Get Mystery Box with random crypto!

✞ ተዋሕዶ ✞ 🇹 🇪 🇼 🇦 🇭 🇪 🇩 🇴

የቴሌግራም ቻናል አርማ tewahedo12 — ✞ ተዋሕዶ ✞ 🇹 🇪 🇼 🇦 🇭 🇪 🇩 🇴
የቴሌግራም ቻናል አርማ tewahedo12 — ✞ ተዋሕዶ ✞ 🇹 🇪 🇼 🇦 🇭 🇪 🇩 🇴
የሰርጥ አድራሻ: @tewahedo12
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 10.16K
የሰርጥ መግለጫ

"ሥርዓትን እማር ዘንድ ያስጨነከኝ መልካም ሆነልኝ"
መዝ 118 (119) ፥ 71
ይህ ቻናል የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ዶግማንና ቀኖናን ትውፊትን እንዲሁም አስተምሮን የጠበቁ የተለያዩ የሚያስተምሩ ነገሮች ይለቀቁበታ፡፡ ግሩፑ
http://t.me/OrthodoxTewahedo12
ይህ Channel #ሐምሌ 26/2010 ዓ.ም አ/ጀመረ
ለአስተያየት 📥 ➩ @Tewahedo12_bot

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 10

2023-04-29 16:07:05 https://telegra.ph/ፍቅር-03-28
410 views✞ ባሮክ ✞, 13:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-29 11:57:36

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ
           አሜን


“ሕያውን ከሙታን መካከል ስለ ምን ትፈልጋላችሁ፤ ተነሥቶአል እንጂ በዚኽ የለም"
ሉቃ 24፥5

"በበጎ ሥራ ሁሉ ፍሬ እያፈራችሁ በእግዚአብሔርም እውቀት እያደጋችሁ፤ ለጌታ እንደሚገባ ትመላለሱ ዘንድ እንለምናለን"
ቆላስይስ 1፥10-11

“ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን” (ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ ተነሣ)
“በዐቢይ ኀይል ወሥልጣን” (በገናና ኀይልና ሥልጣን)
“ዐሠሮ ለሰይጣን” (ሰይጣንን ዐሰረው)
“አግአዞ ለአዳም” (አዳምን ነጻ አወጣው)
“ሰላም” (ፍቅር አንድነት ሆነ)
“እምይእዜሰ” (ከእንግዲህስ)
“ኮነ” (ሆነ)
“ፍሥሐ ወሰላም” (ደስታ ሰላም)

       ✥••••●◉ ✞ ◉●••••✥
            አቤቱ ይቅር በለን
       ✥••••●◉ ✞ ◉●••••✥

❖ ቤተ መቅደስ በሌሊት ተገኝተን ሥርዓተ ቅዳሴውን ከመከታተል ይልቅ ፤ እንቅልፍ የመረጥንበትን እነዚያን ዘመናት ሳስብ ነፍሴ በኀዘን ውስጥ ወደቀችብኝ፤ ዛሬ በጽኑዕ ብንፈልግ ብንናፍቅም መቅደስ ገብተን ፤ ያንን ሰማያዊ ሥርዓት እንከታተል ዘንድ የማንችልበት ዘመን ላይ ቆመናልና አቤቱ ይቅር በለን።

"ከቤተ ክርስቲያን አትራቅ፣ ጠበል እምነቱን ተጠቀም፣ መስቀሉን ተሳለም፣ ጸሎትንና ስግደትን ለማድረግ ትጋ" የሚለውን ምክር በሰላሙ ዘመን ሰማነው፤ እንዳንፈጽመው የእኛ ብለን ቅድሚያ የሰጠናቸው ጉዳዮቻችን ፣ ቸልተኝነታችንና ለነገ ማለታችን አዘናግተው አሰሩን።

