Get Mystery Box with random crypto!

በጎዳና ላይ ካገኘዋቸው የኔ ቢጤ አባት ጋ ያደረኩት የሦስተኛው ቀን ንግግር ክፍል 13 እድሜዬ ከ | የደራሲያን ቤት 123@🇪🇹 የድሮ ሙዚቃዎች 📷📸

በጎዳና ላይ ካገኘዋቸው የኔ ቢጤ አባት ጋ ያደረኩት የሦስተኛው ቀን ንግግር ክፍል 13

እድሜዬ ከ80በላይ ነው አሉኝና በትዝታ ስምጥ አሉ ወዲያው ፊታቸው ቅይርይር አለ የተከፉ ይመስላሉ አይናቸው ላይ የእምባ ጠብታ ሳይ አንጀቴ ስፍስፍ አለ አምባዬን ማቆም አቃተኝ አይናቸውን እብስ አደረጉና እንዲህ ሲሉ ንግግራቸውን ቀጠሉ። ልጄ እኔ ከማን ልወለድ ከማን የማውቀው ነገር የለኝም ጎዳና ላይ ነው እራሴን ያገኘሁት ማን ይውለደኝ ከማን ልወለድ የማውቀው ታሪክ የለም።

ብቻ እራሴን ያገኘሁት መንገድ ላይ ነው እራሴን ካወኩ ጀምሮ እዚሁ በጎዳና ላይ ነው የኖርኩኝ በጎዳና ከ80አመት በላይ አሳልፊያለሁ አሉኝ። ይህን ሲሉኝ በሃዘን እርር አልኩኝ። ወዲያው አንድ ጥያቄ መጣልኝና እንዲህ ስል ጥያቄዬን ጠየኳቸው። እኒህ አባት ቤት ንብረት አለኝ አሁን ግን ለደካሞች መጦሪያ አድርጌዋለሁ ብለውኝ ነበር ታድያ እርስዎ ለምን እዛ አይሄዱም እድሜዎም እኮ ብዙ ነው ደክመዋል አልኳቸው።

ልክ ነህ አባታችን ሕዝቅያስ ቤት ንብረት አላቸው ሁሉም የሞላላቸው የኢትዮጵያ ድንቅ አባት ናቸው ሲሉኝ እንዴ ሕዝቅያስ ነው ስማቸው አልኩኝ እስካሁን ስማቸውን አታውቀውም አሉኝና ሳቁብኝ አዎ አላውቅም ከምክራቸውና ከህይወት ገጠመኛቸው እንጂ ከስማቸው ምን አለኝ ብለው ነው አልኳቸው። እሱስ ልክ ነህ አሉኝና ዝም አሉ። እና ለምን አባታችን ቤት አይሄዱም አልኳቸው አባታችን ሕዝቅያስ ለምን እንዳልሄዱ ታውቃለህ አሉኝ አይ ምክንያታቸው ብዙም አሳማኝ አይደለም አልኳቸው።

ልጄ መስማት አቅቶህ ወይም መረዳት አልችል ብለህ ይሆናል እንጂ ንግግራቸው እንኳን ሁልጊዜም አሳማኝ ነው አሉኝና የኔም ምክንያት ተመሳሳይ ነው እንጂ እንድሄድ በጣም ጥረው ነበር አሉኝ። ሁለቱ ሲተያዩ በስስት ነው አቤት ፍቅር በጣም ያስቀናሉ። ቀጠልኩኝና እንዲህ አልኩኝ ግዕዝ ከየት ተምረው ነው ቅድም ሲያወሩ የሰማዎት አልኩኝ ልጄ ግዕዝ እኮ የኛ የአፍ መፍቻ ቋንቋችን ነበር እኛ ጣልነው እንጂ አሉኝ ገባኝ ግን የት ነው የተማሩ አልኳቸው። የምዎዳቸው አባት ሕዝቅያስ በመሀል ገቡና የኔ ልጅ የማይጠየቅ ጥያቄ አንዳንዴ መዝለል ልመድ እንጅ አሉኝ እንዴ አባቴ አጠይቁኝ እኮ ነው ሃገር ከሃገር የሚያፈርስ አልኳቸው ልክ ብለሃል አሉና ሁለቱም በአንድነት አጨበጨቡ።

