Get Mystery Box with random crypto!

ልጩህበት ! #ክፍል_አስራ_አራት መደነስ እኔ ሰውየው እምጥ ይግባ ስምጥ ሄዶ ካናገረው በኋ ላ | የደራሲያን ቤት 123@🇪🇹 የድሮ ሙዚቃዎች 📷📸

ልጩህበት !

#ክፍል_አስራ_አራት

መደነስ እኔ ሰውየው እምጥ ይግባ ስምጥ ሄዶ ካናገረው በኋ ላ ከሽንት ቤት ባለመመለሱ ምን አርጎት ነው የመጣው እያልኩ ግራ ተጋብቻለሁ ጭራሽ ደንስ ይለኛል ምን አይነት ባህሪ ያለው ሰው ነው እሄ ደግሞ ቢያንስ እንኳን የኔ ጭንቀት ለምን አይገባውም እንዴ በራሴ ጉዳይ ዝም በል ጠጣ ደንስ ስላለኝ ዝም የምል ይመስለዋል?!
ወደ ሽንት ቤት ሌላ ሰው በሄደ እና በወጣ ቁጥር እያየሁ በጭንቀት ከመፈንዳቴ በፊት እራሴ ሄጄ ለማረጋገጥ ስለፈለኩ•••
••• እሺ መጣሁ አንዴ ስመለስ አብሪያት እደንሳለሁ አልኩትና ሄድኩ መጀመሪያ ወደነመሲ ገልመጥ ሳደርግ ሁለቱ ብቻ ናቸው እነሱም እንደኔ ሰውየው የት ሄደ ብለው ግራ ተጋብተዋል መሰለኝ ግራና ቀኝ ይገላመጣሉ ።
ወደ ወንዶች ሽንት ቤት በፍጥነት ሄድኩና ከአምስቱ ሽንት ቤቶች መሀከል ክፍት የሆኑትን ሁለቱን አየት አድርጌ በማለፍ ሶስተኛውን ስበረግደው•••
----------
"ምን አይነት ሰው ነህ በናትህ! ምሽግ ውስጥ ነው እንዴ ያደከው? አታንኳኳም!" አለኝ በብስጭት አንድ የማላውቀው ሰው።
ይቅርታ ይቅርታ አልኩት ቆሌዬ ተገፎ!።
"ባክህ የምናባህ ይቅርታ ነው ይቅርታ ይላል እንዴ ደሞ የልቡን አድርሶ!" አለኝ።
ንግግሩ ሳቅ ጫረብኝ ።
አይይ ስካር ደጉ ታየኝ እኮ እሱን ሽንት ቤት ተቀምጦ በማየቴ የልቤ ሲደርስ እያልኩ ቀሪ ሁለቱ ክፍሎች ውስጥ ሰውየውን መፈለጌን ቀጠልኩ•••
ሰውየው ድራሹ የለም ። ግራ ተጋብቼ በቆምኩበት ሽንትቤቱን ድንገት ከፍቼበት የተበሳጨው ሰውዬ ቆየት እያለ ሲሳደብ ሰማሁት•••
እንዴ! እሄ ደሞ እያረፈ ነው እንዴ እሚሳደበው!
አልኩና ከውስጥ ዘግተህ አትቀመጥም ነበር ሰካራም! ብየው ወደ ቦታዬ ስመለስ የኮንትራት ደንበኛዬ (ዝም ብለህ ጠጣ ሲለኝ የነበረውን ሰው ) ቦታው ላይ አጣሁት።
የክፍሉን ዙርያ ገባ ቃኘት አደረኩ ። እክፍሉ ውስጥም የለም።
እየተደነባበርኩ እነመሲ ወዳሉበት ክፍል በር ስጠጋ •••
አይኔን ተጠራጠርኩት ! ሽንት ቤት ሰውየውን ፍለጋ ደርሼ እስክመጣ ከምኔው ሄዶ ከምኔው ተዋውቋቸው እና ተግባብቷቸው መሳሳቅ እንደጀመሩ ለማመን በሚከብድ ሁኔታ•••
