Get Mystery Box with random crypto!

#ህመሙ ነው ያስረጀኝ - ሮፍናን ኑሪ #ሰው፥ ሰርግ ከቀረበት ሰው ይልቅ ለቅሶ የቀረበትን ነው | ቢኒ የመጻሕፍት ግብዣ

#ህመሙ ነው ያስረጀኝ - ሮፍናን ኑሪ

#ሰው፥ ሰርግ ከቀረበት ሰው ይልቅ ለቅሶ የቀረበትን ነው የሚቀየመው። እኛ ለቅሶ ተበላልተናል። ባለሐገር ማለት ለቅሶ ደራሽ ነው። ሰላም የምናገኘው ለቅሶ ስንዳረስ ነው። ምክንያቱም የጋራ ሐዘን ነው ሀገር የሚፈጥረው። የአንቺ ሐዘን ውስጥ ገብቼ "ውይ በሞትኩ!" ስል ነው - ሀገር የሚፈጥረው። በምሽት፥ ለጎረቤት ጩኸት ሮጠን የምንሄደው ነገ እኛ ጋር ሮጠው እንደሚመጡ እርግጠኛ ስንሆን ነው። ከጀርባው ያለ ምልክት ይኼ ነው። ይኼን ባላስብ ተጠቅልዬ ነው የምተኛው። ጎረቤት ሲጮህ ... "እነ እከሌ ቤት ችግር አለ" ብሎ፥ ያገኘውን ለብሶ፥ ራቁቱን ሮጦ የሚሄደው፥ ለዚህ ነው። አየሽ ባለሐገርነት እንዴት ከባድ እንደሆነ። እኔ እንኳን በዚህች እድሜ የ80 አመት ሽማግሌ አድርጎኛል - ባለሐገርነት። ህመሙ ነው ያስረጀኝ።

#ሁለገቡ ሙዚቀኛ ሮፍናን ኑሪ፥ በሸገር ኤፍኤም ጣቢያ በሚሰናዳው "የጨዋታ እንግዳ" መርኃግብር ላይ፥ ከጋዜጠኛ መዓዛ ብሩ ጋር ባደረገው ቆይታ፥ የተናገረው ንግግር።

https://t.me/binibook