Get Mystery Box with random crypto!

#ፍቅሬን ሜዳ ላይ ጥላ ስትከዳኝ አይቻታለሁ እንደገፋችኝ ትገፋ እያልኩ እረግማታለሁ። ዘወትር ሙሾ | ቢኒ የመጻሕፍት ግብዣ

#ፍቅሬን ሜዳ ላይ ጥላ ስትከዳኝ አይቻታለሁ
እንደገፋችኝ ትገፋ እያልኩ እረግማታለሁ።

ዘወትር ሙሾ ታላዝን የዕንባ ማዕበል ይጠባት
ደስታዬን እንዳጨለመች ደስታዋ ይጨልምባት
ሺህ እጥፍ ትጨድ አበሳ ለዘራችብኝ ጥፋት።

እያልኩ እረግማታለሁ።

የኮራችበትን ገላ መብረቅ ያንድደው በቁጣ
በላይዋ ዲን ይውረድባት ጥጋት መሸሻ ትጣ።

እያልኩ እረግማታለሁ።

የምድር የቀላይ ጥፋት በላይዋ ይውረድ ኩነኔ
ኑሮዋን ሲዖል ያድርገው ስቃይዋን ያሳየኝ በዓይኔ።
እንደከዳችኝ ትከዳ የኔ ያለችው ይሽሻት
ቀላዋጭ ዓይኗን ያፍርጠው ከውካዋ እግሯን ያልምሻት።

እያልኩ እረግማታለሁ ።

ክንዷ በመጅ ይሰበር ሌላ ያቀፈችበት
አባጨጓሬ ይሙላው ፍራሹ የተኛችበት።

እያልኩ እረግማታለሁ።

የሌላ ሆና ብትከዳኝ አይጠሉ ጠልቻታለሁ
ስለማተቤ ብጠየቅበዓለም ላይ ካለ የምሻው
የረገምኳትን እላለሁ
ሌላም እርካታ የለኝ እሷን አምጡልኝ እላለሁ።

ጥላቻዬና ፍቅሬ ናት እርግማኔና በረከቴ
ያለሷ ሕይወት የሌለኝ ያሳበደችኝ ቅናቴ ።

#አበባው መላኩ
#ቅናት
#እኔ ነኝ

https://t.me/binibook