Get Mystery Box with random crypto!

✞ ተዋሕዶ ✞ 🇹 🇪 🇼 🇦 🇭 🇪 🇩 🇴

የቴሌግራም ቻናል አርማ tewahedo12 — ✞ ተዋሕዶ ✞ 🇹 🇪 🇼 🇦 🇭 🇪 🇩 🇴
የቴሌግራም ቻናል አርማ tewahedo12 — ✞ ተዋሕዶ ✞ 🇹 🇪 🇼 🇦 🇭 🇪 🇩 🇴
የሰርጥ አድራሻ: @tewahedo12
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 10.16K
የሰርጥ መግለጫ

"ሥርዓትን እማር ዘንድ ያስጨነከኝ መልካም ሆነልኝ"
መዝ 118 (119) ፥ 71
ይህ ቻናል የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ዶግማንና ቀኖናን ትውፊትን እንዲሁም አስተምሮን የጠበቁ የተለያዩ የሚያስተምሩ ነገሮች ይለቀቁበታ፡፡ ግሩፑ
http://t.me/OrthodoxTewahedo12
ይህ Channel #ሐምሌ 26/2010 ዓ.ም አ/ጀመረ
ለአስተያየት 📥 ➩ @Tewahedo12_bot

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 128

2022-08-31 19:36:08 https://telegra.ph/ስስንክሳር-ዘነሐሴ-09-01
75 views16:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 15:09:32 ❖ የተግዥ ባሕርይን የተዋሐደ ፤ በርሱ ትሕትና እኛ እንከብር ዘንድ የተዋረደ እርሱ ነው፣ ሕማማችንን የታገሠ፣ ደዌያችንን የተሸከመ በደላችንን የተቀበለ ስለእኛ ራሱን የማያልፍ፣ የማይለወጥ መሥዋዕት እድርጎ ያቀረበ፤ የማይሻር ፤ የማይለወጥ ካህን እርሱ ነው።
ኢሳ 43፥1-11  ፣
ፊልጵ 2፥5-9 ፣
ዕብ 7፥19-28፣ 10፥12-21

❖ የሚሠዋ በግ እርሱ ነው፤ የሚሠዋ ካህን እርሱ  ነው፤ ከባሕርይ አባቱ ከአብ፤ ከባሕርይ ሕይወቱ ከመንፈስ ቅዱስ ጋርም መሥዋዕት የሚቀበል እርሱ ነው ።
ዮሐ 1፥24 ፣
ዕብ 9፥16–28

❖ በፈቃዱ መከራን በሥጋው የተቀበለ ፤ መከራንም ሁሉ የታገሠ እርሱ ነው፡፡ እንደ በግ ሊሠዋ መጣ በግ በሚሸልተው ሰው ፊት እንዳይናገር አልተናገረም ፤ በነገሩም ሐሰት አልተገኘበትም፡፡
ኢሳ 53፥7-9 ፣
ሐዋ 8፥32 ፣
1ኛ ጴጥ 2፥21-25

❖ የግርንግሪት ዐሥረው ወደ ፍርድ አደባባይ ወሰዱት ፤ ዐመፀኞች ሹማምንት ይሙት በቃ ፈረዱበት በጎ ስለ አደረገላቸው ፈንታ ክፉ መለሱለት።
መዝ 35(34)፥11-12 ፣
ዮሐ 10፥32-33፣ 11፥49፣ 15፥25

❖ ነፍሱን ከሥጋው እስከ መለየት ደርሶ በሁሉ መከራን ታግሠ፤ ሞቱም በመስቀል የተደረገው ነው፤ በአንደበቱ አንድ ነገርን ስንኳ አልተናገረም።
ፊልጵ 2፥5-9

