Get Mystery Box with random crypto!

ቢኒ የመጻሕፍት ግብዣ

የቴሌግራም ቻናል አርማ binibook — ቢኒ የመጻሕፍት ግብዣ
የቴሌግራም ቻናል አርማ binibook — ቢኒ የመጻሕፍት ግብዣ
የሰርጥ አድራሻ: @binibook
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.36K
የሰርጥ መግለጫ

👉 ሰሞነኛ ትኩስ መፅሐፍት ከነድስቱ እንገጮታለን።
👉 ዘርፈ ብዙ የሆነውን የኪነት ወሬ እስከነቃጭሉ ዱብ እናረጋለን።
👉 ነባርና አዳዲስ መፅሐፍትን መጠነኛ ዳሰሳ አድርገን እንጠቁሞታለን።
✴ ወሬ ጥሩ ስለሆነ በዚህ ቦይ ላኩልኝማ @a3b2ysm

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-08-12 05:52:31
#ካነበብኳቸው የህይወት ታሪክ መጻሕፍት ... #የኔ ምርጥ 10

#ትዝታዬ ስለራሴ የማስታውሰው - መርስዔ ኀዘን ወልደ ቂርቆስ

#ጣልቃ እየገባ - በቀለ ወልደ ኪዳን

#ደማሙ ብዕረኛ - መንግስቱ ለማ

#ኦቶባዮግራፊ (የሕይወቴ ታሪክ) - ፊታውራሪ ተክለ ሐዋርያት ተክለ ማርያም

#ማስታወሻ (የጋሽ ስብሐት ገ/እግዚአብሔር የህይወት ታሪክ) - ዘነበ ወላ

#መጽሐፈ ትዝታ ዘአለቃ ለማ (የአለቃ ለማ ኃይሉ ታሪክ) - መንግስቱ ለማ

#ሕይወቴ - ተመስገን ገብሬ

#በዓሉ ግርማ ሕይወቱና ሥራዎቹ - እንዳለጌታ ከበደ

#ኦደሲ (በዲፕሬሽን ሸለቆ ...) - ኀይል ከበደ

#ከደንቢያ ጎንደር እስከ ዋሽንግተን ዲሲ - አስማማው ኃይሉ

የእናንተስ?

ማስታወሻ፦
1. በአማርኛ ከተጻፉቱ፥ ትርጉም ካልሆኑቱ፥ በሀገራችን ሰዎች ከተጻፉቱ - ነው።
2. የተቀመጡበት ቅድም-ተከተል የሰጠዋቸውን ደረጃ አይገልጽም።

3. ይሄ ሁሉ ማስታወሻ መደርደር ምን ማለት ነው? ... hahahaha ... መልካም ንባብ!

https://t.me/binibook
3.8K viewsBiniyam Abura, edited  02:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-10 07:21:42
#ፍቅሬን ሜዳ ላይ ጥላ ስትከዳኝ አይቻታለሁ
እንደገፋችኝ ትገፋ እያልኩ እረግማታለሁ።

ዘወትር ሙሾ ታላዝን የዕንባ ማዕበል ይጠባት
ደስታዬን እንዳጨለመች ደስታዋ ይጨልምባት
ሺህ እጥፍ ትጨድ አበሳ ለዘራችብኝ ጥፋት።

እያልኩ እረግማታለሁ።

የኮራችበትን ገላ መብረቅ ያንድደው በቁጣ
በላይዋ ዲን ይውረድባት ጥጋት መሸሻ ትጣ።

እያልኩ እረግማታለሁ።

የምድር የቀላይ ጥፋት በላይዋ ይውረድ ኩነኔ
ኑሮዋን ሲዖል ያድርገው ስቃይዋን ያሳየኝ በዓይኔ።
እንደከዳችኝ ትከዳ የኔ ያለችው ይሽሻት
ቀላዋጭ ዓይኗን ያፍርጠው ከውካዋ እግሯን ያልምሻት።

እያልኩ እረግማታለሁ ።

ክንዷ በመጅ ይሰበር ሌላ ያቀፈችበት
አባጨጓሬ ይሙላው ፍራሹ የተኛችበት።

እያልኩ እረግማታለሁ።

የሌላ ሆና ብትከዳኝ አይጠሉ ጠልቻታለሁ
ስለማተቤ ብጠየቅበዓለም ላይ ካለ የምሻው
የረገምኳትን እላለሁ
ሌላም እርካታ የለኝ እሷን አምጡልኝ እላለሁ።

ጥላቻዬና ፍቅሬ ናት እርግማኔና በረከቴ
ያለሷ ሕይወት የሌለኝ ያሳበደችኝ ቅናቴ ።

#አበባው መላኩ
#ቅናት
#እኔ ነኝ

https://t.me/binibook
3.8K viewsBiniyam Abura, edited  04:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-08 05:24:08
#ማነው "ምንትስ"?

