Get Mystery Box with random crypto!

✞ ተዋሕዶ ✞ 🇹 🇪 🇼 🇦 🇭 🇪 🇩 🇴

የቴሌግራም ቻናል አርማ tewahedo12 — ✞ ተዋሕዶ ✞ 🇹 🇪 🇼 🇦 🇭 🇪 🇩 🇴
የቴሌግራም ቻናል አርማ tewahedo12 — ✞ ተዋሕዶ ✞ 🇹 🇪 🇼 🇦 🇭 🇪 🇩 🇴
የሰርጥ አድራሻ: @tewahedo12
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 10.16K
የሰርጥ መግለጫ

"ሥርዓትን እማር ዘንድ ያስጨነከኝ መልካም ሆነልኝ"
መዝ 118 (119) ፥ 71
ይህ ቻናል የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ዶግማንና ቀኖናን ትውፊትን እንዲሁም አስተምሮን የጠበቁ የተለያዩ የሚያስተምሩ ነገሮች ይለቀቁበታ፡፡ ግሩፑ
http://t.me/OrthodoxTewahedo12
ይህ Channel #ሐምሌ 26/2010 ዓ.ም አ/ጀመረ
ለአስተያየት 📥 ➩ @Tewahedo12_bot

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-07-07 14:35:09 https://telegra.ph/ፖርኖግራፊ-ምንድን-ነው-10-12
284 views✞ ባሮክ ✞, 11:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-07 08:01:34 https://telegra.ph/መጥምቁ-ዮሐንስ-በእናቱ-ማሕፀን-ስላቀረበው-ስግደት-ያዕቆብ-ዘሥሩግ-ያቀረበው-ቅኔያዊ-ውዳሴ-07-07-2
482 views✞ ባሮክ ✞, 05:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-06 20:33:24               ✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥
"የሚሰማኝ ግን በእርጋታ ይቀመጣል ከመከራም ሥጋት ያርፋል"
ምሳ 1፥33
                       
#ስንክሳር          
               ዘሰኔ
#ሰላሳ (፴)        
              ✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥
526 views✞ ባሮክ ✞, 17:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-06 20:32:48 ✥•••••••••••••••••••●◉ ✞ ◉●•••••••••••••••••••✥

"ልብህን በእርጋታ አኑረው፤ የሁሉም መጨረሻ እና የሁሉም አገልጋይ ለመሆን በጣም ትጋ ለከንቱ ንግግር ዘገምተኛና ሰነፍ ሁን፤ ነገር ግን የቅዱሳት መጻህፍትን ቃል በማወቅ በመስማት ድኅነትን የሚሰጡ ናቸውና ብልህ ሁን"
ታላቁ ባስልዮስ ዘቂሳሪያ

በሰኔ ወር
#በጠዋትና በማታ #የሚነበቡ የእየለታት #የመጽሐፍ ቅዱስ #ክፍሎች

#ሰኔ


“ስለዚህ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ ሰው ሁሉ ለመስማት የፈጠነ ለመናገርም የዘገየ ለቍጣም የዘገየ ይሁን”
ያዕቆብ 1፥19

መልካም ንባብ

✥•••••••••••••••••••●◉ ✞ ◉●•••••••••••••••••••✥

Share
🇹 🇪 🇼 🇦 🇭 🇪 🇩 🇴
✥••┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈••✥

@Tewahedo12

@OrthodoxTewahedo12

✥••┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈••✥
622 views✞ ባሮክ ✞, 17:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-06 20:29:11 https://telegra.ph/ስንክሳር-ዘወርኀ-ሰኔ-06-28-8
475 views✞ ባሮክ ✞, 17:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-06 16:02:22 https://telegra.ph/አዋልድ-መጽሐፍት-08-24
634 views✞ ባሮክ ✞, 13:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-06 12:11:29
ሽሽታችሁ በክረምት .....እንዳይሆን ፅልዩ
ማቴ 24÷20

➯ እንደሚታወቀው በሀገራችን ክረምት ተብሎ የሚጠራው "ከሰኔ 26 እስከ መስከረም 25" ያለውን ያጠቃልላል፤ በዚህ ወራት ቤተ ክርስቲያን የእግዚአብሔርን መግቦቱን ቸርነቱን በዝናብ አብቅሎ ማብላቱን ትሰብካለች፤ በተጨማሪም የዳግም ምፅአቱን ነገር አበክራ ትናገርበታለች፤ ምክንያቱም ጌታ ዳግም የሚመጣው የት ነበራችሁ ምን ሰራችሁ ብሎ መዝኖ ዋጋ ሊሰጠን ነውና፤ የፅድቅ ፋሬ አፋርተን ካልጠበቅን መጠጊያ መሸሻ አጥተን የምንጨነቅበት ቀን ነውና ተዘጋጁ ትለናለች፡፡

