Get Mystery Box with random crypto!

የደራሲያን ቤት 123@🇪🇹 የድሮ ሙዚቃዎች 📷📸

የቴሌግራም ቻናል አርማ yederasiyanbet — የደራሲያን ቤት 123@🇪🇹 የድሮ ሙዚቃዎች 📷📸
የቴሌግራም ቻናል አርማ yederasiyanbet — የደራሲያን ቤት 123@🇪🇹 የድሮ ሙዚቃዎች 📷📸
የሰርጥ አድራሻ: @yederasiyanbet
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.91K
የሰርጥ መግለጫ

➕ሁሉም ባንድ ላይ ➕
✔የህወት ታሪኮች
✔የፍቅር ገጠመኞች
✔ምክሮች
✔ ግጥሞች
ይገኝበታል⚫

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-10 19:55:43 #Day-285 ጽንአት

(የህይወቴ ገጽ)
“አንድ ሰው የሚያልቅለት ሲሸነፍ አይደለም፤ የሚያልቅለት በበቃኝ ሲያቆም ነው” - Richard M. Nixon

በህይወትህ በአንድ ባመንክበትና ትክክል በሆነ ዓላማ እስከመጨረሻው ከመጽናት ውጪ ምንም ቁም ነገር ልታከናውን አትችልም፡፡ ዛሬ ይህንና ያንን እየጀመርክ እስከጥጉ ሳታደርሳቸው ነገ ደግሞ ወደሌላ ነገር ዘወር የማለት ለማድ ካለህ በተቻለህ ፍጥነት ይህንን ዘይቤ መቀየር እንዳለብህ ትመከራለህ፡፡ አብዛኛውን ጊዜ አንድን የጀመርነውን ነገር እስከጥጉ የማንወስድበት ዋነኛ ምክንያት ስንወድቅ ወይም ያልተሳካልን ሲመስለን ነው፡፡ ሆኖም፣ ውድቀት፣ አለመሳካት፣ እንቅፋትና የመሳሰሉት ሁኔታዎች በማንኛውም አንድን መልካም አላማ ይዞ በሚራመድ ሰው ሕይወት ውስጥ የማይቀሩ ሂደቶች ናቸው፡፡ ስለዚህም፣ አንደኛችንን ውድቀትን አያያዝ ብልሃት ማዳበር አስፈላጊ ነው፡፡

ሲወድቁ መነሳት በጽንአቱ የታወቀ ሰው ለወደቀበት ለእያንዳንዱ ክስተት መነሳትን አስመዝግቦ ወደ ፊት የሚራመድ ሰው ነው፡፡ መሳሳት፣ መውደቅ፣ መክሰር፣ ግብን አለመምታትና የመሳሰሉት ብዙዎችን ኃያላን የጣሉ ሁኔታዎች ለእሱ የእድገት ምክንያቶች እንጂ የተስፋ መቁረጥ ምንጮች አይደሉም፡፡

ውድቀትን እንደ አንድ ብቸኛ ክስተት ማየት
ወድቀው የሚቀሩ ሰዎች ሲወድቁ ውዳቂ ነኝ ብለው የሚያስቡ ሰዎች ናቸው፡፡ በተቃራኒው ስኬታማ ሰዎች አንድ ውድቀት የእነሱን ማንነት እንዲወስን አይፈቅዱም፡፡ ውድቀትን እንደ አንድ ብቸኛ ክስተትና እንደ ትምህርት እድል ነው የሚቆጥሩት፡፡

አደራረግን መቀየር ስኬታማ ሰዎች ነገሮችን በአንድ መልኩ ሞክረው አያቆሙም፡፡ ያልተሳካበትን መንገድ በመተው ሁኔታውን በሌላ መልኩ ይቀርቡታል፡፡ ለማከናወን በአይነ-ህሊናቸው ላዩት ነገር አንዱ መንገድ ካልተሳካ ሌላ መንገድ እንዳለው ጽኑ እምነት አላቸው፡፡

ሃላፊነትን መውሰድ ተሸናፊ ሰዎች ለተከሰተው ስህተት የሚወቀስ ሰው ይፈልጋሉ፡፡ በአንጻሩ ስኬታማ ሰዎች ለሰሩት ስህተት ሃላፊነትን የሚወስዱና የተሻለ መንገድን ለመፈለግ የሚነሱ ሰዎች ናቸው፡፡ አንዱ ሌሎችን በመውቀስ ሲረካና ሲያቆም፣ ሌላኛው ሃላፊነትን በመውሰድ መፍትሄ በማግኘት ይረካል፤ ወደ ፊትም ዘልቆ ይሄዳል፡፡

በውስጥ ላይ ማተኮር አሸናፊ ሰዎች ወሳኙ ነገር በዙሪያቸው የተከናወነው ሳይሆን በውስጣቸው የተከናወነው እንደሆነ ጠንቅቀው ያውቃሉ፡፡ በእነርሱ ዙሪያም ሆነ በእነርሱ ላይ የሆነው ነገር ውስጣቸውን እስካልነካው ድረስ ምንም እንደማይሆኑ ያውቃሉ፡፡ የደረሰባቸው ማንኛውም አስከፊ ሁኔታ በውስጣቸው ያለውን ጽኑ እምነት ካልነካውና ትክክለኛውን ምላሽ መስጠትን ከለመዱ ወደግብ የመድረሳቸው አሸናፊነት ዘላቂነት ይኖረዋል፡፡
2.8K viewsnothing, 16:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 20:17:34
#የህይወት_ወርቃማ_ህጎች_2

#ያለ_ፍርሃት_በአዎንታዊነት_ተንቀሳቀስ
የሆነ ነገር ውስጥ እንደገባህ በተሰማህ ጊዜ ሁሉ… ተረጋጋ፣ አስብ፣ እቅድ አውጣና ያለ ፍርሃት በአዎንታዊነት ተንቀሳቀስ። የፍርሃት ወጥመድ ውስጥ መቆየትና አሉታዊ ነገሮችን ማሰብ ብቻ መፍትሄ አይሆንም፨ ስለዚህ, በእያንዳንዱ አሉታዊ ሁኔታ ውስጥ አዎንታዊ ጎን መፈለግ ተማር፨

#በረከቶችህን_ቁጠር_መልካም_አድርግ
በውጤቱ ላይ ሳታተኩር መልካም መስራትህን ቀጥል፤ ሁልጊዜም የዘራነውን የምናጭድ በመሆኑ በተቻለ መጠን መልካም ነገሮችን ስራ፨ በተጨማሪም ያለፈው ጊዜ ታሪክ ነው፣ መጪው ጊዜ ምስጢር ነው፣ ዛሬ ደግሞ ስጦታ ነው። ስለዚህ ዛሬ ላይ ትኩረት አድርግ፨

#ፈገግ_ማለትህን_ቀጥል
አንድ ቀላል ፈገግታ የአንድን ሰው መጥፎ ቀን ወደ ጥሩ ቀን ሊለውጠው ይችላል። ስለዚህ፣ ፈገግ ማለትህን ቀጥል ይህም የአንተን ግንዛቤ ይለውጣል፨

