Get Mystery Box with random crypto!

ሀገር ጦም ያደረ ማሳ አስከባሪ አራሽ የናፈቀው፤ በግለኝነት አረም ተተብትቦ የበደል አሽክታ ሲውጠ | ቢኒ የመጻሕፍት ግብዣ

ሀገር ጦም ያደረ ማሳ
አስከባሪ አራሽ የናፈቀው፤
በግለኝነት አረም ተተብትቦ
የበደል አሽክታ ሲውጠው
ጭካኔ ያፈራው ግፍ፤
ሞት ሲያረግፍ፤
"አበስኩ" ብቻ፣ "እንትፍ" "እንትፍ!"
ከ"እንትፍ" ምን ሊተርፍ?!
ሬሳ እየከመረ ሞት ቤተኛ አደረገን
ሬሳው በዝቶ ሞትን ከለከለው፤
ኧረ አንድ ባዩ አንድ በለው!
ሀገር ያበቀለው ግፍ፤
ጭካኔ አንቡጦ ሞት ሲያረግፍ፣
አበስኩ! እንትፍ! እንትፍ
ከ "እንትፍ" ምን ሊተርፍ

#የወይራ ስር ጸሎት
#በድሉ ዋቅጅራ(ዶ/ር)

https://t.me/binibook