❖ ከመስቀሉ ወደ ሲኦል በመውረዱ አዳነን፤ በአባታቸው በአዳም በደል ፤ በሲኦል ተግዘው የነበሩ ጻድቃንን ፈታ፤ ከሙታን ተለይቶ አስቀድሞ በተነሣ በእውነተኛ ትንሣኤውም አስነሣን ፤ የንስሓንም በር ከፈተልን።
ሮሜ 1፥25፣ 5፥12–21

❖ የሰማዩ አባታችን እያልን አብን እንጠራው ዘንድ ሥልጣን ሰጠን ፤ ወንድሞቼም አለን ፤ ነፍስን ሥጋን በመዋሐድ መሰለን።
ማቴ 7፥9፣ 25፥40 ፤
ሮሜ 8፥16 ፤
ዕብ 11–14

እግዚአብሔር የቅዱሳን ሃይማኖት በሆነች በቅድስት ተዋሕዶ እስከ ፍጻሜ ያጽናን

"የሚሰማኝ ግን በእርጋታ ይቀመጣል ከመከራም ሥጋት ያርፋል"
ምሳ 1፥33

  አዘጋጅ
  ዲ/ን ቡሩክ ይርጋ

ምንጭ
ፍኖተ ቅዱሳን



ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ፤ እኔም ለእናንተ ከአዘጋጀው በኃዋላ በድካሜ ብዛት ሳይገባኝና ሳይገባኝ በምጽፈው ድርሳንወ ገድላት መጽሐፍት ላይ የቃላት (የፊደል) ሕፀፅ ቢገኝ በጎደለው እየሞላችሁ በጠመመው እያቃናችሁ አንብቡ በረከት ተካፈሉ እላለሁ ከምንም ጊዜ በላይ ለሀገራችንና ለዓለም ሰላም እንዲሁም ለደካማው ወንድማችሁ እንድበረታ (የተጣልሁ) እንዳልሆን ስለ እኔ ጸልዩ
  
"አንተ ሰው ቃለ እግዚአብሔርን ተማር፤ ባትለወጥም ዝም ብለህ ተማር! ኹልጊዜ ተማር። ላትስተካከል ትችላለህ፤ ላትለወጥ ትችላለህ፤ ግን ተማር፤ ቢያንስ ቢያንስ ጥሩ ሰው እንኳን ባትኾን ራስህን ለመውቀስ የምትችልበት ዓቅም ታገኛለህ፤ ካልተማርክ ግን ራስህን እንኳን መውቀስ የምትችልበት ዓቅም አታገኝም፤ ስለዚህ ተማር ስትማር ቢያንስ ኃጢአት እንኳን ስትሠራ ራስህን እየወቀስክ ትሠራለና፤ ይህች የንስሐ በር ትኾንልሃለች፤ አንድ ቀን ወደ ንስሐም ትመራሃለች"
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ



               ወስብሐት ለእግዚአብሔር
                            ይቆየን

ትምህርቱ እንዴት ነው......የእናተ አስተያየትና ጥያቄ ከዚህ የበለጠ ለመትጋት ይረዳልና መልእክት ይተውሉኝ፤ የተሳተውን፤ የተረሳው፤ የተገደፈውን፤ የነጠፈውን በቀና መንፈስ አቃንታቹ አንብቡት ቸሩ መድኃኔዓለም ማስተዋሉን ያድለን፤ በፀሎታቹ አስቡኝ አትርሱኝ የተለያየ ጽሁፍ ያላቹ፣ መተረክ እንችላለን የምትሉ እና ካርድ በመግዛት ቻናሉንና ግሩፑን በተለያየ አገልግሎት ማገዝ የምትፈልጉ በውስጥ መስመር አናግሩኝ።

Coment
@Tewahedo12_bot


 ───────────

Channel
 
https://telegram.me/Tewahedo12

Group
https://telegram.me/OrthodoxTewahedo12

Facebook Like Page (የፌስቡክ ፔጅ)
  
http://facebook.com/Tewahedo12

YouTube Subscribe (ሰብስክራይብ)
https://www.youtube.com/channel/UCvYxUdv1D-5juH_P6iE7XXw