#ሲያስፈልግ_ብቻ_ይቅርታ_ጠይቅ
አሁን አሁን <ይቅርታ> እና <አዝናለሁ> የሚሉት ቃላት በሚጠቀሙባቸው በአብዛኛው ሰዎች ከቃላት ባለፈ ብዙም ትርጉም የላቸውም፨ ይቅርታ መጠየቅ መልካም ቢሆንም፥ ከመጠን በላይ ይቅርታ መጠየቅ ግን ሰዎች የሚፈለገውን አክብሮት እንዳይሰጡህ ያደርጋል፨ ስለዚህ ይቅርታ ስትጠይቅ አስፈላጊ በሚሆንበት ጊዜ ብቻ ይሁን።

#ወርቃማ_ሕጎች መጽሐፍ
1.2K viewsnothing, 17:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-01 21:06:35
እንዴት አመሻችሁ

የአንድ ጎልማሳ ጤነኛ ሰው አዕምሮ በአማካኝ 2.5 ሚሊዮን ጌጋ ባይት ፋይል መያዝ የሚያስችል አቅም እንዳለው ጥናቶች ያሳያሉ።

የሰው ልጅ ይህን አዕምሮውን ስርዓት ባለው ትምህርት በመታገዝ ተሸቀዳድሞ በመልካም እውቀትና ጥበብ ካልሞላ እንደ ተንኮል፣ ቅናት፣ ጥላቻ፣ ግድየለሽነት፣ ዘረኝነት፣ ምቀኝነት፣ ስግብግብነት፣ አድርባይነት በመሳሰሉ የሕይወት ቫይረሶች የመሞላት እድሉ ከፍተኛ ይሆናል።

#ከሰርድዮን መጽሐፍ ተወስዶ በሄቨን ሲሳይ ገጽ ላይ የተፖሰተ።

ሰናይ ምሽት
#ሉባር እና #ሰርድዮን መጽሐፍ በገበያ ላይ ውለዋል።

@yederasiyanbet
2.2K viewsnothing, 18:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-14 17:22:09 ፈላስፋዎቹ ኖረው ካዩት ስለ(Life)ሕይወት?

ዶስቶየቭስኪ፡ ሲኦል ነው።

ሶቅራጠስ፡ ወረራ ነው።

አርስቶትል፡- አእምሮ ነው።

ኒቼ፡ ጥንካሬ ነው።

ፍሮይድ፡ ሞት ነው።

ማርክስ፡ ሀሳቡ ነው።

ፒካሶ፡ ጥበብ ነው።

ጋንዲ፡- ፍቅር ነው።

ሾፐንሃወር፡ መከራ ነው።

ራስል፡ ውድድር ነው።

ስቲቭ ጆብስ፡- እምነት ነው።

አንስታይን፡- እውቀት ነው።

ስቴፈን ሆፕኪንስ፡ ተስፋ ነው።

ካፍካ፡ መጨረሻው ነው።

እና ፣ ህይወት ለአንተ ምንድን ነው?

@yederasiyanbet
6.1K viewslife, 14:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-12 19:39:17 ልጩህበት !

