Get Mystery Box with random crypto!

ቢኒ የመጻሕፍት ግብዣ

የቴሌግራም ቻናል አርማ binibook — ቢኒ የመጻሕፍት ግብዣ
የቴሌግራም ቻናል አርማ binibook — ቢኒ የመጻሕፍት ግብዣ
የሰርጥ አድራሻ: @binibook
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.36K
የሰርጥ መግለጫ

👉 ሰሞነኛ ትኩስ መፅሐፍት ከነድስቱ እንገጮታለን።
👉 ዘርፈ ብዙ የሆነውን የኪነት ወሬ እስከነቃጭሉ ዱብ እናረጋለን።
👉 ነባርና አዳዲስ መፅሐፍትን መጠነኛ ዳሰሳ አድርገን እንጠቁሞታለን።
✴ ወሬ ጥሩ ስለሆነ በዚህ ቦይ ላኩልኝማ @a3b2ysm

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-31 06:56:11 #ሰው ግብሩ የሰይጣን ቢሆንም መጠሪያ ስሙን ግን ማንም አምኖ መቀበል አይፈልግም። - እማማ ቸርነት (እረኛዬ)

ያቺ ሴት፥ ልጅ መውለድ ትፈልግና ፈጣሪዋን ለምና ለምና ... ተስፋ ትቆርጥና፥ "እንደው ልጅ ከሰጠኸኝ ... በእጄ ጋቢ ፈትዬ ስለቱን አገባልሃለሁ!" ብላ ለሰይጣን ትሳላለች። ጉድ በሉ እንግዲህ! ... እንዳለችውም ስለቷ ይደርስና ልጅ ትወልዳለች። ታዲያ እንግዲህ ለሰይጣን ስለቱን የት አግኝታ ትስጠው? ሰይጣን ቤቱ የት ነው? ...

ይገርማችኋል ... እንደው እዛ ሰፈር ላይ አንድ መለኛ የሆኑ መካሪ ... እንዴት ያሉ አባት አሉ? ትሄድና ለሳቸው "እንዲህ ሆኖ፥ እንዲህ ተስዬ፥ ልጅ ወልጄ፥ አሁን የት አግንቼ ልስጠው?" ብላ ስታማክራቸው ... ምን ይሏታል፦ "... ሁለት ወንድማማች ተጣልተው ... ሸንጎ ፊት ሲሟገቱ እድምተኛ ሁኚ። ከዚያም ... ለማስታረቅ ያስቸገረው፥ ሸንጎ ረግጦ ሲወጣ ጠብቀሽ ለሱ ስጪው። እሱ ነው ሰይጣኑ ... ለሱ ስጪው!" አሉ። ...

አያችሁ! እሷም እንደተባለችው ሸንጎ ትሄድና ... ሁለት ወንድማማቾች ሲሸመገሉ ትደርሳለች። ከዚያማ አንዱ ያዙኝ ልቀቁኝ ብሎ ለሽምግልና አስቸግሮ፥ ሸንጎውን ረግጦ ሲሄድ ... አገኘችውና ... ጋቢውን ይዛ "ቆይ ጠብቀኝ! ... ቆይ ጠብቀኝ" እያለች ታስቆመዋለች።

"ይኸው ስጦታህ! እንደው እንዲያው እግዚሐር ይስጥህ - ስለሰጠኸኝ ... እግዚአብሔር ይስጥህ! ይኸው ስጦታዬን ይዤልህ መጥቼያለሁ። ስለትህ ነው" ትለዋለች። ሰውየው ድንግጥ ይልና ግራ ይገበዋል። "ምንድነው?" ሲላት፥ ይህ አሁን የነገርኳችሁን ትነግረዋለች። ወዲያው ስንጥቅ ብሎ፥ ወደ ልቡ ተመልሶ፥ ጋቢውን ጣል ያደርግና ... ልብ ገዝቶ ... ተመልሶ ሄዶ ... ወንድሙ እግር ላይ ዘፍ ብሎ ... ይቅርታ ጠየቀው።

አያችሁ? ሰው ግብሩ የሰይጣን ቢሆንም መጠሪያ ስሙን ግን ማንም አምኖ መቀበል አይፈልግም።

ሴትየዋ አሁንም ድረስ ጋቢውን የሚቀበላት አጥታ ይዛው ትዞራለች አሉ። እዚህ ለማን ትስጠው? እዚህ የሚቀበላት አለ? ማን አለ? ምን በወጣችሁ? ምን በወጣችሁ?

