Get Mystery Box with random crypto!

ለብቻ የመቆም ማሳያ፥ ከግርሻውያን ኀልዮት የማፈንገጫ፤ የእውነት አምድ፥ የጽናት ጉልላት ... አቡ | ቢኒ የመጻሕፍት ግብዣ

ለብቻ የመቆም ማሳያ፥ ከግርሻውያን ኀልዮት የማፈንገጫ፤ የእውነት አምድ፥ የጽናት ጉልላት ... አቡነ ጴጥሮስ።

ጴጥሮስ ያቺን ሰዓት በተሰኘው፥ በሎሬት ጸጋዬ ገ/መድኅን ቲያትር ላይ፥ ግርሻ የተሰኘ የዘመኑን አጎብዳጆች እሚወክል ገጸባህሪ አለ። ለጥልያን እጅ እንስጥ እሚልበት አመክንዮ የዋዛ እሚባል አይደለም። ለአቡነ ጴጥሮስ የኢትዮጵያን ፍጹም ሞት እሚያትትበት መንገድ አጀብ ነው። በቃላት አሽሞንሙኖ የኢትዮጵያን ሞት ያረዳቸዋል። አቡነ ጴጥሮስ ኢትዮጵያን ከድተው በፋሽስት እንዲጠመቁ ሲያብል። አቡኑም እንዲህ ይሉታል፦ "እኔ በኢትዮጵያ ስለማምን፥ እኔ እስካመንኩ እሷ አትሞትም።"

https://t.me/binibook