#ክፍል_አስራ_አምስት


ቴሌግራምህን ክፈት ሶስት መልእክቶች አሉህ በድምፅ! በፅሁፍና; በምስል! ቻው !!"ብቻ ብሎኝ ስልኩን ዘጋው•••
በፍጥነት ቴሌግራም አካውንቴን ስበረግደው ቀድሞ የታየኝ የመሲ ልብስ አልባ ገላ የሚያሳየው ቪድዮ ነበር ከስር የመሲን ስልክ ቁጥር አስቀምጦ
"አቢቲ በዚህ ቁጥሯ የተከፈተ ቴሌግራም አካውንቷ ላይ ቪድዮዋን ልከህ ካሁን ቡኋላ በሴት ተማሪዎች ህይወት መነገዷን እንድታቆም ያለ በለዚያ ግን ቪድዮዋን እንደምትለቀው ነግረህ አስጠንቅቃት!" ይላል በርግጌ ከፍራሼ ላይ ተነሳሁ።
ቪድዮውን ስከፍተው •••
የሶስት ደቂቃ እድሜ ሲኖረው በዚች ሶስት ደቂቃ ውስጥ መሲ ያልተቀረፀ የሰውነት እካሏ አልነበረም ስካሯ ከመጠን ያለፈ ነበርና ያላትን በሙሉ እያደረገች ትስቃለች ። የሚገርመው የሰውየው አንዲት ጣት እንኳን በትይንቱ ውስጥ አለመኖሯ ነው።
ተጫወተባት እናቴ ትሙት በደንብ አርጎ ነው የተጫወተባት አልኩኝ ጮክ ብዬ መጮሄ ሳይታወቀኝ።
ለኔ በአለም ደስ የሚሉ ግን ያልተፃፉ ህግ አስከባሪም ፍርድቤትም ዳኛም ሳያስፈልጋቸው ከሚተገበሩ ተፈጥሮአዊ ህጎች አንዱ
"ሁሉም የእጁን ያገኛል "የሚለው የውስጤ እምነት ነው ማንም ቢሆን በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ የዘራውን ማጨዱ የማይቀር ነው
ይዘግይም ይፍጠን፡ ይነስም ይብዛ ቅጣቱን መቀበሉ የማይቀር ነው
ስንቶቹን በክፋቷ አሳልፋ እንዳልሰጠቻቸው እሷን ከክፉ የሚጠብቃት ከሷ በብዙ ክንድ ራቀና አጋለጣት በክፋታችን ያራቅነውን የላይኛውን ጠባቂ የትኛውም የምድር ሀይል ሊተካው አይችልምና አብሯት የነበረው የሰፈራችን ሰውዬም አስረክቧት ፈረጠጠ።
ቪድዮውን ዘጋሁትና የድምፅ ቅጂ መልእክትን ከፈትኩት።
የድምፅ ቅጂው በሁለት ሰዎች መካከል የተደረገን ምልልስ ይዟል ።
የት እንደገባ እስካሁን ያልተመለሰልኝን ያንን ሽንት ቤት ድረስ ሄጄ የፈለኩት ሰውዬ ተከትሎት ሄዶ ሲያናግረው ይጀምራል•••
በቅጂው የመጀመሪያ አስር ሰከንዶች የኮቴ እና በጭፈራ ቤቱ በዛች ቅፅበት ሲዘፍን የነበረው የ ቦብ ማርሊ ዘፈን በስሱ ይሰማል ።
ልክ አስራ አንደኛው ሰከንድ ላይ •••
"ጤና ይስጥልኝ ?
ጤና ይስጥልኝ ምን ነበር እንተዋወቃለን ወንድም?
እኔ እንጃ እንተዋወቃለን መሰለኝ እንካ እስቲ እሄን ተመልከት!
ምንድን ነው እሱ ?
አይታይህም እንዴ መታወቂያ ነዋ !
ያ የሰፈራችን ሰው መታወቂያውን ካየ በኋላ መሰለኝ ድምፅ ተቀየረ።
ታድያ ም-ም-ም-ም-ም-ምን ልታዘዝ ጌታዬ? በርግጥ አላወኮትም ወይ ያጠፋሁት ነገር ይኖር ይሆን ?
ያጠፋሁት ነገር ይኖር ይሆን ትላለህ እንዴ ደሞ?
ለነገሩ ላንተም ለብዙዎቹም ለህግም ጥፋት መስሎ የማይታይ ጥፋት ስለሆነ አይታወቅህም
ማለት? እንዴት? መቼ? ምን አድርጌ ? የኔ ጌታ እስቲ ና አረፍ በልና ልጋብዝህ እየጠጣን እናውራ!
ህሊናቸውን በብራቸው ቁልል አፍነው የትውልድን አእምሮ የሚያቀንጭር ስራ ላይ ከተሰማሩ ከብቶች መሀል አንዱ ነህና ሰውን ሁሉ በብር በግብዣ ከመግዛት የሚሻገር አስተሳሰብ የለህም እንኳን እኔን ልትጋብዘኝ ከዚች ሰከንድ ጀምሮ አብረሀት ያለችውን አንድ ፍሬ ልጅ ደግመህ ሳታያት እዚሁ ቆሜ እያየሁህ በጓሮ በር ሹልክ ብለህ ጥፋ! ያለበለዚያ •••
ኧረ እሺ እሺ ጌታዬ እሄዳለሁ ግን የጓሮ በር ያለው አይመስለኝም ቤቱ!
በዛጋ ወደ ሽንት ቤቱ መጊቢያ በስተቀኝ በኩል ባለችው ቀጭን መንገድ ወደ ውስጥ ትንሽ ሄደህ ደረጃውን ቁልቁል ስትወርድ በር ታገኛለህ
እሺ ጌታዬ እሄው ያለብኝ ሂሳብ ነው!
ፍጠን!
እሺ እሄው ሄድኩኮ!"
ሰውየውን በዚህ መልኩ ቆሌውን ገፎ ማባረሩን ሳዳምጥ ከተሰማኝን ደስታ ጋር ግን እሄ ሰውዬ ማን ነው? ለምንድን ነው መታወቂያውን ሲያሳየው እንደዛ ምላሱን የዋጣት ይመስል ንግግሩ ሁሉ የተቆላለፈበት ?የሚለው ጥያቄ ገዝፎ አንቃጨለብኝ!።
ሰውየውን ለግዜው እንቆቅልሽ እንደሆነብኝ ተውኩትና ጆሲን ቀስቅሼ ከማታ ጀምሮ የተፈጠረውን ነገር ነገርኩት።
"ለማንኛውም ቪድዮውን ለመሲ ከመላክህ በፊት አስብበት ማለቴ አረጋጋው !" አለኝ።
ቅዳሜን በጣም እወዳታለሁ በዛ ላይ ዛሬ ከኤዱ ጋር ቀጠሮ አለን።
ከቀኑ ልክ 7:30 ላይ ኤዱ ደወለችና ሰፈር መድረሷንና ያለችበትን ቦታ ነገረችኝ ።
ስትነሺ ደውይልኝ መጥቼ እወስድሻለሁ ብያት ስለነበር ለምን ቀድማ እንዳልደወለችልኝ እየጠየኳት ከቤት ወጣሁና ብር ላይ, ያቆምኳትን ባጃጄን! አስነስቼ ከነፍኩ ።
እነሱ ሳያዩኝ ገና ከሩቁ እንዳየሁዋቸው ደነገጥኩ ግን ምን አስደነገጠኝ ? እኔ እንጃ!
ኤዱ ብቻዋን አልነበረም የመጣችው ሶስት ናቸው ከረድኤት አንድ ባለባበሱ ፍንድትድት ያለ ወጣት ወንድ አብሮአቸው አለ።
ማንም አብሮአቸው ቢኖር ግን ምን አገባኝ ?
ግን ለምን ሶስት ሆነው እንደሚመጡ ቀድማ አልነገረችኝም ?
ግን ማን ነው? እያልኩ መልስ በለላቸው ጥያቄዎቼ እራሴንም ባጃጇንም እያጣደፍኩ አጠገባቸው ደረስኩ።
ከሷ እና ከረድኤት ጋር በመተቃቀፍ ሞቅ ያለ የቅርብ ሰው ሰላምታ ከተለዋወጥን ብሀላ ፈንጠር ብሎ ሞባይሉን የሚነካካውን ልጅ እያመለከተችኝ ዳንዬ ተዋወቀው ባለፈው ከመሲ አስመለጠኝ ያልኩህ የክፍሌ ልጅ ፣ ጓደኛዬ እሱ ነው አለችና ደሞ እሱን
ቴዲዬ ተዋወቁ ምርጥ ወንድሜን " አለችው
ልጥጥ እንዳለ እጁን ዘርፕጋልኝ ጨበጥኩትና ግቡ እንሂድ አልኳቸው።
ባጃጅ ውስጥ ገብተው ወደቤት እየሄድን በመካከላችን ወሬ ጠፋ!።
በኔ በኩል የልጁ ሁኔታ ይሁን ሌላ ባይገባኝም የሆነ ደስ የማይል አዲስ ስሜት ውስጤ ሲላወስ እያዳመጥኩት ነበርና ዝም ማለቴንም አላስተዋልኩትም ነበር ።
እቤት እንደደረስን የውስጤ ስሜት ፊቴ ላይ እንዳይታይ እየታገልኩ ላጫውታቸው ብሞክርም ልጁ እኔ ከረድኤትም ይሁን ከኤዱ አልያም ከሁለቱን ጋር ወሬ ስጀምር እየጠበቀ በማክሸፍ ነበርና የራሱን የሚተኩሰው ሊያስወራኝ አልቻለም።
መናደድ ጀመርኩ። ልጁ እኔ ብቻ ላውራ አድምጡኝ በማለት የሚከተለውን ሙድና የኔን ንዴት በመጠኑም ቡሆን የተረዳችው ኤዱ ጀርባዋን ለሱ ሰጥታ እኔን ለማዋራት ሞከረች።
ከቆይታ በኋላ ካርድ ልግዛ በሚል ሰበብ ወጣ ብሎ ሲመለስ በፊት የነበረበትን ቦታ ትቶ እኔና ኤዱ መሀል ገብቶ ሲቀመጥ ንዴቴን መመጠንም መቆጣጠርም አቅቶኝ ጠፍቶ ድንገት ሀይል ጨምሮ እንደመጣ መብራት ሁለመናዬ ቦግ •••••

ይቀጥላል...


@yederasiyanbet
5.5K viewsnothing, 16:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-12 19:38:44 ልጩህበት !