 ───────────
489 viewsedited  12:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 15:09:31

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ
           አሜን  

"በበጎ ሥራ ሁሉ ፍሬ እያፈራችሁ በእግዚአብሔርም እውቀት እያደጋችሁ፤ለጌታ እንደሚገባ ትመላለሱ ዘንድ እንለምናለን"
ቆላስይስ 1፥10-11


ክፍል አስራ ዘጠኝ
✥••┈••●◉ ✞ ◉●••┈••✥
ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ንጽሕይት የቅዱሳን ሃይማኖት
(በቅዱስ ጎርጎርዮስ)
✥••┈••●◉ ✞ ◉●••┈••✥

❖ እግዚአብሔር አብን በመልክ የሚመስለው ፤ በባሕርይ የሚተካከለው ኢየሱስ ክርስቶስ ሰው የሆነበትን ሥራ በልቡናችሁ ዕወቁ ፤ ሽቶ [ቀምቶ] ከእግዚአብሔር ጋር የተካከለ አይደለም ፤ ራሱን አዋርዶ ፤ ሰው ሆኖ የተገዥ ባሕርይን ተዋሕዶ ነው እንጂ።
ፊልጵ 2፥1-8

❖ ሥጋን ከመዋሐድ በቀር የበለጠ በእግዚአብሔር ዘንድ ምን ድኅነት አለ ? ነገር ግን እርሱ ነገሥታትን ፤ መኳንንትን የሚገዛ ሲሆን እኛን ወደ መምሰል በመጣ ጊዜ ፤ የተገዥ ባሕርይንም በተዋሐደ ጊዜ ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ አላነሰም።

❖ ምድርን የፈጠረ እርሱን በትውልድ እንበልጣለን የሚሉ ሐና ቀያፋ ዘበቱበት ፤ ፍጥረትን ሁሉ የሚገዛ እርሱ የሚያርፍበት ቦታ አላገኘም ፤ በሥጋ በተወለደ ጊዜ ላሞች በሚያድሩበት በረት አስተኙት እንጂ።
መዝ 24(23)፥1 ፣ 97(93)፥2 ፣ 46(45)፥13
ማቴ 8፥20፤
ሉቃ 2፥1-7

❖ የማይለወጥ ንጹሕ ቃል የሚለወጥ የሰውን ባሕርይ ተዋሐዶ የሰውንም ሥራ ገንዘብ አደረገ፤ ነፍሱን ከሥጋው እስከ መለየት ደርሶ ትሕትናን አብዝቶ ሠራ። መዝ 12(11)፥6 ፤
ፊልጵ 2፥8

❖ በነፍስ በሥጋ የሚፈርድ እርሱን ይሞት በቃ ወደሚፈረድበት አደባባይ አወጡት፤ ሊቃነ መላእክትን ሁሉ ፈጥሮ የሚገዛ እርሱ በኃጥአን እጅ ተያዘ ፤ ሕይወት እርሱ ሞተ።
ማቴ 17፥22፤
ዕብ 2፥5-10

❖ እኛ ግን በፈቃዳችን የጠላታችን የዲያብሎስን ማታለል በመቀበላችን ከሕይወት ሞትን ፤ ከተድላ ደስታ ኃሣርን መርጠን ወደን በሠራነው ኃጢኣት ፍጻሜ ወደ ሌለው ወደ ዘላለም ኵነኔ በሚወስድ በሚጐዳ መከራ ውስጥ ወደቅን፤ እርሱስ ፈጽሞ አልተወንም ፤ በከሀሊነቱ ተቀበለን እንጂ፤ በይቅርታው በቸርነቱ ብዛት ወዶ እርሱ አቀረበን እንጂ።
ኤፌ 2፥18