እሱ ያወራል እነመሲ ይስቃሉ አሁንም ያወራል እነሱ ተያይተው ያሽካካሉ አፌን ከፍቼ ስመለከታቸው ቆየሁና እየሆነ ያለው ነገር ከመጠጡ ጋር ተደምሮ ትርምስምስ እንዳለብኝ ወደ ቦታዬ ተመለስኩ።
ትንሽ ቆየሁና እሱ አልመጣ ሲለኝ መኖር አለመኖራቸውን ላረጋግጥ ድጋሚ ሄድኩ።
ጭራሽ እሱና መሲ ተጣብቀው እየደነሱ ነው። ጀርባዋን ሰጥታው እላዩ ላይ ተጣብቃለች ወገቧን አቅፎ ማጅራቷ አከባቢ እንደመሳም እየቃጣው ለስለስ ባለው ሙዚቃ ይወዛወዛሉ ።
ልጅቷ ቦታዎ ላይ ተቀምጣ ትቁለጨለጫለች ።
ምናልባት አስጠማጇን እራሷን መሲን አጥምዶ ልጅቷን ሊያፋታት አስቦ ይሆን እንዴ?
ብዬ አሰብኩና የሆነ የደስታ ስሜት ውስጤን ሲነዝረው ታውቀኝ።
ሰውየውን ምን አድርጎት ነው? የሚለው ጥያቄ ስላልተመለሰልኝና ዝም ብለህ ጠጣ ከማለት ውጪ ምን እንዳደረገ? እና ምን ሊያደርግ እንዳሰበ በግልፅ ሊነግረኝ ፍቃደኛ ባለመሆኑ ግን ደስታዬ ብርዝ ሆነብኝ!!
በዳንሳችው መሀል ድንገት ተያየን ጠቀሰኝ እኔ ግን ግራ ተጋብቶ ያፈጠጠ እንጂ የሚጨፈን አይን አልነበረኝም እና ምኑም ላልገባኝ ጥቅሻው መልስ ነፈኩት ዝም ብዬው ከራሴ ጋር እያልጎመጎምኩ•••
ግራ አጋባኝ እኮ እሚገርም ሰው ነው እሄ ሰውዬ እያልኩ ወደ ቦታዩ ተመለስኩ ።
በተመለስኩ በደቂቃዎች ውስጥ ወደኔ በመምጣ
"ፈታ በል አቢቲ ዝም ብለህ አትጨናነቅ እኔ አንድ ነገር ላደርግ ካሰብኩ ውጤቱን እንጂ ጅማሬው ማውራት አልወድም! ለምን መሰለህ?••• መጀመራችንን እንጂ መጨረሳችንን የሚያውቀው ፈጣሪ ብቻ ስለሆነ በርግጥ አሁን ያሰብኩትን ነገር ፈጣሪ ሳይሆን ሰይጣን ነው አጨራረሱን የሚያሳምረው አየህ አንዳንዴ ጥሩ ነገር ለመስራት መጥፎ ነገር ውስጥ መግባቱ ግድ ይልሀል የስራህ ውጤት ከፊሉ የፈጣሪ ከፊሉ የሰይጣን ይሆናል ድብልቅ!
ነገር ግን ፈጣሪ ልብን ሰይጣን ስራን ይመረምራል ብዬ ስለማምን እሱ አያሳስበኝም ! ለማንኛውም ስጨርስ ሁሉንም ነገር እነግርሀለሁ አሁን አንተ አታስፈልገኝም ከሀያ ደቂቃ ቡሀላ በር ላይ ሁለት ባጃጅ እፈልጋለሁ ካንተ ጋር ካሁን ቡሀላ ምናልባት ነገ ካልሄድኩ እንገናኝ ይሆናል ብሎኝ ከኔ መልስ ሳይጠብቅ ጥሎኝ ሄደ ።
እንኳን ምን ለማለት እንደፈለገ ሊገባኝ ያለውን መልሼ ማስታወስ አልቻልኩም።
አንዳንድ ሰዎችን ትንሽ ግዜ አብረሀቸው በቆየህ ቁጥር ወይ በደንብ ታውቃቸዋለህ ወይ ጭራሽ እንደማታውቃቸው ይገባሀል የሚለው የጆሲ ጋደኛ ትዝ አለኝ።
ያለኝ አማራጭ መወዛገቤን ትቼ እስከመጨረሻው የሚሆነውን ነገር መመልከት ብቻ ሆነ።
ካስር ደቂቃ ቡሀላ ኮፍያዬን አዘቅዝቄ አንገቴን አቀርቅሬ ከጭፈራ ቤቱ በፍጥነት ወጣሁ ።