#ክፍል_አስራ_አራት

መደነስ እኔ ሰውየው እምጥ ይግባ ስምጥ ሄዶ ካናገረው በኋ ላ ከሽንት ቤት ባለመመለሱ ምን አርጎት ነው የመጣው እያልኩ ግራ ተጋብቻለሁ ጭራሽ ደንስ ይለኛል ምን አይነት ባህሪ ያለው ሰው ነው እሄ ደግሞ ቢያንስ እንኳን የኔ ጭንቀት ለምን አይገባውም እንዴ በራሴ ጉዳይ ዝም በል ጠጣ ደንስ ስላለኝ ዝም የምል ይመስለዋል?!
ወደ ሽንት ቤት ሌላ ሰው በሄደ እና በወጣ ቁጥር እያየሁ በጭንቀት ከመፈንዳቴ በፊት እራሴ ሄጄ ለማረጋገጥ ስለፈለኩ•••
••• እሺ መጣሁ አንዴ ስመለስ አብሪያት እደንሳለሁ አልኩትና ሄድኩ መጀመሪያ ወደነመሲ ገልመጥ ሳደርግ ሁለቱ ብቻ ናቸው እነሱም እንደኔ ሰውየው የት ሄደ ብለው ግራ ተጋብተዋል መሰለኝ ግራና ቀኝ ይገላመጣሉ ።
ወደ ወንዶች ሽንት ቤት በፍጥነት ሄድኩና ከአምስቱ ሽንት ቤቶች መሀከል ክፍት የሆኑትን ሁለቱን አየት አድርጌ በማለፍ ሶስተኛውን ስበረግደው•••
----------
"ምን አይነት ሰው ነህ በናትህ! ምሽግ ውስጥ ነው እንዴ ያደከው? አታንኳኳም!" አለኝ በብስጭት አንድ የማላውቀው ሰው።
ይቅርታ ይቅርታ አልኩት ቆሌዬ ተገፎ!።
"ባክህ የምናባህ ይቅርታ ነው ይቅርታ ይላል እንዴ ደሞ የልቡን አድርሶ!" አለኝ።
ንግግሩ ሳቅ ጫረብኝ ።
አይይ ስካር ደጉ ታየኝ እኮ እሱን ሽንት ቤት ተቀምጦ በማየቴ የልቤ ሲደርስ እያልኩ ቀሪ ሁለቱ ክፍሎች ውስጥ ሰውየውን መፈለጌን ቀጠልኩ•••
ሰውየው ድራሹ የለም ። ግራ ተጋብቼ በቆምኩበት ሽንትቤቱን ድንገት ከፍቼበት የተበሳጨው ሰውዬ ቆየት እያለ ሲሳደብ ሰማሁት•••
እንዴ! እሄ ደሞ እያረፈ ነው እንዴ እሚሳደበው!
አልኩና ከውስጥ ዘግተህ አትቀመጥም ነበር ሰካራም! ብየው ወደ ቦታዬ ስመለስ የኮንትራት ደንበኛዬ (ዝም ብለህ ጠጣ ሲለኝ የነበረውን ሰው ) ቦታው ላይ አጣሁት።
የክፍሉን ዙርያ ገባ ቃኘት አደረኩ ። እክፍሉ ውስጥም የለም።
እየተደነባበርኩ እነመሲ ወዳሉበት ክፍል በር ስጠጋ •••
አይኔን ተጠራጠርኩት ! ሽንት ቤት ሰውየውን ፍለጋ ደርሼ እስክመጣ ከምኔው ሄዶ ከምኔው ተዋውቋቸው እና ተግባብቷቸው መሳሳቅ እንደጀመሩ ለማመን በሚከብድ ሁኔታ•••
እሱ ያወራል እነመሲ ይስቃሉ አሁንም ያወራል እነሱ ተያይተው ያሽካካሉ አፌን ከፍቼ ስመለከታቸው ቆየሁና እየሆነ ያለው ነገር ከመጠጡ ጋር ተደምሮ ትርምስምስ እንዳለብኝ ወደ ቦታዬ ተመለስኩ።
ትንሽ ቆየሁና እሱ አልመጣ ሲለኝ መኖር አለመኖራቸውን ላረጋግጥ ድጋሚ ሄድኩ።
ጭራሽ እሱና መሲ ተጣብቀው እየደነሱ ነው። ጀርባዋን ሰጥታው እላዩ ላይ ተጣብቃለች ወገቧን አቅፎ ማጅራቷ አከባቢ እንደመሳም እየቃጣው ለስለስ ባለው ሙዚቃ ይወዛወዛሉ ።
ልጅቷ ቦታዎ ላይ ተቀምጣ ትቁለጨለጫለች ።
ምናልባት አስጠማጇን እራሷን መሲን አጥምዶ ልጅቷን ሊያፋታት አስቦ ይሆን እንዴ?
ብዬ አሰብኩና የሆነ የደስታ ስሜት ውስጤን ሲነዝረው ታውቀኝ።
ሰውየውን ምን አድርጎት ነው? የሚለው ጥያቄ ስላልተመለሰልኝና ዝም ብለህ ጠጣ ከማለት ውጪ ምን እንዳደረገ? እና ምን ሊያደርግ እንዳሰበ በግልፅ ሊነግረኝ ፍቃደኛ ባለመሆኑ ግን ደስታዬ ብርዝ ሆነብኝ!!
በዳንሳችው መሀል ድንገት ተያየን ጠቀሰኝ እኔ ግን ግራ ተጋብቶ ያፈጠጠ እንጂ የሚጨፈን አይን አልነበረኝም እና ምኑም ላልገባኝ ጥቅሻው መልስ ነፈኩት ዝም ብዬው ከራሴ ጋር እያልጎመጎምኩ•••
ግራ አጋባኝ እኮ እሚገርም ሰው ነው እሄ ሰውዬ እያልኩ ወደ ቦታዩ ተመለስኩ ።
በተመለስኩ በደቂቃዎች ውስጥ ወደኔ በመምጣ
"ፈታ በል አቢቲ ዝም ብለህ አትጨናነቅ እኔ አንድ ነገር ላደርግ ካሰብኩ ውጤቱን እንጂ ጅማሬው ማውራት አልወድም! ለምን መሰለህ?••• መጀመራችንን እንጂ መጨረሳችንን የሚያውቀው ፈጣሪ ብቻ ስለሆነ በርግጥ አሁን ያሰብኩትን ነገር ፈጣሪ ሳይሆን ሰይጣን ነው አጨራረሱን የሚያሳምረው አየህ አንዳንዴ ጥሩ ነገር ለመስራት መጥፎ ነገር ውስጥ መግባቱ ግድ ይልሀል የስራህ ውጤት ከፊሉ የፈጣሪ ከፊሉ የሰይጣን ይሆናል ድብልቅ!
ነገር ግን ፈጣሪ ልብን ሰይጣን ስራን ይመረምራል ብዬ ስለማምን እሱ አያሳስበኝም ! ለማንኛውም ስጨርስ ሁሉንም ነገር እነግርሀለሁ አሁን አንተ አታስፈልገኝም ከሀያ ደቂቃ ቡሀላ በር ላይ ሁለት ባጃጅ እፈልጋለሁ ካንተ ጋር ካሁን ቡሀላ ምናልባት ነገ ካልሄድኩ እንገናኝ ይሆናል ብሎኝ ከኔ መልስ ሳይጠብቅ ጥሎኝ ሄደ ።
እንኳን ምን ለማለት እንደፈለገ ሊገባኝ ያለውን መልሼ ማስታወስ አልቻልኩም።
አንዳንድ ሰዎችን ትንሽ ግዜ አብረሀቸው በቆየህ ቁጥር ወይ በደንብ ታውቃቸዋለህ ወይ ጭራሽ እንደማታውቃቸው ይገባሀል የሚለው የጆሲ ጋደኛ ትዝ አለኝ።
ያለኝ አማራጭ መወዛገቤን ትቼ እስከመጨረሻው የሚሆነውን ነገር መመልከት ብቻ ሆነ።
ካስር ደቂቃ ቡሀላ ኮፍያዬን አዘቅዝቄ አንገቴን አቀርቅሬ ከጭፈራ ቤቱ በፍጥነት ወጣሁ ።
ከማውቃቸው በዛ ሰአት ስራ ላይ ይሆናሉ ብዬ ወዳሰበኳቸው ሁለት የባጃጅ ሹፌሮች ደወልኩና በር ላይ እንዲጠብቁአቸው ነግሬ እኔ ራቅ ብዬ ባጃጄ ውስጥ እንዳደፈጥኩ ስጠባበቅ ልክ ባለው ሰአት መሲ እና እሱ ተቃቅፈው ግራና ቀኝ እየትወዛወዙ እና እየተሳሳቁ ልጅቷም በሁኔታቸው አብራ ፈገግ እያለች ወደ ጎን ተደርድረው ከጭፈራ ቤቱ ሲቅወጡ ተመለከትኩ።
ባጃጆቹ ጋር እንደደረሱ ሰውየው ያቀፋትን መሲን ለቅቅ አድርጎ ወደ ልጅታ ተጠጋና አናገራት። ጨብጣው ከፉት ያለው ባጃጅ ውስጥ ጥልቅ አለች እሱና መሲ ሌላኛው ባጃጅ ውስጥ ገቡና ፊትና ኋላ ሆነው ተፈተለኩ እኔም ተከትያቸው ተፈተለኩ ።
በቅርብ እየተከተልኳቸው ልጅቷን ወደ ያዘው የባጃጅ ሹፌር ደወልኩ ። አነሳው።
ምን አለህ? ስለው•••
"ግቢ አድርሳት አለኝ ወደ ግቢ እየወሰድኳት ነው " አለኝ ። በረጅሙ ተነፈስኩ እና ጀግና አቦ አልኩት ግራ ያጋባኝን ሰው።
ወደ ግቢ የሚሄደው ባጃጅና እነመሲን የያዘው ባጃጅ የሚለያዩበት ቦታ ላይ ደረሱ ልጅቷን የያዘው በዲፖ በኩል ሽቅብ ወደ ሰይዶ ሲሸመጥጠው እነመሲን የያዘው ባጃጅ በፀሀይ ሆቴል በኩል ቁልቁል ቆሰቆሰው•••
ወደያዘው ክፍል ይዟት እየሄደ መሆኑን ብረዳም ልጅቷን ትቼ የመሲን መጨረሻ ለማየት ተከተልኳቸው ።
ደረሱ ። ከባጇጃ ወርደው የሰከረችውን መሲን ከመሸከም በማይተናነስ ሀኔታ ደግፎ ወደያዘው ክፍል አስገባት ።
ለሰው ያጠመድሽው እራስሽ ላይ ባርቆ ሊዘርርሽ ነው አይ መሲ !
እያልኩ ወደ ቤቴ ገብቼ ተዘረርኩ ጥዋት ሶስት ሰአት ላይ የቀሰቀሰኝ የስልኬ ጥሪ ነበር ሰውየው ነው በፍጥነት አንስቼው ሀሎ ስል•••
" ደና አደርክ አቢቲ ተመልሼ ወደመጣሁበት እየሄድኩ ነው ምናልባት ከስድስት ወር ቡሀላ እመጣ ይሆናል የማታውን ሙሉ ትያትር ለማየት እና ለመስማት እንደምትፈልግ አውቃለሁ ቴሌግራምህን ክፈት ሶስት መልእክቶች አሉህ በድምፅ! በፅሁፍና; በምስል! ቻው !!"ብቻ ብሎኝ ስልኩን ዘጋው•••
በፍጥነት ቴሌግራም አካውንቴን ስበረግደው ቀድሞ የታየኝ የመሲ ልብስ አልባ ገላ የሚያሳየው ቪድዬ ነበር ከስር የመሲን ስልክ ቁጥር አስቀምጦ
"አቢቲ በዚህ ቁጥሯ የተከፈተ ቴሌግራም አካውንቷ ላይ ቪድዬዋን ልከህ ካሁን ቡሀላ በሴት ተማሪዎች ሂወት መነገዷን እንድታቆም ያለ በለዚያ ግን ቪድዮዋን እንደምትለቀው ነግረህ አስጠንቅቃት!" ይላል በርግጌ ከፍራሼ ላይ ተነሳሁ።
ቪድዮውን ስከፍተው ••