❖ እንግዲህ ወዲህ የእጆቹ ፍጥረቶች ወድቀን እንድንቀር አልወደደም፤ በቸርነቱ፤ በይቅርታው ብዛት የሚታየውን ፤ የማይታየውን ሁሉ የፈጠረበትን አካላዊ ቃሉን ላከልን እንጂ ፤ የሚታዩት ያላቸው የሚዳሠሱ ፍጥረቶች ናቸው ፤ የማይታዩ ያላቸውም ረቂቃን መላእክት ናቸው፡፡
መዝ 107(106)፥20 ፤
ዮሐ 1፥1-14

❖ በከበሩ በነቢያት ቃል አስቀድሞ እንዳናገረ ከተመሰገኑ ከሦስቱ አንዱ አካል ቀዳማዊ ቃል በግብረ መንፈስ ቅዱስ ከቅድስት ድንግል ማርያም ሥጋን ተዋሐደ፤ ሰው መሆኑም እውነተኛ የማይመረመር የማይነግር ምሥጢር ነው፤ ሰው መሆኑም እውነተኛ ነው እንጂ ምትሐት አይደለም ፤ መከራን ፤ ረኀብን ፤ ጽምእን ፤ ድካምን በመቀበል ከእኛ ጋር አንድ የሚሆን ሥጋን በፈቃዱ ፣ በአባቱ በመንፈስ ቅዱስም ፈቃድ ፈጥሮ ተዋሐደ እንጂ፤ ወንጌላውያን እንደመሰከሩ። ማቴ 1፥18-25
ሉቃ 1፥21–34
ዮሐ 4፥6፣ 19፥28

❖ ቃል ከርሷ [ከእመቤታችን] የነሣውን ሥጋ በአብ ፈቃድ ፤ በርሱ ፈቃድ ፤ በመንፈስ ቅዱስም ፈቃድ ፣ ሐሰት ያይደለ እውነተኛ ተዋሕዶን ከመለኮቱ ጋር አዋሐደ ፤ በአብ ከርሱም አንድ ባሕርይ ፣ አንድ ፈቃድ ፣ አንድ ሥልጣን ፣ አንድ የእግዚአብሔር ወልድ አካል አደረገው ፤ በቀዳማዊ ባሕርይ የአምላክነት ሥራ ሁሉ ገንዘቡ ነው፤ ዳግመኛም ከእኛ በነሣው ከእርሱም ጋር አንድ አካል አንድ ባሕርይ በሆነ በሥጋ ባሕርይ ከኃጢአት ብቻ በቀር የሰውነት ሥራ ሁሉ ገንዘቡ ነው።
ዮሐ 8፥46

❖ በእናቱ ማኅፀን ሳለ ዮሐንስ የሰገደለት ይህ ነው ፤ በተወለደ ጊዜ መላእክት ያመሰገኑት ይህ ነው፤ የከብት ጠባቆች ልደቱን የተናገሩለት ይህ ነው ፤ በተወለደ ጊዜ ጥበብ ያላቸው ሰዎች እጅ መነሻ ይዘው መጥተው የአይሁድ ንጉሥ እንደ ሆነ እየተናገሩ የሰገዱለት ይህ ነው።
ሉቃ 1፥39-45
ማቴ 2፥1-12

❖ ስለዚህ ስለመሰለውም መጻሕፍት እርሱ በሠራው ሁሉ ወንድሞቹን እንደመሰላቸው ተናገሩ ፤ እንግዲያማ ሰማይ ምድርን የፈጠረ ሲሆን እንደምን የአይሁድ ንጉሥ በተባለ ነበር።
ዕብ 2፥12-17

❖ ሁለት ግብራት ለርሱ አንድ እንደሆኑ አየህን? ሰው የሆነ አምላክ እርሱ ነው፤ አንድ ነው ፤ ሁለት አይደለም፤ ፈጣሪ መለኮቱን ፍጡር ወደመሆን አልለወጠውም ፍጡር ሥጋውንም ፈጣሪ ወደ መሆን አልለወጠውም፤ መቼም መች አንድ ብቻ ነው ሁለት አይደለም ።
336 viewsedited  12:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 12:49:04