❖ ዛሬ እግሮቻችን ቢፋጠኑ፣ ልቡናችን ቢነቃቃም እንኳን፤ ወደ መቅደስህ መገስገስ ለጸሎት መቆም፣ መስቀልን መሳለም፤ የማንችልበት ዘመን ላይ ደርሰናልና አቤቱ ይቅር በለን።

"ንስሓ ግቡ የሚለው የቅድስቲቱ ቤተ ክርስቲያን ጥሪ፤ ጆሮዎቻችን ሰምተውት አልፎም ለምደውት ነበር፤ ቅዱስ ጳውሎስ ስለ ክርስቶስ "እርሱም የአካሉ ማለት የቤተ ክርስቲያን ራስ ነው"  እንዳለ ጥሪው በሙሽራይቱ ቤተ ክርስቲያን በኩል የቀረበ የመድኃኔ ዓለም ጥሪ ነበር፤ በሰላሙ ዘመን ይህን ጥሪ ቸል አልነው ቦታም አልሰጠነው።
ቆላ 1፥18

❖ አሁን ደግሞ ወቅቱ ከቤት የማይወጣበት እየሆነ ነውና፤ ብንፈልግም ንስሓ የማንገባበት "እግዚአብሔር ይፍታህ" ለመባል ካህኑን በአካል የማናገኝበት ዘመን ላይ ቆመናልና አቤቱ ይቅር በለን"

❖ ለምድራዊው ማእድ ቀን ከሌሊት እንደክማለን፤ በሰላሙ ዘመን ከ350 ቀናት በላይ በየዕለቱ እየተሠዋ "የዘላለም ሕይወት የሚያሰጠውን የሕይወት ማእድ ተቀበሉ" ስንባል፤ "ገና ነኝ፣ አልበቃሁም፣ ወጣትነቴ ይለፍ" ብለን ብዙ ምክንያት አቀረብን፤ ዛሬ ደግሞ ይህን ሰማያዊ መሥዋዕት ለምነንም ላናገኝ የምንችልበት ፤ ድርገት ወርደው "እስመ ኃያል አንተ እኩት ወስቡሕ" ብለን የማናዜምበት ዘመን ላይ ቆመናልና አቤቱ ይቅር በለን።

❖ "አሟሟቴን አሳምርልኝ" የሚለው የእናቶች ጸሎት፤ ትርጉሙና ምሥጢሩ አሁን የተገለጠ ይመስላል፤ በደጉ ዘመን በካህን መፈታት ፤ በቤተ ዘመድ ልቅሶ በጎረቤት ዕንባ መቀበር ፤ አየር የመተንፈስ ያህል የተለመደና የሚደንቅ አልነበረም።

❖ ዛሬ ግን በጸሎተ ፍትሐት ሳያልፉ፤ ያለ ቀባሪ መቀበር ግድ የሆነበት ዘመን ላይ ደርሰናልና አቤቱ ይቅር በለን።

"ነጋሢ ግሩም አጽናፈ ዓለም ዘኢይጸውሮ ወኢያገምሮ፤ መንክር ግብሩ ዘኢትይፌጸም በተናግሮ ወነኪር ነገሩ ዘኢየኃልቅ በአንክሮ፤ ያፈቅሮ ለዘያፈቅሮ ወይሰምዖ ለዘያሠምሮ፤ ሥልጣኑ መላኢ ወመለኮቱ ይእኅዝ ኲሎ ወኲሎ ይቀኒ"

"ዓለም የማይወስነው ግሩም ንጉሥ የዓለም ዳርቻ መሸከም የማይችለው፤ አስደናቂ ሥራው በመናገር የማይፈጸም፤ ልዩ ምሥጢሩም በአድናቆት የማይፈጸም ነው፤ የሚወደውን ይወደዋል ፤ ደስ የሚያሰኘውንም ይሰማዋል፤ ሥልጣኑ ምሉዕ መለኮቱም ገዥ ነው፤ በሥልጣኑም ሁሉን ይይዛል፤ ሁሉንም ይገዛል" የተባለልህ መድኃኔ ዓለም ሆይ! ደብረ ምሕረት (የምሕረት ተራራ)፤ ባሕረ ትዕግሥት (የትዕግሥት ባሕር) ነህና ስለ ቸርነትህ ማረኝ ኃጢአተኛ ባሪያህን ይቅር በለኝ።