ይቀጥላል...


@yederasiyanbet
3.7K viewsnothing, 16:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-12 19:36:35 በጎዳና ላይ ካገኘዋቸው የኔ ቢጤ አባት ጋ ያደረኩት የሦስተኛው ቀን ንግግር ክፍል 14

ለጥቅምና ለእድገትህ ስትል ጊዜያዊ አለመመቸትን ለመታገስ ቁረኛ ሁን ይሉኝታን ትተህ ዝቅ ብለህ አውቀትን መቃረም ልመድ እያሉ ንግግራቸውን ቀጠሉ።ከጎዳና ተዳዳሪ ለዛውም ምንም አልተማርኩም ካለ ግለሰብ ይሄን ያክል እውቀት እያልኩ ማዳመጤን ቀጠልኩ የሳቸው ንግግርም እየጋለ መጣ።

ልጄ አለም በስንት መከራ የሚሰራውን የኛ አባቶች በቀላል መንገድ እየሰሩ ነው። አኔተ ሂደህ ማየት ብቻ ነው የሚጠበቅብህ በአለም ላይ መድሃኒት የሌለው በሽታን እያጠፉት ነው ግን እነሱን ማየትም ሆነ መንካት አልታደላችሁም አየህ ልጄ ብዙ ማወቅ ከፈለክ ዝቅ በል ስለ ደረሰብህ በደል ማንንም አትውቀስ ሁሉም በጊዜው የሰራውን ያገኛል። ገንዘብህን ብትከሰክስ ጤናህን ቢያሳጡህ ህልምህን ቢያጠፉት እምነትህን ቢሰብሩት ቢክዱህ ቢዋሹህ አሁን ምን ሆንክ አሉኝና ቆጣ አሉ አሁን ስቃይ ላይ ብትሆንም አመስጋኝ ሁን ዛሬ ብዙ ሰማህ የሰማኸውንም ተግብር አሉኝ። እኒህ አባት ለምንድን ነው ንግግራችንን እሚቀላቅሉት አውቀው ነው ወይስ ምንድነው እያልኩ ግራ ስጋባ አየህ ልጄ አሉኝ ከሃሳቤ ተመለስኩና መስማቱን ቀጠልኩበት።

