Get Mystery Box with random crypto!

#የህይወት_ወርቃማ_ህጎች_2 #ያለ_ፍርሃት_በአዎንታዊነት_ተንቀሳቀስ የሆነ ነገር ውስጥ እንደገባህ | የደራሲያን ቤት 123@🇪🇹 የድሮ ሙዚቃዎች 📷📸

#የህይወት_ወርቃማ_ህጎች_2

#ያለ_ፍርሃት_በአዎንታዊነት_ተንቀሳቀስ
የሆነ ነገር ውስጥ እንደገባህ በተሰማህ ጊዜ ሁሉ… ተረጋጋ፣ አስብ፣ እቅድ አውጣና ያለ ፍርሃት በአዎንታዊነት ተንቀሳቀስ። የፍርሃት ወጥመድ ውስጥ መቆየትና አሉታዊ ነገሮችን ማሰብ ብቻ መፍትሄ አይሆንም፨ ስለዚህ, በእያንዳንዱ አሉታዊ ሁኔታ ውስጥ አዎንታዊ ጎን መፈለግ ተማር፨

#በረከቶችህን_ቁጠር_መልካም_አድርግ
በውጤቱ ላይ ሳታተኩር መልካም መስራትህን ቀጥል፤ ሁልጊዜም የዘራነውን የምናጭድ በመሆኑ በተቻለ መጠን መልካም ነገሮችን ስራ፨ በተጨማሪም ያለፈው ጊዜ ታሪክ ነው፣ መጪው ጊዜ ምስጢር ነው፣ ዛሬ ደግሞ ስጦታ ነው። ስለዚህ ዛሬ ላይ ትኩረት አድርግ፨

#ፈገግ_ማለትህን_ቀጥል
አንድ ቀላል ፈገግታ የአንድን ሰው መጥፎ ቀን ወደ ጥሩ ቀን ሊለውጠው ይችላል። ስለዚህ፣ ፈገግ ማለትህን ቀጥል ይህም የአንተን ግንዛቤ ይለውጣል፨

#ሲያስፈልግ_ብቻ_ይቅርታ_ጠይቅ
አሁን አሁን <ይቅርታ> እና <አዝናለሁ> የሚሉት ቃላት በሚጠቀሙባቸው በአብዛኛው ሰዎች ከቃላት ባለፈ ብዙም ትርጉም የላቸውም፨ ይቅርታ መጠየቅ መልካም ቢሆንም፥ ከመጠን በላይ ይቅርታ መጠየቅ ግን ሰዎች የሚፈለገውን አክብሮት እንዳይሰጡህ ያደርጋል፨ ስለዚህ ይቅርታ ስትጠይቅ አስፈላጊ በሚሆንበት ጊዜ ብቻ ይሁን።

#ወርቃማ_ሕጎች መጽሐፍ