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ
           አሜን

"በበጎ ሥራ ሁሉ ፍሬ እያፈራችሁ በእግዚአብሔርም እውቀት እያደጋችሁ፥
ለጌታ እንደሚገባ ትመላለሱ ዘንድ እንለምናለን"
ቆላስይስ 1፥10-11

                    ቀናችንን በጸሎት እንጀምር

    ✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥
 ልጄ ሆይ ከሰው ጋ በሰላም ለመኖር የሚረዱህ ምክሮች እነሆ       
    ✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥

❖ ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ፤ “ሁለተኛይቱም ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ የምትል እርስዋን የምትመስል ይህች ናት፤ ከእነዚህ የምትበልጥ ሌላ ትእዛዝ የለችም”
ማር 12፥3

❖ ለመስማት እንጂ ለመናገር አትፍጠን፤
“ስለዚህ፥ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ፥ ሰው ሁሉ ለመስማት የፈጠነ ለመናገርም የዘገየ ለቍጣም የዘገየ ይሁን፤”
ያዕ 1፥19

❖ ይቅር ስትል ቂም አትያዝ፤
"እርስ በርሳችሁ ትዕግሥትን አድርጉ፥ ማንም በባልንጀራው ላይ የሚነቅፈው ነገር ካለው፥ ይቅር ተባባሉ፤ ክርስቶስ ይቅር እንዳላችሁ እናንተ ደግሞ እንዲሁ አድርጉ፤ በእነዚህም ሁሉ ላይ የፍጻሜ ማሰሪያ የሆነውን ፍቅርን ልበሱት"
ቆላ 3፡13-14

❖ በሁሉም ነገር ትዕግሥተኛ ሁን፤
“ፍቅር ይታገሣል፥ ቸርነትንም ያደርጋል፤ ፍቅር አይቀናም፤ ፍቅር አይመካም፥ አይታበይም፤”
1ኛ ቆሮ 13፥4

❖ ሳትሰስት ሰጥ፤
“ኀጥእ ቀኑን ሁሉ ምኞትን ይመኛል፤ ጻድቅ ግን ይሰጣል፥ አይሰስትም”
ምሳሌ 21፥26

❖ የሰው ንግግር ሳታቋርጥ አዳምጥ፤
“ሳይሰማ ነገርን በሚመልስ ስንፍናና እፍረት ይሆንበታል”
ምሳሌ 18፥13

❖ መልስ ስትመልስ አትከራከር፤
“ጥል ባለበት ዘንድ እርድ ከሞላበት ቤት በጸጥታ ደረቅ ቍራሽ ይሻላል”
ምሳሌ 17፥1

❖ የገባኽውን ቃል ጠብቅ፤
“የምትዘገይ ተስፋ ልብን ታሳዝናለች፤ የተገኘች ፈቃድ ግን የሕይወት ዛፍ ናት”
ምሳሌ 13፥12)

❖ ሰውን ስታምን ካለመጠራጠር ይሁን፤
"ሁሉን ይታገሣል፥ ሁሉን ያምናል፥ ሁሉን ተስፋ ያደርጋል፥ በሁሉ ይጸናል”
1ኛ ቆሮ 13፥7

❖ ሰዎች ላይ ክፉ አታስብ፤
“በመጥፎና በጠማማ ትውልድ መካከል ያለ ነቀፋ የዋሆችም ነውርም የሌለባቸው የእግዚአብሔር ልጆች እንድትሆኑ ሳታንጐራጉሩ ክፉም ሳታስቡ ሁሉን አድርጉ፤”
ፊል 2፥14-15

❖ ይቅር መባባልን ሁሌም አትዘንጋ፤
"መራርነትና ንዴት ቁጣም ጩኸትም መሳደብም ሁሉ ከክፋት ሁሉ ጋር ከእናንተ ዘንድ ይወገድ፤ እርስ በርሳችሁም ቸሮችና ርኅሩኆች ሁኑ፥ እግዚአብሔርም ደግሞ በክርስቶስ ይቅር እንዳላችሁ ይቅር ተባባሉ"
ኤፌሶን 4፥31-32