ስኬትን ከፈለክ ስኬትን አላማህ አድርገህ አትያዝ። የምታምንበትንና የምትወደውን ነገር ከልብህ ስታደርግ ስኬት ራሱ ይመጣል ለትክክለኛ አላማ መቆም ስኬትን ይቀድማል እንጂ ስኬት አላማን አይቀድምም።

ተሳካላቸው በመባል የሚታወቁ ሰዎች ለስኬት የኖሩ ሰወች ሳይሆን ለአንድ አላማ በፅናት የኖሩ ናቸው ያንን ሲያደርጉ ስኬት ተከተላቸው ለስኬት የሚኖሩ ሰው ስኬት ያጣ ሲመስለው ያቆማል ሲሉኝ ቆይ ይህ ንግግር እንዴት አንድ ምንም አልተማርኩም ከሚል ሰው ይወጣል እያልኩ ጭራሽ ግራ እየተጋባሁ እያለ ንግግራቸውን ቀጠሉ።

የምትወደውንና መልካም የሆነውን አድርግ ያንን የምታደርገውን ነገር ደግሞ ውደደው ልጄ ስኬትን ፍለጋ ከአላማ ውጪ የሆነን ታላቅ ነገር ከማድረግ አላማን በመከተል አስቸጋሪ ጎዳና መጓዝ ይመረጣል ስለዚህ ለአላማህ አስቸጋሪ መንገድን ሂድ በእሾህ ላይ ተራመድ አሉኝና ዝም አሉ እና ሁለቶቹ እርስ በርስ ተያዩና በጣም እምወዳቸው ሕዝቅያስ ንግግሩን ተቀብለው ንግግራቸውን ቀጠሉ።

እኒህ ሰዎች ግን ምንድን ናቸው እያልኩ ግራ ግብት አለኝ ጎዳና ተዳዳሪ ናቸው ወይስ ሃገር አስተዳዳሪ እንዴት ሰው ይህን ምጡቅ አስተሳሰብ ይዞ መንገድ ላይ ቆይ ግን ይች ሃገር እንዴት ልጇን መለየት ያቅታታል እያልኩ በውስጤ እርር አልኩኝ የተለመደው እምባዬ እንዳይፈስ ብዬ ከሃሳብ ተመለስኩና እሚሉትን መስማት ያዝኩኝ።

የኔ ልጅ አሉኝ ፈገግ ብለው ሕዝቅያስ የኔ ልጅ ሲሉኝ የወለደኝ አባቴ ትምህርት ቤት ወይም በመታወቂያ ካርዴ ላይ የምጠራበት መልኩን ግን የማላቀው አባቴ ከመቃብር ተነስቶ የጠራኝ ይመስለኛል አላቅም ብቻ ውስጤ በደስታ ይሞላል በሃሳብ መስመጤን አይተው የኔ ልጅ ሲሉኝ ድጋሚ አቤት አባቴ ብዬ ከሃሳቤ ተመልሼ አይን አይናቸውን ማየት ጀመርኩ።

ንግግራቸውንም እንዲህ ሲሉ ጀመሩ የኔ ልጅ በትንሽ ማገዶ ከፍተኛ ሙቀት እንደማይገኝ ሁሉ በትንሽ ምኞት ትልቅ ዉጤት መጠበቅ ከንቱ ድካም ነው። አንተ ያጋጠሙህ ነገሮች ዉጤት ሳትሆን የዉሳኔህ ዉጤት ነህ። ህልምህን እዉን አድርገዉ አለበለዚያ ሌላ ሰዉ የራሱን ህልም እንድትገነባለት ይቀጥርሃል ተቀጣሪ ደግሞ መሆን የለብህም አዕምሮህን በደንብ አሰራው እና እምትፈልገውን ነገር አዝዘው አሉኝና ንግግራቸውን ቀጠሉ።

የኔ ልጅ ረዥም እድሜ ማለት የበትር ምርኩዝ እስኪይዙ መኖር አይደለም።ረዥም እድሜ ማለት በዉስጥህ ያለዉን ራዕይን ከመጨረሻ ማድረስ ማለት ነዉ፡፡

የኔ ልጅ ስኬታማ ለመሆን ለስኬት ያለህ ፍላጎት ለዉድቀት ካለህ ፍርሃት መብለጥ አለበት። ገንዘብ ካጣህ ምንም ነገር አላጣህም ጊዜ ካጣህ አንዳች ነገር አጥተሃል ተስፋ ካጣህ ግን ሁሉንም ነገር አጥተሃልና ተስፋ ማጣት የለብህም የኔ ልጅ አትፍራ ደፋር መሆን አለብህ።

ድፍረት ማለት ፍርሃትን መቋቋምና በፍርሃት ላይ መንገስ እንጂ ፍርሃትን ማስቀደም አይደለም። ማየት የማይችል ሰዉ የዓለምን ዳርቻ የሚወስነዉ በዳሰስዉ ልክ ብቻ ሲሆን ራዕይ ያለዉ ሰዉ ግን የዓለምን ዳርቻ የሚወስነው በራዕዩ ልክ ነዉ እሉኝ እኒህን አባቶች በማግኜቴ ፈጣሪዬን ቀና ብዬ አቤቱ የእናታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ልጅ እግዚያብሄር ሆይ ተመስገን ሁሌም ክበርልን አለም ስራህን ይወቅ ብዬ አመስግኜ ሳልጨርስ እምባዬ በጉንጨ ላይ ፈሰሰ።

ሁለቱም እምሆነውን አይተው ፈገግ አሉና አባ ሕዝቅያስ ንግግራቸውን ቀጠሉ የኔ ልጅ የችግርህን ብዛት ለፈጣሪ ከምትናገር የፈጣሪን ታላቅነት ለችግርህ ተናገር አሉኝና ይህን አስከተሉ you will not get your dream without God's help, so in any case, do not forget God!! አሉኝ። በጣም ደነገጥኩ ቆይ እንዴት እንግዘኛቸው እስካሁን አይጠፋባቸውም እያልኩ እያለ ጭራሽ የምፈራቸው አባትም በአውንታ ጭንቅላታቸውን ሲያወዛውዙ አየኋቸው።

እርስዎም እንግሊዝኛ ይችላሉ እንዴት አልኳቸው ሳቅ አሉና የድሮ ዱርዬ አራዳ ነበርኩ እኮ አሉኝና ሳቃቸውን ለቀቁት እና እንግሊዝኛ ይችላሉ ማለት ነው? አልኳቸው በመገረም ትንሽ ዝም አሉና እንዲህ አሉኝ street kids can do anything እንዲህ ሲሉኝ ከተቀመጥኩበት ብድግ አልኩኝ እኒህ ሰዎች እየቀለዱብኝ ነው እንዴት አልኩኝ።

በጣም ግራ አጋቡኝ የምፈራቸው አባት ቀስ ብለው እንዲህ አሉኝ ልጄ የጎዳና ልጆች እኮ እማያውቁት እማይችሉት ነገር የለም ከእራብ እስከ ጥጋብ ከብርድ እስከ ሙቀት ችግር መከራ አዲስ ነገር ሸክም ትችት...ሁሉንም ነገር ያውቃሉ እኮ አሉኝ።