#እረኛዬ
#እማማ ቸርነት
#ቅድስት ይልማ
#አዜብ ወርቁ
#ቤዛ ኀይሉ
811 viewsBiniyam Abura, 03:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 06:44:15
ሱሪያሊቱ ሰዓሊ ሳልቫዶር ዳሊ "የሴትን ልጅ ውበት ከአበባ ጋር ያመሳሰለው የመጀመሪያው ሰው - ፈላስፋ ነው፡፡ የደገመው ግን ደደብ ነው" ይላል፡፡ አልበርት ካሙም በካሊጉላ አንደበት "አያትህን መብለጥ ካልቻልክ አስቀድሞውኑ ሞተህ መቀበር ነበረብህ" የሚል ግልምጫ ሰንዝሯል፡፡

#ከባዶ ላይ መዝገን
#ያዕቆብ ብርሃኑ

https://t.me/binibook
1.2K viewsBiniyam Abura, edited  03:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-24 07:11:23
#በዚህ አለም ላይ ሁለት አይነት የሰው ዘሮች አሉ። የጨዋ ሰው ዘር እና የባለጌ ሰው ዘር። የትኛውም ማህበረሰብ ሙሉ በሙሉ የጨዋ ሰዎች ወይም ሙሉ ለሙሉ የባለጌ ሰዎች ስብስብ አይደለም። የትኛውም ቡድን ንጹህ ዘር አይደለም። ስለዚህም ከካምፑ ዘሮች የጨዋ ሰው ዘር ይገኛሉ።

#ለምንን ፍለጋ
#Man's search for meaning
#ቪክተር ኢ. ፍራንክል
#ተርጓሚ ቴዎድሮስ አጥላው

https://t.me/binibook
2.0K viewsBiniyam Abura, edited  04:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-21 07:43:53
ቅዠታም አዳሩን
ጨፍጋጋ ውሎዉን
ዝብርቅርቅ ተስፋውን
ደረቅ ትዝታውን...
በይሉኝታ ከፈን እየጠቀለለ
ከጥርሱ ሲጥለው
ተቀባይ ይሻማል ሳቅ እየመሰለው።

#መራራቅ
#በረከት በላይነህ
#የመንፈስ ከፍታ

https://t.me/binibook
2.8K viewsBiniyam Abura, edited  04:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-19 05:56:08
#ህመሙ ነው ያስረጀኝ - ሮፍናን ኑሪ

#ሰው፥ ሰርግ ከቀረበት ሰው ይልቅ ለቅሶ የቀረበትን ነው የሚቀየመው። እኛ ለቅሶ ተበላልተናል። ባለሐገር ማለት ለቅሶ ደራሽ ነው። ሰላም የምናገኘው ለቅሶ ስንዳረስ ነው። ምክንያቱም የጋራ ሐዘን ነው ሀገር የሚፈጥረው። የአንቺ ሐዘን ውስጥ ገብቼ "ውይ በሞትኩ!" ስል ነው - ሀገር የሚፈጥረው። በምሽት፥ ለጎረቤት ጩኸት ሮጠን የምንሄደው ነገ እኛ ጋር ሮጠው እንደሚመጡ እርግጠኛ ስንሆን ነው። ከጀርባው ያለ ምልክት ይኼ ነው። ይኼን ባላስብ ተጠቅልዬ ነው የምተኛው። ጎረቤት ሲጮህ ... "እነ እከሌ ቤት ችግር አለ" ብሎ፥ ያገኘውን ለብሶ፥ ራቁቱን ሮጦ የሚሄደው፥ ለዚህ ነው። አየሽ ባለሐገርነት እንዴት ከባድ እንደሆነ። እኔ እንኳን በዚህች እድሜ የ80 አመት ሽማግሌ አድርጎኛል - ባለሐገርነት። ህመሙ ነው ያስረጀኝ።

#ሁለገቡ ሙዚቀኛ ሮፍናን ኑሪ፥ በሸገር ኤፍኤም ጣቢያ በሚሰናዳው "የጨዋታ እንግዳ" መርኃግብር ላይ፥ ከጋዜጠኛ መዓዛ ብሩ ጋር ባደረገው ቆይታ፥ የተናገረው ንግግር።

https://t.me/binibook
3.0K viewsBiniyam Abura, edited  02:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-18 09:58:22
አምላኬ ሆይ
በኃይል ስለሆነ እንጂ ...
በፍትህ ቢሆን የምንዳኘው፤
አንተ ነበርክ በፍርድ ቀን
ለፍርድ የምትቀርበው

ዳዊት ጸጋዬ ገጽ - 29

https://t.me/binibook
3.0K viewsBiniyam Abura, edited  06:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-17 21:40:07
#ምርጥዬ ቻነል!