የት እንደተማርኩ ትደርስበታለህ ብለው ወሬያቸውን ሳይጨርሱ እሽ ለምንድን ነው ትላንት እንደዚያ ያዩኝ ምንስ ተገንቶ ነው ዛሬ እንዲህ ደግ የሆኑት አልኳቸው ፈራ ተባ እያልኩኝ።ሳቅ አሉና የኔ ልጅ እናንተ እኛ እብዶችን እንደምትፈሩን ሁሉ እኛም እናንተን እንፈራችኋለን።

እኛ የጎዳና ነዋሪዎች እብዶች ወይም ለማኞች አይደለንም እኛ የናንተን ቦታ ብንይዝ የፍቅር አባቶች የሰላም መስራቾች ህዝቦች ነን አሉና እንደው እውነት ይወራ ከተባለ እኮ እብዶች እናንተ ናችሁ ላላበደ እብድ ብላችሁ ስም የምታወጡ አሉኝና ኮስተር አሉ። የሁለቱም አባቶች ንግግር በቀስታ የተሞላ ምርጥ መልክ የያዘ ለመስማት የማይከብድ ደስ የሚል ቃና ያላው ድምፅ አላቸው።

ልጄ እናንተ ማለት እኮ ህፃን አጋድማችሁ የምትደፍሩ ለአለም የሚፀልዩ በነሱ በረከት የምንኖር ስለ ሃጢያታችን የሚያለቅሱ የገዳም እናቶችን የምትደፍሩ የማታከብሩ በየ መንገዱ የአለምን እናት እናት አይደለችም እያላችሁ የምትጮሁ ከእንስሳት በባሰ በየ ጎዳናው ዝሙት የምታደርጉ አራዳ ነን ብላችሁ የወረዳችሁ የተማርን ነን ብላችሁ ያልተማራችሁ፣ከናንተ ሆድ ይልቅ የሌላ ሰው ሆድ የማይታያችሁ አጋሰሶች እኔን እንጂ እኛን የማታውቁ እብዶች ለሃገር እንቁም ያሉትን ንፁሃን የምትቀብሩ ሲታመኑላችሁ የማትታመኑ ፍቅር ሲሰጧችሁ የማትወዱ...ከንቱ እብዶች አብዳችኋል ግን እንደ ጤነኛ የምትኖሩ አስመሳይ ፍጡራን ናችሁ አሉና ማዕቱን አፈሉብኝ።

የመከራከሪያ አንደበት ግን አልነበረኝም እንደውም አሳነሱን እንጂ ከዚህም በላይ ነን። ንግግራቸው አሁንም እንደቀጠለ ነው የኔ ልጅ ኢትዮጵያ የወደቀችዉ በተማረው ህብረተሰብ ነው።መማር በወረቀት ላይ በሰፈረ ውጤት መለካት አልነበረበትም ይቺ ሃገር ወረቀት ሳይሆን የምትሻ ጭንቅላት ነው አሉኝ እራሳቸውን በሌባ ጣታቸው እየነካኩና እያሳዩኝ። ሸምድዶ በተማረ ሳንሆን ጭንቅላት ባለው ሰው ነበር መመራት ያለባት ወደ ገጠሩ ወጣ ብለህ አባቶችን ብታይ እዚህ በስንት መከራ የሚፈጠረውን ፈጠራ ፈጥረው ታገኛቸዋለህ አሉኝና ቀጠሉ።

እስኪ ልጠይቅህ እዚህ አለም ላይ ድንጋይን እንደ ውሃ የሚያፈስ ቴክኖሎጂ አለ አሉኝ?ልጄ እኔ በአይኔ ተመልክቻለሁ ድንጋይን እንደ ውሃ ሲያፈሱት ካላመንከኝ እኒህን አባት ጠይቃቸው ከኔ በላይ እሳቸዎ ያውቃሉ አየህ ድንጋይ እንደ ውሃ የሚያቀልጡት አባቶች እነማን እንደሆኑ ያልተማሩት ናቸው አሉኝና ቆጣ አሉ።እውቀት ወረቀት ወይም የመመረቂያ ጋውን መልበስ አይደለም እናንተ የምታውቁት እዉቀት ከንቱ ድካም ነው።

