ 6፥2-7 ፤
መዝ 42(41)፥103

❖ ዳግመኛም የእግዚአብሔርን ጌትነቱን በነገር ብንመረምር ድፍረት ነው ፤ የማይመረመር ጌትነቱን ከማወቅ ልቡናችን ይደክማልና አይደርስበትምና ሕሊና መርምሮ ሊያውቀው ያልቻለውንም ቃል ገልጦ ሊናገረው አይችልምና። መዝ.139(138)፥6 ፤
ኢሳ 40፥13 -14  ፤
ሮሜ 16፥33–35 ፤
1ኛ ቆሮ 2፥16

❖ የምናያቸው ፍጡራንን መርምሮ ማወቅ ለልቡናችን የሚርቀው ከሆነ ፤ እንደሚገባቸውም እንናገር ዘንድ ካልተቻለን የማናውቀውን ለመናገር እንደምን  እንደፍራለን ?
961 viewsedited  11:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