"የሚሰማኝ ግን በእርጋታ ይቀመጣል ከመከራም ሥጋት ያርፋል"
ምሳ 1፥33

"
#ወአንቢበክሙ አንትሙ #ለዘኢያንበበ አይድኡ
#እናንተ_አንብባችሁ_ላላነበበው_ንገሩ"



ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ፤ እኔም ለእናንተ ከአዘጋጀው በኃዋላ በድካሜ ብዛት ሳይገባኝና ሳይገባኝ በምጽፈው ድርሳንወ ገድላት መጽሐፍት ላይ የቃላት (የፊደል) ሕፀፅ ቢገኝ በጎደለው እየሞላችሁ በጠመመው እያቃናችሁ አንብቡ በረከት ተካፈሉ እላለሁ ከምንም ጊዜ በላይ ለሀገራችንና ለዓለም ሰላም እንዲሁም ለደካማው ወንድማችሁ እንድበረታ (የተጣልሁ) እንዳልሆን ስለ እኔ ጸልዩ

"ልብህን በእርጋታ አኑረው፤ የሁሉም መጨረሻ እና የሁሉም አገልጋይ ለመሆን በጣም ትጋ ለከንቱ ንግግር ዘገምተኛና ሰነፍ ሁን፤ ነገር ግን የቅዱሳት መጻህፍትን ቃል በማወቅ በመስማት ድኅነትን የሚሰጡ ናቸውና ብልህ ሁን"
ታላቁ ባስልዮስ ዘቂሳሪያ

               ወስብሐት ለእግዚአብሔር
                              ይቆየን 

───────────
                    Channel
   
https://telegram.me/Tewahedo12

        FB Like Page (የፌስቡክ ፔጅ)
 
http://facebook.com/Tewahedo12  

        YouTube Subscribe (ሰብስክራይብ)
https://www.youtube.com/channel/UCvYxUdv1D-5juH_P6iE7XXw
 ───────────
508 views09:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 07:18:06 የበቃሁ ነኝ" የሚባለው መቼ ነው?

❖ በአንድ ገዳም ውስጥ የሚኖር መነኩሴ ነበር፤ ከገዳሙ አበምኔት ጋርም ስለመንፈሳዊ ሕይወታቸው እያነሱ ሲወያዩ
"አባቴ እኔ ዛሬ የዓለምን ኋጢአት ግፍና በደል አየሁ፤ ስለዚህ የበቃሁ ሆኛለሁ" ብሎ አጫወታቸው፤ አበምኔቱም " ወንድሜ ሆይ እስቲ በርትተህ ጸልይ ገና ነህ" ብለው መለሱለት።

❖ እንዲሁም በሌላ ግዜ ወደ አበምኔቱ ቀርቦ
" አባቴ አሁንስ በቅቻለሁ ቅዱሳን መላእክት ከሰማይ ሲወጡና ሲወርዱ የሕዝቡንም ኋጢአት ሲያስተርዩ አይቻለሁ" አላቸው።

"ልጄ ሆይ ገና ነህ፥ አሁንም በርታና ጸልይ" ብለው ሸኙት፡፡

❖ ይህም መነኩሴ ወደ ዋሻው ገብቶ ኣብዝቶ ይጾምና  ይጸልይ ጀመር፤ ይህም መነኩሴ ወደ ዋሻው ገብቶ አብዝቶ ይጾምና ይጸልይ ጀመር፤ ለሶስተኛ ጊዜ ስላየውም ራእይ  ለአበምኔቱ እንዲህ ሲል ገለጠላቸው፡፡

" አባቴ ሆይ ዛሬስ በዓለም ሳለሁ የሰራሁትን ኋጢአት ሁሉ አንድ በአንድ አሳየኝ"  አላቸው እርሳቸውም " ልጄ የበቃኸው አሁን ነው" ብለው አሰናበቱት።