ከማውቃቸው በዛ ሰአት ስራ ላይ ይሆናሉ ብዬ ወዳሰበኳቸው ሁለት የባጃጅ ሹፌሮች ደወልኩና በር ላይ እንዲጠብቁአቸው ነግሬ እኔ ራቅ ብዬ ባጃጄ ውስጥ እንዳደፈጥኩ ስጠባበቅ ልክ ባለው ሰአት መሲ እና እሱ ተቃቅፈው ግራና ቀኝ እየትወዛወዙ እና እየተሳሳቁ ልጅቷም በሁኔታቸው አብራ ፈገግ እያለች ወደ ጎን ተደርድረው ከጭፈራ ቤቱ ሲቅወጡ ተመለከትኩ።
ባጃጆቹ ጋር እንደደረሱ ሰውየው ያቀፋትን መሲን ለቅቅ አድርጎ ወደ ልጅታ ተጠጋና አናገራት። ጨብጣው ከፉት ያለው ባጃጅ ውስጥ ጥልቅ አለች እሱና መሲ ሌላኛው ባጃጅ ውስጥ ገቡና ፊትና ኋላ ሆነው ተፈተለኩ እኔም ተከትያቸው ተፈተለኩ ።
በቅርብ እየተከተልኳቸው ልጅቷን ወደ ያዘው የባጃጅ ሹፌር ደወልኩ ። አነሳው።
ምን አለህ? ስለው•••
"ግቢ አድርሳት አለኝ ወደ ግቢ እየወሰድኳት ነው " አለኝ ። በረጅሙ ተነፈስኩ እና ጀግና አቦ አልኩት ግራ ያጋባኝን ሰው።
ወደ ግቢ የሚሄደው ባጃጅና እነመሲን የያዘው ባጃጅ የሚለያዩበት ቦታ ላይ ደረሱ ልጅቷን የያዘው በዲፖ በኩል ሽቅብ ወደ ሰይዶ ሲሸመጥጠው እነመሲን የያዘው ባጃጅ በፀሀይ ሆቴል በኩል ቁልቁል ቆሰቆሰው•••
ወደያዘው ክፍል ይዟት እየሄደ መሆኑን ብረዳም ልጅቷን ትቼ የመሲን መጨረሻ ለማየት ተከተልኳቸው ።
ደረሱ ። ከባጇጃ ወርደው የሰከረችውን መሲን ከመሸከም በማይተናነስ ሀኔታ ደግፎ ወደያዘው ክፍል አስገባት ።
ለሰው ያጠመድሽው እራስሽ ላይ ባርቆ ሊዘርርሽ ነው አይ መሲ !
እያልኩ ወደ ቤቴ ገብቼ ተዘረርኩ ጥዋት ሶስት ሰአት ላይ የቀሰቀሰኝ የስልኬ ጥሪ ነበር ሰውየው ነው በፍጥነት አንስቼው ሀሎ ስል•••
" ደና አደርክ አቢቲ ተመልሼ ወደመጣሁበት እየሄድኩ ነው ምናልባት ከስድስት ወር ቡሀላ እመጣ ይሆናል የማታውን ሙሉ ትያትር ለማየት እና ለመስማት እንደምትፈልግ አውቃለሁ ቴሌግራምህን ክፈት ሶስት መልእክቶች አሉህ በድምፅ! በፅሁፍና; በምስል! ቻው !!"ብቻ ብሎኝ ስልኩን ዘጋው•••
በፍጥነት ቴሌግራም አካውንቴን ስበረግደው ቀድሞ የታየኝ የመሲ ልብስ አልባ ገላ የሚያሳየው ቪድዬ ነበር ከስር የመሲን ስልክ ቁጥር አስቀምጦ
"አቢቲ በዚህ ቁጥሯ የተከፈተ ቴሌግራም አካውንቷ ላይ ቪድዬዋን ልከህ ካሁን ቡሀላ በሴት ተማሪዎች ሂወት መነገዷን እንድታቆም ያለ በለዚያ ግን ቪድዮዋን እንደምትለቀው ነግረህ አስጠንቅቃት!" ይላል በርግጌ ከፍራሼ ላይ ተነሳሁ።
ቪድዮውን ስከፍተው ••

ይቀጥላል...


@yederasiyanbet