#ሁነት አዲስ (EventAddis) ይሰኛል።

የተለያዩ የኪነጥበብና ኤቨንት መረጃዎችን የሚያገኙበት ኦንላይ ሚዲያ ነው። በቅርቡ በራዲዮ መተላለፍ የሚጀምር የራዲዮ ዝግጅትም ነው።

ገባ ገባ እያላችሁ! (ከታች ባለው ማስፈንጠሪያ እየተፈናጠጣችሁ)

https://t.me/EventAddis1
485 viewsBiniyam Abura, edited  18:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-15 08:57:15
#ይታተማሉ የተባሉቱ የዶ/ር እጓለ ገ/ዮሐንስ ሦስቱ መጻሕፍት ወዴት ገቡ?

"ብፁዓን ንጹሓነ ልብ" በተሰኘው መጽሐፋቸው፥ "የጋሽ እጓለ ሦስት መጻሕፍት ወደፊት ይታተማሉ!" ተብሎ በገጽ 175 ላይ ተቀምጦ ነበር። የመጻሕፍቱ አርእስትም፦

1. ሥነ ምግባር (የጀርመናዊው ፈላስፋ ኢማኑኤል ካንት ስለሞራል ፊሎሶፊ ከጻፋቸው ሦስት መጻሕፍት በአንደኛው ላይ የተመረኮዘ መጽሐፍ)

2. ከተረት ወደ ሕሊና (ስለፍልስፍና መንፈስ ልደትና እድገት በመተንተን ስለሰው መንፈስ የድል ጎዳና በሰፊው እሚያትት መጽሐፍ)

3. ፋውስት (ጀርመናዊው ባለቅኔ ጎተ፥ ለሃምሳ አመታት ደጋግሞ የጻፈው፥ የትራጀዲ ዘውግ ያለው መጽሐፍ)

#እነዚህን የመሳሰሉ መጻሕፍት የውሃ ሽታ ሆነው መቅረታቸው ያሳዝነኛል። ኧረ የጋሽ እጓለን ድካም፥ የህትመትን ብርሃን እንዲመለከቱ በማድረግ፥ መጻሕፍቱ ለትውልድ እንዲደርሱ እንረባረብ።

#የከፍተኛ ትምህርት ዘይቤን በድጋሚ እንዲታተም ያደረጋችሁት በሞላ፥ ገለታ ይግባችሁ። በነካ እጃችሁ፥ ሦስቱንም መጻሕፍታቸውን የህትመት ብርሃን እንዲያገኛቸው ታትሩ። ስለንባብ አምላክ!

https://t.me/binibook
3.9K viewsBiniyam Abura, edited  05:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-13 09:34:47
#የጋዜጠኝነት ትምህርት ካልተማርኩ እያላችሁ ለምትጨቀጭቁኝ ሁላ፥ ንዝንዛችሁ የእውነት መሆኑን አለመሆኑን የምናረጋግጥበት ጊዜው መጥቷል። ከ30 ጊዜ በላይ አሰልጥኖ ያስመረቀው ኢካሽ የጋዜጠኝነት የስልጠና ማእከል አዲስ ምዝገባ ጀምሯል።

#ምስሉ ላይ ባለው ስልክ ይደውሉ! ይመዝገቡ! ይማሩ! ይገዝጡ(ጋዜጠኛ ይሁኑ)

#ዳይ ወደ JoCo

+251911063349
የቴሌግራም ቻናል ከፈለጉ @litjournalism
535 viewsBiniyam Abura, edited  06:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-12 15:07:01
BlueDelivery
https://www.blueridy.com/
በጣም በአጭር ግዜ ውስጥ ከ600 በላይ ምግብ ቤቶችና ካፌዎች ተመዝግብዋል፡፡

ይፍጠኑ ይመዝገቡ ለደንበኛዎ የደልቨሪ አግልግሎት ለመስጠት ለ2 ወር በነጻ አግልግሎት እንሰጣለን

Addis Abeba +251 91 661 0667
Adama +251 91 381 8893
Hawassa +251 91 078 0208
Shashemene +251 91 078 0208
Dire Dawa +251 91 504 3603

እርሶ ብቻ ይደውሉ በለሙያዎቻችን ባሉብት ድረስ ይመጣሉ

configration and Installation Included
Online Registration for Store: https://www.blueridy.com/store/apply
491 viewsBiniyam Abura, 12:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