➯ ታዲያ ወርሃ ክረምት ከዚህ ጋር ምን አገናኝው ስንል እንደሚታወቀው ገበሬው በቤት ውስጥ ያለውን እኽል አውጥቶ ዘርቶ በመጀመርያው ቡቃያውን ለማየት ይጓጓል ቀጥሎም ቡቃያውንና ቅጠሉን እያየ ወደፊት ደግሞ አበባና ፍሬን ለማየት ወርኃ ጽጌን በተስፋ ይጠብቃል፤ በዚህ ግዜ ሽሽት ቢመጣ ለመንገድ የሚሆን ስንቅ የለውምና ከባድ ይሆንበታል ፡፡

➯ ሊቃውንት ቤተክርስቲያንም ይህን መሠረት አድርገው ቡቃያና ቅጠል እንጂ ፍሬ በማይገኝበት ክረምት ስደት አስቸጋሪ እንደሆነ ሁሉ መንፈሳዊ ፍሬ ሳናፈራ የጽድቅ ሥራ ሳንሰራ ጌታ ለፍርድ መጥቶ የት ነበራችሁ? ምን ሰራችሁ? ባለን ጊዜ ምክንያትና  ምላሽ እንዳናጣ በሃይማኖት ቁመን ትሩፋት እንድንሰራና መጨረሻየን አሳምርልኝ ፍሬ ሳላፈራ ቀኑ እንዳይደርስብኝ እርዳኝ እያልን በጸሎት እንድንተጋም ያስተምረናል።

ምንጭ
ብጽእ አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ
ስምዐ ጽድቅ
726 views✞ ባሮክ ✞, 09:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-06 06:44:48

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ
           አሜን

"በበጎ ሥራ ሁሉ ፍሬ እያፈራችሁ በእግዚአብሔርም እውቀት እያደጋችሁ፥
ለጌታ እንደሚገባ ትመላለሱ ዘንድ እንለምናለን"
ቆላስይስ 1፥10-11

                    ቀናችንን በጸሎት እንጀምር

    ✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥
ቅዱስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ እንዲህ አለ       
    ✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥

“ከልቦቻችን በማይነቀሉ የፍቅሩ ችንካሮች ተቸነከርን፤ ያዝነው አንለቀውም እርሱም አቀፈን አልተወንም ወደ እርሱ በሃይማኖት አቀረበን ከእርሱም ወደ ቀኝ ወደ ግራ አንሸሽም እንደ ቀለበት በልባችን እንደ ማኅተም በክንዳችን አኖርነው እንደ ዕንቁ በልባችን ሳጥን አስቀመጥነው እንደ ወርቅ በሕሊናችን መዝገብ አኖርነው እንደ ግምጃ ለበስነው እንደ ሐር ግምጃ ተጎናጸፍነው እንደ ወታደር ሰይፍ ታጠቅነው ለጦር ዕቃ እንደተዘጋጀ የድል ጋሻ ተደገፍነው ተከዜና ግዮን በኢሎል ወር እንደሚሞሉ ፍቅሩ በልባችን መልቶአል እንደ መከር ጊዜ የዮርዳኖስ ወንዝ እንደ ክረምት ጊዜም የጤግሮስ ወንዝ ስንዴ ሲያሹት እንደሚሆን እንደ ኤፍራጥስ ወንዝ ልባችንን በወንጌል ፈሳሽነት አረሰረሰው፤ መርከባችንንም በሃይማኖት ወንዝ አስዋኘው"
መጽሐፈ ምሥጢር 24፥20

"ከእኛ ወገን ክርስቲያን እየተባሉ በገዛ መንገዳቸው የሚኖሩ ብዙዎች ናቸው ... የእንስሳ ሥጋ ከመብላት የሚከለከሉ የሰውን ሥጋ ለመብላት ግን የሚተጉ እነዚህ ናቸው"

"ስምዖን ጴጥሮስ ከሐዋርያት ሁሉ አብልጦ ክርስቶስን ወደደው፤ ክርስቶስ ግን ከሐዋርያት ሁሉ አልቆ ወንጌላዊው ዮሐንስን ይወድደው ነበር፤ ስለወደደው ግን አለቃ መሆንን ለዮሐንስ አልሠጠም እርሱ ከወደደው በላይ እርሱን የሚወደውን አለቃ አደረገው እንጂ"