... ኧረ ስንቱ፥ ሞልቶ ስንቱ፥ ብኩን የመንፈስ ምንትስ
ለስጋውም አብሮን ወድቆ፥ ዳግም በአእምሮው ሲረክስ
በልቦናውም ሲሴስን፥ በህሊናው ህግ ሲድስ
'ፍሪ-ደሜ' ነው እያለ፥ የኔኑ ደም ሲያልከሰክስ
በቃሉና በመንፈሱ፥ ወድቆ ደቅቆ ሲበሰብስ
ቴህ ወዲያ ማነው ምንትስ! ...

#ሎሬት ጸጋዬ ገ/መድኅን
#እሳት ወይ አበባ
#ማነው "ምንትስ"?

https://t.me/binibook
3.8K viewsBiniyam Abura, edited  02:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-06 05:28:22
#የቻይናውያን ውርደት ኮንፊሽየስንና ላዎቱዙን፥ የሩሲያውያን ስቃይ ፑሽኪንን እና ዶስቶቭስኪን፥ የዳቶች ሰቆቃ ቫን ግን፥ የህንዶች እና የደቡብ አፍሪካውያን ዋይታ ጋንዲንና ማንዴላን፥ የጥቁር አሜሪካውያንን ሕመም የጃዝ ሙዚቃን ሲወልድ፥ ምነው የሃበሻ ርሃብና ድህነት፥ ውርደትና ሃፍረት እንዲሁ መከነ?"

#ኬክሮስና ኬንትሮስ
#በስንቅነህ እሸቱ
#ኦታም ፑልቶ

https://t.me/binibook
4.5K viewsBiniyam Abura, edited  02:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-04 06:22:53
#ለብ ባለ ውሃ፥ ገላውን ለመታጠብ ገንዳ የሚሞላ ሰው፥ ገንዳው ውስጥ ዘሎ ከመግባቱ በፊት፥ የውሃውን ሙቀት እጁን ወይም ክንዱን እያስገባ ይለካል። ደርግም ንጉሱን አውርዶ ስልጣን በእጁ እስካስገባበት - እስከ መስከረም 2፣ 1967 ዓ.ም ያደረገው ነገር፥ የገላ ታጣቢውን ምሳሌ የሚመስል ነው። ከነገሌው የወታደሮች አመጽ ጀምሮ፥ ከታህሳስ 1966 ዓ.ም እስከ መስከረም 2፣ 1967 ዓ.ም ድረስ የነበረው ጊዜ፥ ለወታደሮቹ የውሃውን ሙቀት የመሞከሪያ ጊዜ ነበር። ወታደሮቹ "ዘሎ ስልጣን መያዝ የሚፋጅ ነገር ሊሆን ይችላል" የሚል ትልቅ ስጋት ነበራቸው።

#ገጽ 420
#ትውልድ አይደናገር እኛም እንናገር
#አንዳርጋቸው ፅጌ

https://t.me/binibook
3.7K viewsBiniyam Abura, edited  03:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-01 05:54:20
ሀገር ጦም ያደረ ማሳ
አስከባሪ አራሽ የናፈቀው፤
በግለኝነት አረም ተተብትቦ
የበደል አሽክታ ሲውጠው
ጭካኔ ያፈራው ግፍ፤
ሞት ሲያረግፍ፤
"አበስኩ" ብቻ፣ "እንትፍ" "እንትፍ!"
ከ"እንትፍ" ምን ሊተርፍ?!
ሬሳ እየከመረ ሞት ቤተኛ አደረገን
ሬሳው በዝቶ ሞትን ከለከለው፤
ኧረ አንድ ባዩ አንድ በለው!
ሀገር ያበቀለው ግፍ፤
ጭካኔ አንቡጦ ሞት ሲያረግፍ፣
አበስኩ! እንትፍ! እንትፍ
ከ "እንትፍ" ምን ሊተርፍ