"ንጽሕት ሆይ ከሥጋና ከነፍሴ ርኩሰት ንጹሕ አድርጊኝ የረከሰውን ለማንፃት ልጅሽ ይችላል ዳዊት በመዝሙር እንደተናገረ እንዲህ ሲል "በሄሶጵ እርጨኝ እጠበኝ ከበረድም ይልቅ እነፃለሁ"
መዝ 51፣7

❖"ከነፍስና ከሥጋዬም ቁስል ፈውሺኝ፤ የባለ መድኃኒት እናት ሆይ የታመመውንና የቆሰለውን ለመፈወስ ልጅሽ ይችላል፡፡

❖ ዳዊት በመዝሙር እንደተናገረ እንዲህ ሲል
"ማረኝ አቤቱ ድውይ ነኝና ፈውሰኝ አቤቱ አጥንቶቼ ታውከዋልና የሠራሁት ኃጢአቴንም ባሰብሁት ጊዜ ነፍሴ ደነገጠች ልቤም ታወከች"
መዝ 6፥2፣3
አርጋኖን ዘቀዳሚት

"የመጨረሻው ፍርድ ቀን ቀርቧል፤ አሁን ሆነም አልሆነም፤ ለአንተ የዓለም መጨረሻ ሞትህ ነውና፤ ሁልጊዜም ቢሆን ተዘጋጅተህ ኑር"

"የሚሰማኝ ግን በእርጋታ ይቀመጣል ከመከራም ሥጋት ያርፋል"
ምሳ 1፥33

" #ወአንቢበክሙ አንትሙ #ለዘኢያንበበ አይድኡ
➘ #እናንተ_አንብባችሁ_ላላነበበው_ንገሩ"

ምንጭ
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ



ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ፤ እኔም ለእናንተ ከአዘጋጀው በኃዋላ በድካሜ ብዛት ሳይገባኝና ሳይገባኝ በምጽፈው ድርሳንወ ገድላት መጽሐፍት ላይ የቃላት (የፊደል) ሕፀፅ ቢገኝ በጎደለው እየሞላችሁ በጠመመው እያቃናችሁ አንብቡ በረከት ተካፈሉ እላለሁ ከምንም ጊዜ በላይ ለሀገራችንና ለዓለም ሰላም እንዲሁም ለደካማው ወንድማችሁ እንድበረታ (የተጣልሁ) እንዳልሆን ስለ እኔ ጸልዩ

"ልብህን በእርጋታ አኑረው፤ የሁሉም መጨረሻ እና የሁሉም አገልጋይ ለመሆን በጣም ትጋ ለከንቱ ንግግር ዘገምተኛና ሰነፍ ሁን፤ ነገር ግን የቅዱሳት መጻህፍትን ቃል በማወቅ በመስማት ድኅነትን የሚሰጡ ናቸውና ብልህ ሁን"
ታላቁ ባስልዮስ ዘቂሳሪያ

               ወስብሐት ለእግዚአብሔር
                              ይቆየን 

───────────
                    Channel
    https://telegram.me/Tewahedo12

        FB Like Page (የፌስቡክ ፔጅ)
  http://facebook.com/Tewahedo12  

        YouTube Subscribe (ሰብስክራይብ)
https://www.youtube.com/channel/UCvYxUdv1D-5juH_P6iE7XXw
 ───────────
512 views✞ ባሮክ ✞, 08:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-29 06:16:43               ✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥
"የሚሰማኝ ግን በእርጋታ ይቀመጣል ከመከራም ሥጋት ያርፋል"
ምሳ 1፥33
                        #ስንክሳር          
             ዘሚያዚያ #ሃያ አንድ (፳፩)        
              ✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥
404 views✞ ባሮክ ✞, edited  03:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-29 06:14:51 ✥•••••••••••••••••••●◉ ✞ ◉●•••••••••••••••••••✥