ንግግራቸው በከፊል ቢገባኝም ይህን እሚመስል የውጭ ሃገር ኗሪ በሚመስል አነጋገር የተናገሩት እንግሊዝኛ ግን ምንም አልተዋጠልኝም ሕዝቅያስስ እሽ ባይሆን ሁለት ዲግሪ አለኝ ብለውኛል የዚህኛው አባት እንግሊዝኛ ግን አልተዋጠልኝም።

በጣም ግራ አጋብተውኛል ቢሆኖም ሁሉንም በሂደት እደርስበታለሁ ብዬ እንዲህ ስል ሁለቱንም ጠየኳቸው ኢትዮጵያን እኛ ነን እምናኖራት ወይስ እሷ ነች እኛን የምታኖረን አልኳቸውና አሁንም የዚህን ጥያቄ መልስ ሳልጠብቅ እንዲህ ስል ሌላ ጥያቄ አስከተልኩኝ አንድ ሰው ችግር ውስጥ በሆነ ሰዓት ያ ችግር እሚያልፍ እስከማይመስለው ድረስ ያስባል ያንን ችግር እንዴት ማስቆም ይቻላል አልኳቸው።

ሁለቱም ፈገግ አሉና የምወዳቸው አባት እንዲህ ሲሉ ንግግራቸውን ቀጠሉ Ethiopia is useless without us and we are useless without Ethiopia እንደውም አለም ያለ ኢትዮጵያ ከንቱ ነች አሉኝ ኮስተር ብለው እንዲህ ሲሉም ንግግራቸውን ቀጠሉ the existence of one is important to the other አይደል የሚባለው አሉኝ በለው አልኩኝ ለራሴ ሲመስለኝ ገና እኒህን ሰዎች አላቃቸውም እያልኩኝ እያለ እንዲህ ሲሉ ንግግራቸውን ቀጠሉ።
ክፍል15...ይቀጥላል

@yederasiyanbet
2.7K viewsnothing, 16:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-12 19:35:44 በጎዳና ላይ ካገኘዋቸው የኔ ቢጤ አባት ጋ ያደረኩት የሦስተኛው ቀን ንግግር ክፍል 13

እድሜዬ ከ80በላይ ነው አሉኝና በትዝታ ስምጥ አሉ ወዲያው ፊታቸው ቅይርይር አለ የተከፉ ይመስላሉ አይናቸው ላይ የእምባ ጠብታ ሳይ አንጀቴ ስፍስፍ አለ አምባዬን ማቆም አቃተኝ አይናቸውን እብስ አደረጉና እንዲህ ሲሉ ንግግራቸውን ቀጠሉ። ልጄ እኔ ከማን ልወለድ ከማን የማውቀው ነገር የለኝም ጎዳና ላይ ነው እራሴን ያገኘሁት ማን ይውለደኝ ከማን ልወለድ የማውቀው ታሪክ የለም።

ብቻ እራሴን ያገኘሁት መንገድ ላይ ነው እራሴን ካወኩ ጀምሮ እዚሁ በጎዳና ላይ ነው የኖርኩኝ በጎዳና ከ80አመት በላይ አሳልፊያለሁ አሉኝ። ይህን ሲሉኝ በሃዘን እርር አልኩኝ። ወዲያው አንድ ጥያቄ መጣልኝና እንዲህ ስል ጥያቄዬን ጠየኳቸው። እኒህ አባት ቤት ንብረት አለኝ አሁን ግን ለደካሞች መጦሪያ አድርጌዋለሁ ብለውኝ ነበር ታድያ እርስዎ ለምን እዛ አይሄዱም እድሜዎም እኮ ብዙ ነው ደክመዋል አልኳቸው።

ልክ ነህ አባታችን ሕዝቅያስ ቤት ንብረት አላቸው ሁሉም የሞላላቸው የኢትዮጵያ ድንቅ አባት ናቸው ሲሉኝ እንዴ ሕዝቅያስ ነው ስማቸው አልኩኝ እስካሁን ስማቸውን አታውቀውም አሉኝና ሳቁብኝ አዎ አላውቅም ከምክራቸውና ከህይወት ገጠመኛቸው እንጂ ከስማቸው ምን አለኝ ብለው ነው አልኳቸው። እሱስ ልክ ነህ አሉኝና ዝም አሉ። እና ለምን አባታችን ቤት አይሄዱም አልኳቸው አባታችን ሕዝቅያስ ለምን እንዳልሄዱ ታውቃለህ አሉኝ አይ ምክንያታቸው ብዙም አሳማኝ አይደለም አልኳቸው።

ልጄ መስማት አቅቶህ ወይም መረዳት አልችል ብለህ ይሆናል እንጂ ንግግራቸው እንኳን ሁልጊዜም አሳማኝ ነው አሉኝና የኔም ምክንያት ተመሳሳይ ነው እንጂ እንድሄድ በጣም ጥረው ነበር አሉኝ። ሁለቱ ሲተያዩ በስስት ነው አቤት ፍቅር በጣም ያስቀናሉ። ቀጠልኩኝና እንዲህ አልኩኝ ግዕዝ ከየት ተምረው ነው ቅድም ሲያወሩ የሰማዎት አልኩኝ ልጄ ግዕዝ እኮ የኛ የአፍ መፍቻ ቋንቋችን ነበር እኛ ጣልነው እንጂ አሉኝ ገባኝ ግን የት ነው የተማሩ አልኳቸው። የምዎዳቸው አባት ሕዝቅያስ በመሀል ገቡና የኔ ልጅ የማይጠየቅ ጥያቄ አንዳንዴ መዝለል ልመድ እንጅ አሉኝ እንዴ አባቴ አጠይቁኝ እኮ ነው ሃገር ከሃገር የሚያፈርስ አልኳቸው ልክ ብለሃል አሉና ሁለቱም በአንድነት አጨበጨቡ።

የት እንደተማርኩ ትደርስበታለህ ብለው ወሬያቸውን ሳይጨርሱ እሽ ለምንድን ነው ትላንት እንደዚያ ያዩኝ ምንስ ተገንቶ ነው ዛሬ እንዲህ ደግ የሆኑት አልኳቸው ፈራ ተባ እያልኩኝ።ሳቅ አሉና የኔ ልጅ እናንተ እኛ እብዶችን እንደምትፈሩን ሁሉ እኛም እናንተን እንፈራችኋለን።

እኛ የጎዳና ነዋሪዎች እብዶች ወይም ለማኞች አይደለንም እኛ የናንተን ቦታ ብንይዝ የፍቅር አባቶች የሰላም መስራቾች ህዝቦች ነን አሉና እንደው እውነት ይወራ ከተባለ እኮ እብዶች እናንተ ናችሁ ላላበደ እብድ ብላችሁ ስም የምታወጡ አሉኝና ኮስተር አሉ። የሁለቱም አባቶች ንግግር በቀስታ የተሞላ ምርጥ መልክ የያዘ ለመስማት የማይከብድ ደስ የሚል ቃና ያላው ድምፅ አላቸው።

