Get Mystery Box with random crypto!

በጎዳና ላይ ካገኘዋቸው የኔ ቢጤ አባት ጋ ያደረኩት የሦስተኛው ቀን ንግግር ክፍል 14 ለጥቅምና | የደራሲያን ቤት 123@🇪🇹 የድሮ ሙዚቃዎች 📷📸

በጎዳና ላይ ካገኘዋቸው የኔ ቢጤ አባት ጋ ያደረኩት የሦስተኛው ቀን ንግግር ክፍል 14

ለጥቅምና ለእድገትህ ስትል ጊዜያዊ አለመመቸትን ለመታገስ ቁረኛ ሁን ይሉኝታን ትተህ ዝቅ ብለህ አውቀትን መቃረም ልመድ እያሉ ንግግራቸውን ቀጠሉ።ከጎዳና ተዳዳሪ ለዛውም ምንም አልተማርኩም ካለ ግለሰብ ይሄን ያክል እውቀት እያልኩ ማዳመጤን ቀጠልኩ የሳቸው ንግግርም እየጋለ መጣ።

ልጄ አለም በስንት መከራ የሚሰራውን የኛ አባቶች በቀላል መንገድ እየሰሩ ነው። አኔተ ሂደህ ማየት ብቻ ነው የሚጠበቅብህ በአለም ላይ መድሃኒት የሌለው በሽታን እያጠፉት ነው ግን እነሱን ማየትም ሆነ መንካት አልታደላችሁም አየህ ልጄ ብዙ ማወቅ ከፈለክ ዝቅ በል ስለ ደረሰብህ በደል ማንንም አትውቀስ ሁሉም በጊዜው የሰራውን ያገኛል። ገንዘብህን ብትከሰክስ ጤናህን ቢያሳጡህ ህልምህን ቢያጠፉት እምነትህን ቢሰብሩት ቢክዱህ ቢዋሹህ አሁን ምን ሆንክ አሉኝና ቆጣ አሉ አሁን ስቃይ ላይ ብትሆንም አመስጋኝ ሁን ዛሬ ብዙ ሰማህ የሰማኸውንም ተግብር አሉኝ። እኒህ አባት ለምንድን ነው ንግግራችንን እሚቀላቅሉት አውቀው ነው ወይስ ምንድነው እያልኩ ግራ ስጋባ አየህ ልጄ አሉኝ ከሃሳቤ ተመለስኩና መስማቱን ቀጠልኩበት።

ስኬትን ከፈለክ ስኬትን አላማህ አድርገህ አትያዝ። የምታምንበትንና የምትወደውን ነገር ከልብህ ስታደርግ ስኬት ራሱ ይመጣል ለትክክለኛ አላማ መቆም ስኬትን ይቀድማል እንጂ ስኬት አላማን አይቀድምም።

ተሳካላቸው በመባል የሚታወቁ ሰዎች ለስኬት የኖሩ ሰወች ሳይሆን ለአንድ አላማ በፅናት የኖሩ ናቸው ያንን ሲያደርጉ ስኬት ተከተላቸው ለስኬት የሚኖሩ ሰው ስኬት ያጣ ሲመስለው ያቆማል ሲሉኝ ቆይ ይህ ንግግር እንዴት አንድ ምንም አልተማርኩም ከሚል ሰው ይወጣል እያልኩ ጭራሽ ግራ እየተጋባሁ እያለ ንግግራቸውን ቀጠሉ።

የምትወደውንና መልካም የሆነውን አድርግ ያንን የምታደርገውን ነገር ደግሞ ውደደው ልጄ ስኬትን ፍለጋ ከአላማ ውጪ የሆነን ታላቅ ነገር ከማድረግ አላማን በመከተል አስቸጋሪ ጎዳና መጓዝ ይመረጣል ስለዚህ ለአላማህ አስቸጋሪ መንገድን ሂድ በእሾህ ላይ ተራመድ አሉኝና ዝም አሉ እና ሁለቶቹ እርስ በርስ ተያዩና በጣም እምወዳቸው ሕዝቅያስ ንግግሩን ተቀብለው ንግግራቸውን ቀጠሉ።