እኛ ለማኝ እብድ ብንመስልም ንፁሀን ነን አሉኝና የሃዘን ፊት አሳዩኝ። ልጄ ያልተማረ የምትሉት ማህበረሰብ እንቁ እውቀት አለው ችግሩ አንድ ቦታ ብቻ ታፍኖ እውቀቱን አያወጣውም በየ ቤቱ ገብተህ ብትመለከት ግን ሁሉም ብርሃን ነው። ከተሜነት የምትሉት ግን እብደት ነው አየህ ልጄ አሉ ጠንከር ብለው ንግግራቸው ማቆሚያ ያለው አይመስልም በዚች አለም ላይ ስትኖር ከዚህ በፊት አድርገህ የማታውቀውን ነገር ማድረግ ስትጀምር ከዚህ በፊት አድርገህ የማታቀውን አግኝተህ የማታቀውን አዲስ ነገር ማግኘት ትጀምራለህ።ከዚህ በፊት ያልነበረህን ነገር ለማግኘት ከፈለክ ከዚህ በፊት አድርገህ የማታቀውን ነገር ለማድረግ ፍቃደኛ መሆን አለብህ።

አዲስና የላቀ ልምምድ ከፈለክ አዳዲስና ሳይማሩ የተማሩ ማህበረሰቦችን ጋር መተዋወቅ የግድ ነው።በተመሳሳይ የተከፈተ በር እየገባህና እየወጣህ ሌላ እድል ልታገኝ አትችልም። አዲስ እድል ከፈለክ አዲስ በርን ማንኳኳት አለብህ ሰው ያላወቀውን መንገድ መጠቀም መልመድ አለብህ የተለመደ ስራ እየሰራህ ሌላ የገቢ ደረጃ አትጠብቅ አዲስና የጨመረ ገቢ ከፈለክ አዲስና ተጨማሪ ገቢ የሚሰጥህ ስራ ወይም ኢንቨስትመንት ውስጥ መግባት አስፈላጊ ነው አዲስ ኢንቨስትመንት ወይም ስራ ከፈለክ ደግሞ ታች ያሉ የመሰሏችሁ ነገር ግን እላይ ያሉ እንቁ የመንገድ ላይ ሽማግሌዎችንና የገዳም አባቶችን እንዲሁም ሳይማሩ የተማረውን የሚቀልቡትን ምሁራን ገበሬዎችን መጠቀም ይኖርብሃል።

በምታውቀው እውቀት ዙሪያ የመሽከርከር ስራ እየሰራህ በአዲስ እውቀት ማደግን አትጠብቅ አዲስ እውቀት ለማግኘት አዳዲስ ነገር ለማንበብ ለማየትና ለመስማት ክፍት መሆን አለብህ ዛሬ ከኛ ብዙ ተምርህ ይሆናል ይህ የሆነው ዝቅ ብለህ ስላዬህ ነው አዬህ የኔ ልጄ የሚመችህ ሰፈር እየዋልክ የሚመችህን ነገር እያደረክ ከሚመችህ ሰው ጋር ብቻ እየተገናኘህ የሰለቸህን የኑሮ አዙሪትና ድግግሞሽ እንዲለወጥ አትጠብቅ የለመድከውና የሰለቸህ ነገር እንዲለወጥ ከፈለክ ላልለመድከውና እንግዳ ለሆነ ነገር ማካፈልንና ዝቅ ማለትን መልመድ አስፈላጊ ነው።ለጥቅምና ለእድገትህ ስትል ጊዜያዊ አለመመቸትን ለመታገስ ቁረኛ ሁን ይሉኝታን ትተህ ዝቅ ብለህ አውቅን መቃረም ልመድ እያሉ ንግግራቸውን ቀጠሉ።ከጎዳና ተዳዳሪ ለዛውም ምንም አልተማርኩም ካለ ግለሰብ ይሄን ያክል እውቀት እያልኩ ማዳመጤን ቀጠልኩ
ክፍል14...ይቀጥላል


@yederasiyanbet