ልጄ እናንተ ማለት እኮ ህፃን አጋድማችሁ የምትደፍሩ ለአለም የሚፀልዩ በነሱ በረከት የምንኖር ስለ ሃጢያታችን የሚያለቅሱ የገዳም እናቶችን የምትደፍሩ የማታከብሩ በየ መንገዱ የአለምን እናት እናት አይደለችም እያላችሁ የምትጮሁ ከእንስሳት በባሰ በየ ጎዳናው ዝሙት የምታደርጉ አራዳ ነን ብላችሁ የወረዳችሁ የተማርን ነን ብላችሁ ያልተማራችሁ፣ከናንተ ሆድ ይልቅ የሌላ ሰው ሆድ የማይታያችሁ አጋሰሶች እኔን እንጂ እኛን የማታውቁ እብዶች ለሃገር እንቁም ያሉትን ንፁሃን የምትቀብሩ ሲታመኑላችሁ የማትታመኑ ፍቅር ሲሰጧችሁ የማትወዱ...ከንቱ እብዶች አብዳችኋል ግን እንደ ጤነኛ የምትኖሩ አስመሳይ ፍጡራን ናችሁ አሉና ማዕቱን አፈሉብኝ።

የመከራከሪያ አንደበት ግን አልነበረኝም እንደውም አሳነሱን እንጂ ከዚህም በላይ ነን። ንግግራቸው አሁንም እንደቀጠለ ነው የኔ ልጅ ኢትዮጵያ የወደቀችዉ በተማረው ህብረተሰብ ነው።መማር በወረቀት ላይ በሰፈረ ውጤት መለካት አልነበረበትም ይቺ ሃገር ወረቀት ሳይሆን የምትሻ ጭንቅላት ነው አሉኝ እራሳቸውን በሌባ ጣታቸው እየነካኩና እያሳዩኝ። ሸምድዶ በተማረ ሳንሆን ጭንቅላት ባለው ሰው ነበር መመራት ያለባት ወደ ገጠሩ ወጣ ብለህ አባቶችን ብታይ እዚህ በስንት መከራ የሚፈጠረውን ፈጠራ ፈጥረው ታገኛቸዋለህ አሉኝና ቀጠሉ።

እስኪ ልጠይቅህ እዚህ አለም ላይ ድንጋይን እንደ ውሃ የሚያፈስ ቴክኖሎጂ አለ አሉኝ?ልጄ እኔ በአይኔ ተመልክቻለሁ ድንጋይን እንደ ውሃ ሲያፈሱት ካላመንከኝ እኒህን አባት ጠይቃቸው ከኔ በላይ እሳቸዎ ያውቃሉ አየህ ድንጋይ እንደ ውሃ የሚያቀልጡት አባቶች እነማን እንደሆኑ ያልተማሩት ናቸው አሉኝና ቆጣ አሉ።እውቀት ወረቀት ወይም የመመረቂያ ጋውን መልበስ አይደለም እናንተ የምታውቁት እዉቀት ከንቱ ድካም ነው።

እኛ ለማኝ እብድ ብንመስልም ንፁሀን ነን አሉኝና የሃዘን ፊት አሳዩኝ። ልጄ ያልተማረ የምትሉት ማህበረሰብ እንቁ እውቀት አለው ችግሩ አንድ ቦታ ብቻ ታፍኖ እውቀቱን አያወጣውም በየ ቤቱ ገብተህ ብትመለከት ግን ሁሉም ብርሃን ነው። ከተሜነት የምትሉት ግን እብደት ነው አየህ ልጄ አሉ ጠንከር ብለው ንግግራቸው ማቆሚያ ያለው አይመስልም በዚች አለም ላይ ስትኖር ከዚህ በፊት አድርገህ የማታውቀውን ነገር ማድረግ ስትጀምር ከዚህ በፊት አድርገህ የማታቀውን አግኝተህ የማታቀውን አዲስ ነገር ማግኘት ትጀምራለህ።ከዚህ በፊት ያልነበረህን ነገር ለማግኘት ከፈለክ ከዚህ በፊት አድርገህ የማታቀውን ነገር ለማድረግ ፍቃደኛ መሆን አለብህ።

አዲስና የላቀ ልምምድ ከፈለክ አዳዲስና ሳይማሩ የተማሩ ማህበረሰቦችን ጋር መተዋወቅ የግድ ነው።በተመሳሳይ የተከፈተ በር እየገባህና እየወጣህ ሌላ እድል ልታገኝ አትችልም። አዲስ እድል ከፈለክ አዲስ በርን ማንኳኳት አለብህ ሰው ያላወቀውን መንገድ መጠቀም መልመድ አለብህ የተለመደ ስራ እየሰራህ ሌላ የገቢ ደረጃ አትጠብቅ አዲስና የጨመረ ገቢ ከፈለክ አዲስና ተጨማሪ ገቢ የሚሰጥህ ስራ ወይም ኢንቨስትመንት ውስጥ መግባት አስፈላጊ ነው አዲስ ኢንቨስትመንት ወይም ስራ ከፈለክ ደግሞ ታች ያሉ የመሰሏችሁ ነገር ግን እላይ ያሉ እንቁ የመንገድ ላይ ሽማግሌዎችንና የገዳም አባቶችን እንዲሁም ሳይማሩ የተማረውን የሚቀልቡትን ምሁራን ገበሬዎችን መጠቀም ይኖርብሃል።

በምታውቀው እውቀት ዙሪያ የመሽከርከር ስራ እየሰራህ በአዲስ እውቀት ማደግን አትጠብቅ አዲስ እውቀት ለማግኘት አዳዲስ ነገር ለማንበብ ለማየትና ለመስማት ክፍት መሆን አለብህ ዛሬ ከኛ ብዙ ተምርህ ይሆናል ይህ የሆነው ዝቅ ብለህ ስላዬህ ነው አዬህ የኔ ልጄ የሚመችህ ሰፈር እየዋልክ የሚመችህን ነገር እያደረክ ከሚመችህ ሰው ጋር ብቻ እየተገናኘህ የሰለቸህን የኑሮ አዙሪትና ድግግሞሽ እንዲለወጥ አትጠብቅ የለመድከውና የሰለቸህ ነገር እንዲለወጥ ከፈለክ ላልለመድከውና እንግዳ ለሆነ ነገር ማካፈልንና ዝቅ ማለትን መልመድ አስፈላጊ ነው።ለጥቅምና ለእድገትህ ስትል ጊዜያዊ አለመመቸትን ለመታገስ ቁረኛ ሁን ይሉኝታን ትተህ ዝቅ ብለህ አውቅን መቃረም ልመድ እያሉ ንግግራቸውን ቀጠሉ።ከጎዳና ተዳዳሪ ለዛውም ምንም አልተማርኩም ካለ ግለሰብ ይሄን ያክል እውቀት እያልኩ ማዳመጤን ቀጠልኩ
ክፍል14...ይቀጥላል


@yederasiyanbet
2.5K viewsnothing, 16:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