እኒህ ሰዎች ግን ምንድን ናቸው እያልኩ ግራ ግብት አለኝ ጎዳና ተዳዳሪ ናቸው ወይስ ሃገር አስተዳዳሪ እንዴት ሰው ይህን ምጡቅ አስተሳሰብ ይዞ መንገድ ላይ ቆይ ግን ይች ሃገር እንዴት ልጇን መለየት ያቅታታል እያልኩ በውስጤ እርር አልኩኝ የተለመደው እምባዬ እንዳይፈስ ብዬ ከሃሳብ ተመለስኩና እሚሉትን መስማት ያዝኩኝ።

የኔ ልጅ አሉኝ ፈገግ ብለው ሕዝቅያስ የኔ ልጅ ሲሉኝ የወለደኝ አባቴ ትምህርት ቤት ወይም በመታወቂያ ካርዴ ላይ የምጠራበት መልኩን ግን የማላቀው አባቴ ከመቃብር ተነስቶ የጠራኝ ይመስለኛል አላቅም ብቻ ውስጤ በደስታ ይሞላል በሃሳብ መስመጤን አይተው የኔ ልጅ ሲሉኝ ድጋሚ አቤት አባቴ ብዬ ከሃሳቤ ተመልሼ አይን አይናቸውን ማየት ጀመርኩ።

ንግግራቸውንም እንዲህ ሲሉ ጀመሩ የኔ ልጅ በትንሽ ማገዶ ከፍተኛ ሙቀት እንደማይገኝ ሁሉ በትንሽ ምኞት ትልቅ ዉጤት መጠበቅ ከንቱ ድካም ነው። አንተ ያጋጠሙህ ነገሮች ዉጤት ሳትሆን የዉሳኔህ ዉጤት ነህ። ህልምህን እዉን አድርገዉ አለበለዚያ ሌላ ሰዉ የራሱን ህልም እንድትገነባለት ይቀጥርሃል ተቀጣሪ ደግሞ መሆን የለብህም አዕምሮህን በደንብ አሰራው እና እምትፈልገውን ነገር አዝዘው አሉኝና ንግግራቸውን ቀጠሉ።

የኔ ልጅ ረዥም እድሜ ማለት የበትር ምርኩዝ እስኪይዙ መኖር አይደለም።ረዥም እድሜ ማለት በዉስጥህ ያለዉን ራዕይን ከመጨረሻ ማድረስ ማለት ነዉ፡፡

የኔ ልጅ ስኬታማ ለመሆን ለስኬት ያለህ ፍላጎት ለዉድቀት ካለህ ፍርሃት መብለጥ አለበት። ገንዘብ ካጣህ ምንም ነገር አላጣህም ጊዜ ካጣህ አንዳች ነገር አጥተሃል ተስፋ ካጣህ ግን ሁሉንም ነገር አጥተሃልና ተስፋ ማጣት የለብህም የኔ ልጅ አትፍራ ደፋር መሆን አለብህ።

ድፍረት ማለት ፍርሃትን መቋቋምና በፍርሃት ላይ መንገስ እንጂ ፍርሃትን ማስቀደም አይደለም። ማየት የማይችል ሰዉ የዓለምን ዳርቻ የሚወስነዉ በዳሰስዉ ልክ ብቻ ሲሆን ራዕይ ያለዉ ሰዉ ግን የዓለምን ዳርቻ የሚወስነው በራዕዩ ልክ ነዉ እሉኝ እኒህን አባቶች በማግኜቴ ፈጣሪዬን ቀና ብዬ አቤቱ የእናታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ልጅ እግዚያብሄር ሆይ ተመስገን ሁሌም ክበርልን አለም ስራህን ይወቅ ብዬ አመስግኜ ሳልጨርስ እምባዬ በጉንጨ ላይ ፈሰሰ።

