Get Mystery Box with random crypto!

ትምህርት ሚኒሰትር መረጃዎች

የቴሌግራም ቻናል አርማ mereja_neaea — ትምህርት ሚኒሰትር መረጃዎች
የቴሌግራም ቻናል አርማ mereja_neaea — ትምህርት ሚኒሰትር መረጃዎች
የሰርጥ አድራሻ: @mereja_neaea
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 3.23K
የሰርጥ መግለጫ

Students Info

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-26 11:09:44 የ8ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ።

የደቡብ ክልል እና የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የ8ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ይፋ መሆኑ ዛሬ ተገልጿል።

በሁለቱ ክልሎች ውሳኔ መሰረት የማለፊያ ነጥብ ፦

ለወንዶች 41፣
ለሴቶች 40 እና
ለአይነ ስውራን 39 ሆኖ ተወስኗል።

በዚህ መሰረት ፦ በ2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በሁለቱም ክልሎች ለፈተና ከተቀመጡ ከ257 ሺህ በላይ ተማሪዎች 187 ሺህ 500 በላይ ተማሪዎች ወደቀጣይ ክፍል የሚያሳልፋቸውን ውጤት አምጥተዋል።

ለፈተና ከተቀመጠው አጠቃላይ ተማሪ ቁጥር ሲታይ ከ73 በመቶ በላይ ተማሪዎች አልፈዋል።

በተለየ መልኩ ከጸጥታ ጋር በተያያዘ በአሉታዊ ጫና ውስጥ ሆነው የተማሩና ለፈተና የተቀመጡ የደራሼ ልዩ ወረዳ ተማሪዎችን ውጤት በተለየ መልኩ ታይቷታ።

በዚህም መሰረት ፦

ለወንዶች 39፣
ለሴቶች 38 እና
ለአይነ ስውራን 37 ሆኖ ተወስኗል።

የሁለቱ ክልሎች ተማሪዎች ውጤታቸውን ከነገ ጀምሮ መውሰድ ይችላሉ ተብሏል።

የደራሼ ልዩ ወረዳ ተማሪዎች ግን ውጤታቸው በእጅ የሚሰራ በመሆኑ የ1 ሳምንት ጊዜ ዘግይቶ ይደርሳል እስከዛው በትዕግስት እንዲጠባበቁ መልዕክት ተላልፏል።

@MEREJA_NEAEA
#SHARE
461 viewsEYU, 08:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-23 19:12:09 ትምህርት ሚኒሰትር መረጃዎች pinned «#JigjigaUniversity በ2014 ዓ.ም በጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ በመጀመሪያ ዲግሪ አዲስ የተመደባችሁ መደበኛ ተማሪዎች መግቢያ ከግንቦት 01 እስከ 03/2014 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል። ወደ ተቋሙ ስትሄዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦ • ከ8ኛ እስከ 12ኛ ክፍል የትምህርት ማስረጃዎች ዋናውና ኮፒው • ጉርድ ፎቶግራፍ (8) • ብርድልብስ፣ አንሶላ፣ የትራስ ልብስ • የስፖርት ትጥቅ ለተጨማሪ…»
16:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-06 12:14:54 #JigjigaUniversity

በ2014 ዓ.ም በጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ በመጀመሪያ ዲግሪ አዲስ የተመደባችሁ መደበኛ ተማሪዎች መግቢያ ከግንቦት 01 እስከ 03/2014 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ወደ ተቋሙ ስትሄዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

• ከ8ኛ እስከ 12ኛ ክፍል የትምህርት ማስረጃዎች ዋናውና ኮፒው
• ጉርድ ፎቶግራፍ (8)
• ብርድልብስ፣ አንሶላ፣ የትራስ ልብስ
• የስፖርት ትጥቅ

ለተጨማሪ መረጃ የዩኒቨርሲቲውን ድረ-ገጽ www.regi@jju.edu.et መጎብኘት ትችላላችሁ፡፡

@MEREJA_NEAEA
#SHARE
4.2K viewsEYU, 09:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-05 15:52:14 #WachemoUniversity

በ2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ የመጀመሪያ ዲግሪ መደበኛ ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ግንቦት 09 እና 10/2014 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ወደ ተቋሙ ስትሄዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

• የ10ኛ እና 12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው
• ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው
• የ8ኛ ክፍል ሰርተፊኬት
• 3×4 ፎቶግራፍ (8)
• ብርድልብስ፣ አንሶላ፣ የትራስ ልብስ
• የስፖርት ትጥቅ