"ክርስቶስን መውደድ ከወንድሞቹ ይልቅ በጴጥሮስ ላይ በዛ ከወንድሞቹ ይልቅ ወደ ጌታ ኢየሱስ ለመድረስ ቸኩሏልና ከመርከቢቱ ዘልሎ ወደ ባሕር ተወረወረ እንጂ በመርከብ ለመጎተት አልቆየም ወደ ወደደው ለመድረስ ቀደማቸው ከመርከቢቱ ላይ ያዘለለችው ወደ ጥልቁም ባሕር የወረወረችው ፍቅር እርስዋ የክህደቱን መጽሐፍ ደመሰሰችለት፤ ራሱን ወደ ጥልቁ የጥብርያዶስ ባሕር በወረወረ ጊዜ የዕዳው መጽሐፍ ሰጠመ፤ እርሱ ግን በብዙ ጭንቅ በብዙም ፍለጋ በዋናተኞችም በብልጠታቸው ጥበብ እንደሚገኝ እንደሚያበራ ዕንቁ ሆኖ ከባሕር ውስጥ ወጣ"

"የሚሰማኝ ግን በእርጋታ ይቀመጣል ከመከራም ሥጋት ያርፋል"
ምሳ 1፥33

ምንጭ
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ከመጽሐፈ ምሥጢር ውብ ገጾች



ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ፤ እኔም ለእናንተ ከአዘጋጀው በኃዋላ በድካሜ ብዛት ሳይገባኝና ሳይገባኝ በምጽፈው ድርሳንወ ገድላት መጽሐፍት ላይ የቃላት (የፊደል) ሕፀፅ ቢገኝ በጎደለው እየሞላችሁ በጠመመው እያቃናችሁ አንብቡ በረከት ተካፈሉ እላለሁ ከምንም ጊዜ በላይ ለሀገራችንና ለዓለም ሰላም እንዲሁም ለደካማው ወንድማችሁ እንድበረታ (የተጣልሁ) እንዳልሆን ስለ እኔ ጸልዩ

"ልብህን በእርጋታ አኑረው፤ የሁሉም መጨረሻ እና የሁሉም አገልጋይ ለመሆን በጣም ትጋ ለከንቱ ንግግር ዘገምተኛና ሰነፍ ሁን፤ ነገር ግን የቅዱሳት መጻህፍትን ቃል በማወቅ በመስማት ድኅነትን የሚሰጡ ናቸውና ብልህ ሁን"
ታላቁ ባስልዮስ ዘቂሳሪያ

               ወስብሐት ለእግዚአብሔር
                              ይቆየን 

───────────
                    Channel
   
https://telegram.me/Tewahedo12

        FB Like Page (የፌስቡክ ፔጅ)
 
http://facebook.com/Tewahedo12  

        YouTube Subscribe (ሰብስክራይብ)
https://www.youtube.com/channel/UCvYxUdv1D-5juH_P6iE7XXw
 ───────────
684 views✞ ባሮክ ✞, 03:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-06 06:44:22               ✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥
"የሚሰማኝ ግን በእርጋታ ይቀመጣል ከመከራም ሥጋት ያርፋል"
ምሳ 1፥33
                       
#ስንክሳር          
               ዘሰኔ
#ሃያ ዘጠኝ (፳፱)        
              ✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥
392 views✞ ባሮክ ✞, 03:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-06 06:43:49 ✥•••••••••••••••••••●◉ ✞ ◉●•••••••••••••••••••✥

"ልብህን በእርጋታ አኑረው፤ የሁሉም መጨረሻ እና የሁሉም አገልጋይ ለመሆን በጣም ትጋ ለከንቱ ንግግር ዘገምተኛና ሰነፍ ሁን፤ ነገር ግን የቅዱሳት መጻህፍትን ቃል በማወቅ በመስማት ድኅነትን የሚሰጡ ናቸውና ብልህ ሁን"
ታላቁ ባስልዮስ ዘቂሳሪያ

በሰኔ ወር
#በጠዋትና በማታ #የሚነበቡ የእየለታት #የመጽሐፍ ቅዱስ #ክፍሎች

#ሰኔ


“ስለዚህ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ ሰው ሁሉ ለመስማት የፈጠነ ለመናገርም የዘገየ ለቍጣም የዘገየ ይሁን”
ያዕቆብ 1፥19

መልካም ንባብ

✥•••••••••••••••••••●◉ ✞ ◉●•••••••••••••••••••✥

Share
🇹 🇪 🇼 🇦 🇭 🇪 🇩 🇴
✥••┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈••✥

@Tewahedo12

@OrthodoxTewahedo12

✥••┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈••✥
480 views✞ ባሮክ ✞, 03:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