ሁለቱም እምሆነውን አይተው ፈገግ አሉና አባ ሕዝቅያስ ንግግራቸውን ቀጠሉ የኔ ልጅ የችግርህን ብዛት ለፈጣሪ ከምትናገር የፈጣሪን ታላቅነት ለችግርህ ተናገር አሉኝና ይህን አስከተሉ you will not get your dream without God's help, so in any case, do not forget God!! አሉኝ። በጣም ደነገጥኩ ቆይ እንዴት እንግዘኛቸው እስካሁን አይጠፋባቸውም እያልኩ እያለ ጭራሽ የምፈራቸው አባትም በአውንታ ጭንቅላታቸውን ሲያወዛውዙ አየኋቸው።

እርስዎም እንግሊዝኛ ይችላሉ እንዴት አልኳቸው ሳቅ አሉና የድሮ ዱርዬ አራዳ ነበርኩ እኮ አሉኝና ሳቃቸውን ለቀቁት እና እንግሊዝኛ ይችላሉ ማለት ነው? አልኳቸው በመገረም ትንሽ ዝም አሉና እንዲህ አሉኝ street kids can do anything እንዲህ ሲሉኝ ከተቀመጥኩበት ብድግ አልኩኝ እኒህ ሰዎች እየቀለዱብኝ ነው እንዴት አልኩኝ።

በጣም ግራ አጋቡኝ የምፈራቸው አባት ቀስ ብለው እንዲህ አሉኝ ልጄ የጎዳና ልጆች እኮ እማያውቁት እማይችሉት ነገር የለም ከእራብ እስከ ጥጋብ ከብርድ እስከ ሙቀት ችግር መከራ አዲስ ነገር ሸክም ትችት...ሁሉንም ነገር ያውቃሉ እኮ አሉኝ።

ንግግራቸው በከፊል ቢገባኝም ይህን እሚመስል የውጭ ሃገር ኗሪ በሚመስል አነጋገር የተናገሩት እንግሊዝኛ ግን ምንም አልተዋጠልኝም ሕዝቅያስስ እሽ ባይሆን ሁለት ዲግሪ አለኝ ብለውኛል የዚህኛው አባት እንግሊዝኛ ግን አልተዋጠልኝም።

በጣም ግራ አጋብተውኛል ቢሆኖም ሁሉንም በሂደት እደርስበታለሁ ብዬ እንዲህ ስል ሁለቱንም ጠየኳቸው ኢትዮጵያን እኛ ነን እምናኖራት ወይስ እሷ ነች እኛን የምታኖረን አልኳቸውና አሁንም የዚህን ጥያቄ መልስ ሳልጠብቅ እንዲህ ስል ሌላ ጥያቄ አስከተልኩኝ አንድ ሰው ችግር ውስጥ በሆነ ሰዓት ያ ችግር እሚያልፍ እስከማይመስለው ድረስ ያስባል ያንን ችግር እንዴት ማስቆም ይቻላል አልኳቸው።

ሁለቱም ፈገግ አሉና የምወዳቸው አባት እንዲህ ሲሉ ንግግራቸውን ቀጠሉ Ethiopia is useless without us and we are useless without Ethiopia እንደውም አለም ያለ ኢትዮጵያ ከንቱ ነች አሉኝ ኮስተር ብለው እንዲህ ሲሉም ንግግራቸውን ቀጠሉ the existence of one is important to the other አይደል የሚባለው አሉኝ በለው አልኩኝ ለራሴ ሲመስለኝ ገና እኒህን ሰዎች አላቃቸውም እያልኩኝ እያለ እንዲህ ሲሉ ንግግራቸውን ቀጠሉ።
ክፍል15...ይቀጥላል

@yederasiyanbet