በ Re-admission እና Withdrawal ወጥታችሁ የነበራችሁ የአንደኛ ዓመት ተማሪዎች ዳግም ቅበላ ግንቦት 11 እና 12/2014 ዓ.ም እንደሚከናወን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

ከተጠቀሱት ቀናት ውጪ የሚመጡ ተማሪዎችን የማያስተናግድ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳስቧል።

@MEREJA_NEAEA
#SHARE
4.0K viewsEYU, 12:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-04 18:46:54 #Update

መግቢያ / ሪፖርት ማድረጊያ ቀናት ፦

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሪፖርት ማድረጊያ ሚያዚያ 24 እና 25/2014 ዓ/ም ፤ በረመዷን በዓል ምክንያት መድረስ ለማይችሉ እስከ አርብ ሚያዚያ 28 /2014 ዓ/ም ድረስ

ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የኦንላይን ምዝገባ ግንቦት 01 እስከ 05/2014 ዓ/ም ፤ ወደ ዩኒቨርሲቲ መግቢያ እና ሪፖርት ማድረጊያ ግንቦት 8 እና 9/2014 ዓ/ም

ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ ግንቦት 08 እና 09/2014 ዓ.ም

ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ሚያዚያ 27 እና 28/2014 ዓ/ም

ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ግንቦት 1 እና 2 /2014 ዓ/ም

መደወላቡ ዩኒቨርሲቲ ግንቦት 01 እና 02/2014 ዓ/ም

ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ሚያዚያ 29 እና 30 /2014 ዓ/ም

ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሚያዚያ 28 እስከ 30 /2014 ዓ/ም

ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ ሚያዚያ 28 እና 29/2014 ዓ/ም

ASTU / AASTU ሚያዚያ 28 እና 29 /2014 ዓ/ም በቅጣት ግንቦት 1 /2014 ዓ/ም

ኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ የመግቢያ ቀን ግንቦት 8 እና 9 ፤ ምዝገባ ግንቦት 10 እና 11

መደወላቡ ዩኒቨርሲቲ የመግቢያ ቀን ግንቦት 01 እና 02 /2014 ዓ/ም

ሐረማያ ዩኒቨርስቲ ግንቦት 12፣ 13 እና 14

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ግንቦት 1 እና 2/2014 ዓ/ም

ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ግንቦት 1 እና 2/2014 ዓ/ም

መቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ግንቦት 10 እና 11 /2014 ዓ/ም

ጅማ ዩኒቨርሲቲ ግንቦት 4 እና 5 /2014 ዓ/ም

ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ግንቦት 4 እና 5 /2014 ዓ/ም

ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ከሚያዚያ 28 እስከ 30/2014 ዓ.ም

ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ግንቦት 3 እና 4 /2014 ዓ/ም

መቱ ዩኒቨርሲቲ ግንቦት 3 እና 4/2014 ዓ/ም

እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ከግንቦት 9 እስከ 11/2014 ዓ/ም

@MEREJA_NEAEA
#SHARE
3.2K viewsEYU, 15:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-04 18:44:41 #DebreMarkosUniversity

በ2014 ዓ.ም የዩንቨርሲቲ መግቢያ ውጤት አስመዝግባቹህ በትምህርት ሚኒስቴር ወደ ደብረማርቆስ ዩኒቨርስቲ የተመደባችሁ አዲስ ገቢ መደበኛ ተማሪዎች ምዝገባ ግንቦት 04 እና 05/2014 ዓ.ም መሆኑን የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ህዝብና ግንኙነትና ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት አሳውቋል።

@MEREJA_NEAEA
#SHARE
2.3K viewsEYU, 15:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-03 14:12:24 #MaddaWalabuUniversity

መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ በ2014 ዓ.ም የተመደባችሁ አዲስ ገቢ መደበኛ ተማሪዎች ምዝገባ ግንቦት 01 እና 02/2014 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል።

ተማሪዎች በተገለጹት ቀናት ብቻ ምዝገባ እንዲያደርጉ ዩኒቨርሲቲው አሳስቧል።

ተማሪዎች ወደ ተቋሙ ሲሄዱ ሊይዟቸው የሚገቡ፦

• የትምህርት ማስረጃዎች
• ጉርድ ፎቶግራፍ (4)
• አንሶላ፣ ብርድ ልብስ እና የትራስ ልብስ
• የስፖርት ትጥቅ
• የኮቪድ-19 መከላከያዎች