❖ ክርስቲያናዊ ሕይወት ምድራዊ ፍላጎቶችንና የሰይጣን ሸንገላ በመቃወም ሰማያዊ መንግስት የሚወረስበት ምሥጢር በመሆኑ ፈተናውን የዛኑ ያህል ከበድ ይላል፤ ብዙ ሰዎች ወደ
ቤተክርስቲያን መመላለስ ቃለ እግዚአብሔር መማር ሲጀምሩ የራሳቸው ኋጢአት እያሰቡ ከማልቀስ እና ንስሐ ከመግባት ይልቅ የሌላውን በደል መቁጠር ይጀምራሉ፡፡

❖"እነ እገሌ እንኳን እንዲህ አደረጉ ጉድ ነው!"  ማለት ያበዛሉ።

❖ ሌላውን ሲመለከቱ ሊድኑበት የሚችሉበትን ወርቃማ የንሰሐ ጊዜ በከንቱ ያበላሹታል፤ መጽሓፍ ግን
"ለዚህ ዓለም ከማይመችና የአረጊቶችን  ሴቶች ጨዋታ ከሚመስለው ተረት ራቅ" ይላል።
1ኛ ጢሞ 4፥7

❖ ይህ መነኩሴ የተገለጠለት ራእይ ለመዳኑ የጠቀመው የራሱን ኋጢአት ያየ ጊዜ መሆኑን ከታሪኩ መረዳት እንችላለን፤ እኛስ የሚታየን የማን ኋጢአት ነው? የራሳችን ወይስ የሌላው?
770 views04:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 06:26:25               ✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥
"የሚሰማኝ ግን በእርጋታ ይቀመጣል ከመከራም ሥጋት ያርፋል"
ምሳ 1፥33
                       
#ስንክሳር          
               ዘነሐሴ
#ሃያ አምስት (፳፭)        
              ✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥
468 viewsedited  03:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 19:18:45 ከአክራሪ እስልምና ወደ ክርስትና
#በእውነተኛ_ታሪክ_ላይ_የተመሰረተ
ክፍል 1
#ባለታሪክ_እና_ጸሀፊ
ናሕድ ማሕሙድ ሙቱዋሊ
#ተርጓሚ ዲ/ን ዳንኤል ክብረት

ናታኒም ቲዩብ SUBSCRIBE በማድረግ አገልግሎቱን ያበረታቱ ናታኒም ማለት የእግዚአብሔር ቤት ጠራጊ ታናሽ አገልጋይ ማለት ነውና።






47 views16:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 19:18:17 ✥•••••••••••••••••••●◉ ✞ ◉●•••••••••••••••••••✥

"ልብህን በእርጋታ አኑረው፤ የሁሉም መጨረሻ እና የሁሉም አገልጋይ ለመሆን በጣም ትጋ ለከንቱ ንግግር ዘገምተኛና ሰነፍ ሁን፤ ነገር ግን የቅዱሳት መጻህፍትን ቃል በማወቅ በመስማት ድኅነትን የሚሰጡ ናቸውና ብልህ ሁን"
ታላቁ ባስልዮስ ዘቂሳሪያ

በነሐሴ ወር
#በጠዋትና በማታ #የሚነበቡ የእየለታት #የመጽሐፍ ቅዱስ #ክፍሎች

#ነሐሴ


“ስለዚህ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ ሰው ሁሉ ለመስማት የፈጠነ ለመናገርም የዘገየ ለቍጣም የዘገየ ይሁን”
ያዕቆብ 1፥19

መልካም ንባብ

✥•••••••••••••••••••●◉ ✞ ◉●•••••••••••••••••••✥

Share
🇹 🇪 🇼 🇦 🇭 🇪 🇩 🇴
✥••┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈••✥

@Tewahedo12

@OrthodoxTewahedo12

✥••┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈••✥
41 views16:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