2023-05-17 13:54:44
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ
አሜን
“ሕያውን ከሙታን መካከል ስለ ምን ትፈልጋላችሁ፤ ተነሥቶአል እንጂ በዚኽ የለም"
ሉቃ 24፥5
"በበጎ ሥራ ሁሉ ፍሬ እያፈራችሁ በእግዚአብሔርም እውቀት እያደጋችሁ፥
ለጌታ እንደሚገባ ትመላለሱ ዘንድ እንለምናለን"
ቆላስይስ 1፥10-11
ቀናችንን በጸሎት እንጀምር
ክፍል ፭
✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥
ስለ ጋብቻ
✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥
የኦርቶዶክሳዊ ጋብቻ ዋና ግብ
➯ እስከ አሁን ከውድቀት በፊት ከነበረው የሰው ኹኔታ አንሥተን ከትንሣኤ ዘጉባኤ በኋላ እስካለው ጊዜ ድረስ ከጋብቻ አንጻር በጣም በጥቂቱ ተመልክተናል፤ ስለዚህስ ከዚህ ተነሥተን የጋብቻ ዋና ግቡ ምንድን ነው ልንል እንችላለን?
➯ ብዙዎቻችን ዘር ለመቀጠል፣ ለመረዳዳትና ከዝሙት ለመጠበቅ ተብለው ስለ ሦስት የጋብቻ ዓላማዎች ሰምተናል፤ አንብበናልም፤ ጋብቻ ከተሰጠበት ዋና ዓላማ አንጻር ስናያቸው ግን እነዚህ ያንሱብናል፤ ጋብቻ የተሰጠን ወደ ጥንተ ተፈጥሮአችን እንድንመለስበት ከዚያም በላይ እግዚአብሔርን መስለን እንድናድግበት የድኅነት መንገድ ኾኖ ነውና ጥንቱን በገነት ውስጥ መባዛት አልነበረም፤ ከትንሣኤ ዘጉባኤ በኋላም በመንግሥተ ሰማያት “ብዙ ተባዙ” የለም፡፡
➯ ዳግመኛም፥ ዘር መቀጠል የጋብቻ ዋና ዓላማ ቢኾን ኖሮ በዙሪያችን እንኳን የምናውቃቸው ብዙ መካን ክርስቲያኖች አሉ፤ አንዲት ሴት የማረጥ ጊዜ ላይ ስትደርስ በተአምር ካልኾነ በቀር ብዙውን ጊዜ አትወልድም፤ ምናልባትም ባል ወይም ሚስት በተለያየ የጤና ችግር ምክንያት ልጅ መውለድ ላይችሉ ይችላሉ፡፡
➯ በሌላ መልኩ ደግሞ በዚህ ዓለም ኑሮ መረዳዳት የጋብቻ ተቀዳሚ ዓላማ ቢኾን “ድኾች” ክርስቲያኖች ምንኛ ምስኪናን ናቸው? አንድ ለአንድ ተወስኖ ሩካቤ መፈጸም የጋብቻ ተቀዳሚ ዓላማ ቢኾን ኖሮስ ከአንዳንድ ክርስቲያን ካልኾኑት ብቻ ሳይኾን ደበኔ ከተባለው ርግብ መሰል ወፍ ምን ብልጫ አለን?
➯ ጋብቻችን በርግጥም ኦርቶዶክሳዊ ነው የሚባለው እነዚህ ኹሉ በዋናው ዓላማ ማለትም ጽድቅን በመፈጸም ሥር ሲኾኑ ነው፤ ንዑድ ክቡር የሚኾን ጳውሎስ
“እንግዲህ የአይሁዳዊ ብልጫው ምንድር ነው?” ይላል።
ሮሜ 3፥1
➯ ይህም ከያዝነው አሳብ ጋር አስተሳስረን ስናየው “ክርስቲያን የመኾናችን ብልጫው ምንድን ነው? ክርስቲያን ኾነን የማግባታችንስ? ትዳራችን እንደዚህ ዓለም ሰዎች ልጅ መውለድ ከኾነ ምንድን ነው? ዘማውያንስ እንኳን ይወልዱ የለምን? ደግሞስ ልጅ መውለድ የትዳር ተቀዳሚ ዓላማ የምናደርግ ከኾነ በተቀደሰ መኝታ ሳይቀር ልጅ ካልተወለደ ሩካቤ ማድረግን እንደ ኃጢአት እንደሚቈጥሩት እንደነ አውግስጢኖስ ትምህርት ማስተማራችን አይደለምን? ልጅ ያልተሰጣቸው ባለትዳሮችስ የትዳርን ዓላማ አይኖሩም ማለት ነውን? ስለ ሰዎች የምናገረውስ ለምንድን ነው? እንስሳት ስለሚወልዱ የትዳርን ዓላማ ተግብረው ይኖራሉ ሊባል ነውን? ከእንስሳት ምንድን ነው ብልጫችን? ከአሕዛብ ከመናፍቃን ምንድን ነው ብልጫችን?” ማለት ነው፤ ይልቅስ ቅድስት ቤተክርስቲያናችን፥ ጋብቻን በቅዱስ ሥጋውና በክቡር ደሙ አትማ የምትመሠርትበት ዋና ምክንያት፥ ተጋቢዎች ጋብቻቸው ድኅነታቸውን እንዲፈጽሙበት፣ አንድነታቸውን ወደ መንፈሳዊ አንድነት እንዲያሳድጉበት፣ ኦርቶዶክሳዊ ዘርንም እንዲቀጥሉበት ለማድረግ እንደ ኾነ መረዳት ያስፈልጋል፤ በዚህ ፍኖት እንድንጓዝ የአባት እናቶቻችን አምላክ ይርዳን።
ይቀጥላል.....
"የሚሰማኝ ግን በእርጋታ ይቀመጣል ከመከራም ሥጋት ያርፋል"
ምሳ 1፥33
" #ወአንቢበክሙ አንትሙ #ለዘኢያንበበ አይድኡ
➘ #እናንተ_አንብባችሁ_ላላነበበው_ንገሩ"
አዘጋጅ
ዲ/ን ባሮክ
ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ፤ እኔም ለእናንተ ከአዘጋጀው በኃዋላ የተጣልሁ እንዳልሆን ስለ እኔ ጸልዩ
"ልብህን በእርጋታ አኑረው፤ የሁሉም መጨረሻ እና የሁሉም አገልጋይ ለመሆን በጣም ትጋ ለከንቱ ንግግር ዘገምተኛና ሰነፍ ሁን፤ ነገር ግን የቅዱሳት መጻህፍትን ቃል በማወቅ በመስማት ድኅነትን የሚሰጡ ናቸውና ብልህ ሁን"
ታላቁ ባስልዮስ ዘቂሳሪያ
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ይቆየን
───────────
Channel
https://telegram.me/Tewahedo12
FB Like Page (የፌስቡክ ፔጅ)
http://facebook.com/Tewahedo12
YouTube Subscribe (ሰብስክራይብ)
https://www.youtube.com/channel/UCvYxUdv1D-5juH_P6iE7XXw
───────────
687 views✞ ባሮክ ✞, 10:54