ከተጠቀሱት ቀናት ውጪ የሚመጡ ተማሪዎችን የማያስተናግድ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

@MEREJA_NEAEA
#SHARE
2.5K viewsEYU, 11:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-03 08:55:11 #OdabultumUniversity

በ2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ቀን ግንቦት 8 እና 9 ሲሆን ምዝገባ የሚካሄደው ግንቦት 10 እና 11 ይሆናል፡፡

ወደ ዩኒቨርሲቲው በምትመጡበት ጊዜ፡-

፨የ8ኛ ክፍል ሰርትፊኬት ኦርጅናልና ኮፒ

፨የ10ኛ እና 12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ኦርጅናልና ኮፒ

፨ከ9-12ኛ ክፍል የተማራችሁበት ትራንስክሪብት ኦርጅናልና ኮፒ

፨አራት ፓስፖርት ሳይዝ ጉርድ ፎቶ ግራፍ እንዲሁም

፨አንሶላ፣ የስፖርት ትጥቅ፣ የትራስ ጨርቅ እና ብርድ ልብስ በመያዝ በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በምዕራብ ሐረርጌ ዞን ጭሮ ከተማ በሚገኘዉ ዋናዉ ካምፓስ በአካል ቀርባችሁ እንድትመዘገቡ እናሳስባለን፡፡

ማሳሰቢያ፡- ከተጠቀሰው ቀን በፊትም ሆነ በኋላ የሚመጡ ተማሪዎችን የማናስተናግድ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

ለበለጠ መረጃ www.obu.edu.et ወይም https://t.me/OBURegistrar ይጎብኙ

የኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራር ጽ/ቤት

       
@MEREJA_NEAEA
#SHARE
2.2K viewsEYU, 05:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-03 08:54:16 #HawassaUniversity

በ2014 ዓ.ም በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎች ምዝገባ #በኦንላይን ከግንቦት 01 እስከ 05/2014 ዓ.ም ድረስ እንደሚከናወን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

የተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ የመግቢያ እና ሪፖርት ማድረጊያ ጊዜ ግንቦት 08 እና 09/2014 ዓ.ም በዋናው ግቢ እንደሆነ ዩኒቨርሲቲው ገልጿል፡፡

ስለምዝገባ ሂደቱ ዝርዝር መረጃዎች በተቋሙ ድረ-ገጽ https://hu.edu.et እና በዩኒቨርሲቲው የማኅበራዊ ገጾች የሚገለጹ መሆኑ ተገልጿል፡፡


ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲው ሲሄዱ ሊይዟቸው የሚገቡ፦

• የ12ኛ እና የ10ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት
ዋናውና ኮፒው
• ከ9ኛ-12ኛ ክፍል ትራንስክርፕት ዋናውና ኮፒው
• ጉርድ ፎቶግራፍ (4)
• የሌሊት አልባሳት
• የስፖርት ትጥቅ

ትምህርት አቋርጣችሁ ለመልሶ ቅበላ ውጤታችሁ የሚያበቃችሁ ተማሪዎች አዲስ ከተመደቡ አንደኛ ዓመት ተማሪዎች ጋር በመቅረብ በ2014 ዓ.ም የመጀመሪያ ሴሚስተር ለመልሶ ቅበላ ግንቦት 10 እና 11/2014 ዓ.ም እንድታመለክቱ ተብሏል፡፡

ከተጠቀሱት ቀናት ውጪ የሚመጡ ተማሪዎችን የማናስተናግድ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።


@MEREJA_NEAEA
#SHARE
2.0K viewsEYU, 05:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-03 08:53:45 #BoranaUniversity

ቦረና ዩኒቨርሲቲ #የሁለተኛ ዓመት መደበኛ ተማሪዎች ምዝገባ ግንቦት 02 እና 03/2014 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል።

ተማሪዎች በተገለጹት ቀናት ምዝገባ እንዲያደርጉ ዩኒቨርሲቲው አሳስቧል።

የአንደኛ ዓመት አዲስ ገቢ መደበኛ ተማሪዎች ምዝገባ የሚከናወንበት ጊዜ በቅርቡ እንደሚያሳውቅ ተቋሙ ገልጿል።

@MEREJA_NEAEA
#SHARE
1.8K viewsEYU, 05:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