#የወይራ ስር ጸሎት
#በድሉ ዋቅጅራ(ዶ/ር)

https://t.me/binibook
4.7K viewsBiniyam Abura, edited  02:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-29 08:44:22
ለብቻ የመቆም ማሳያ፥ ከግርሻውያን ኀልዮት የማፈንገጫ፤ የእውነት አምድ፥ የጽናት ጉልላት ... አቡነ ጴጥሮስ።

ጴጥሮስ ያቺን ሰዓት በተሰኘው፥ በሎሬት ጸጋዬ ገ/መድኅን ቲያትር ላይ፥ ግርሻ የተሰኘ የዘመኑን አጎብዳጆች እሚወክል ገጸባህሪ አለ። ለጥልያን እጅ እንስጥ እሚልበት አመክንዮ የዋዛ እሚባል አይደለም። ለአቡነ ጴጥሮስ የኢትዮጵያን ፍጹም ሞት እሚያትትበት መንገድ አጀብ ነው። በቃላት አሽሞንሙኖ የኢትዮጵያን ሞት ያረዳቸዋል። አቡነ ጴጥሮስ ኢትዮጵያን ከድተው በፋሽስት እንዲጠመቁ ሲያብል። አቡኑም እንዲህ ይሉታል፦ "እኔ በኢትዮጵያ ስለማምን፥ እኔ እስካመንኩ እሷ አትሞትም።"

https://t.me/binibook
4.8K viewsBiniyam Abura, edited  05:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-28 06:42:04
#የእኛን መሬት ያህል ጠፍ መሬት እያለ እስትንፋሳቸውን አዝለው ማርስ ላይ ይኖሩ ይመስሏችኋል? አትሳሳቱ እነዚህ አድላቢዎች የሚጠብቁት ነብያቸውን ዳግማዊ ጆርጅ ዋሽንግተንን ነው። እኛም ከእንቅልፍ መበርከት የምናልቅ ቀይ ህንዶች ነን።

#የተጠላው እንዳልተጠላ
#አለማየሁ ገላጋይ

https://t.me/binibook
4.5K viewsBiniyam Abura, edited  03:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-26 10:29:31
የአውሮፓ እስታንዳርድ የሆኑ፥ ኳሊቲ እና ለየት ያሉ የቦንዳ ልብሶችን፥ ቦርሳዎችን እና ጫማዋች በታላቅ ቅናሽ

● ለሴት ለወንድ ለሕፃናት የሚሆኑ ልብሶችና ጫማዎች አሉን

አዳዲስ እቃዎች ዘወትር ሰኞ ይገባሉ

#አድራሻ

22 አውራሪስ ሆቴል ገባ ብሎ festival ሕንፃ 2ኛ ፎቅ

0921809843

ከሰኞ -እሁድ ከጠዋት 2:30 - ማታ 1:30 ሱቃችን ክፍት ነው


https://t.me/yawimelaku

@yawimelaku
733 viewsBiniyam Abura, edited  07:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-25 06:04:41
#ሌሊሳ ግርማ

የቀኗ አዲስ አበባ ሁሌ ለነገ የምትዘጋጅ ከተማ ናት። ነገ ለማማር ዛሬ ጸጉሯን ተተኩሳ በቢጎዲን ጠቅልላ፣ ፊቷን ምናምን ለቅልቃ ተኝታለች። ለነገ ውበቷ ስታስብ ዛሬ በነጻነት ሊነካት ለፈለገው ባሏ እንደማትመቸው ሚስት። አዲሳባ ሁሌ ለነገ ነው የምትዘጋጀው።

የምሽቷ አዲስ አበባ ደግሞ ከቆሻሻ የጥበብ ቀሚሷ ስር የፈረንጅ ውስጥ ልብሷ የረዘመባት ባለንቅሳቷን ሴት ትመስላለች። ጸጉሯን ግማሹን ተተኩሳ ግማሹን ሹሩባ የተሰራች።

አፍሮጋዳ ገጽ 59

https://t.me/binibook
4.4K viewsBiniyam Abura, edited  03:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