"ልብህን በእርጋታ አኑረው፤ የሁሉም መጨረሻ እና የሁሉም አገልጋይ ለመሆን በጣም ትጋ ለከንቱ ንግግር ዘገምተኛና ሰነፍ ሁን፤ ነገር ግን የቅዱሳት መጻህፍትን ቃል በማወቅ በመስማት ድኅነትን የሚሰጡ ናቸውና ብልህ ሁን"
ታላቁ ባስልዮስ ዘቂሳሪያ

ሚያዚያ ወር 
#በጠዋትና በማታ #የሚነበቡ የእየለታት #የመጽሐፍ ቅዱስ #ክፍሎች

#ሚያዚያ


“ስለዚህ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ ሰው ሁሉ ለመስማት የፈጠነ ለመናገርም የዘገየ ለቍጣም የዘገየ ይሁን”
ያዕቆብ 1፥19

                መልካም ንባብ 

✥•••••••••••••••••••●◉ ✞ ◉●•••••••••••••••••••✥

Share   
           🇹 🇪  🇼 🇦  🇭 🇪 🇩 🇴
    ✥••┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈••✥

              
@Tewahedo12

      
@OrthodoxTewahedo12

   ✥••┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈••✥
423 views✞ ባሮክ ✞, 03:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-29 06:14:35 https://telegra.ph/ስንክሳር-ዘወርኀ-ሚያዝያ-04-25
422 views✞ ባሮክ ✞, 03:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-28 14:45:54 https://telegra.ph/ቅዱሳን-ሐዋርያት-06-15
725 views✞ ባሮክ ✞, 11:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-28 07:33:38
" ጌታዬና መድሃኒቴ ኢየሱስ ክርስቶስ የደረሰበትን ጉስቁልና ሊተካከል የሚችል ጉስቁልና እንደምን ያለ ነው? ቀላያት ፊቱን በተመለከቱ ጊዜ የሚንቀጠቀጡለት ፀሐይ ብርሃኗን የምትከለክልለት ጨረቃ የምታለቅስለት ከዋክብት የሚረግፉለት ክፉዎች አይሁድ ተፉበት እጃቸውን አክርረው መቱት ከስድብ ሁሉ የከፋ ስድብ ሰደቡት፤ ስድባቸው እንዲሁ የቃላት ብቻ አልነበረምና ምራቅና ቡጢም አለበት እንጂ ይህ ብቻ አይደለም  ክርስቶስ ሆይ በጥፊ የመታህ ማን ነው? ትንቢት ተናገርልን የሚል ስላቅም አለበትና፤ ጌታዬና ንጉሴ መከራ ያልደረሰበት አካል አልነበረውም፤ ጭንቅላቱ ላይ የእሾኽ አክሊል ደፉበት ፊቱን በጥፊ መቱት ትከሻውን መስቀል አሸከሙት እጁን በችንካር ቸነከሩት እግሩን በምስማር ቸነከሩት አፉን ኮምጣጤ አጠጡት መላ አካልቱን በጅራፍ ገረፉት ወዮ! እንዲህ ያለ መውደድ እንደምን ያለ ፍቅር ነው"

❖  "አቤቱ ነፍሴን ከሲኦል አወጣሃት ወደ ጕድጓድም እንዳልወርድ አዳንኸኝ"
መዝ 30፥3

ምንጭ
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
819 views✞ ባሮክ ✞, 04:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-27 19:36:42               ✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥
"የሚሰማኝ ግን በእርጋታ ይቀመጣል ከመከራም ሥጋት ያርፋል"
ምሳ 1፥33
                        #ስንክሳር          
             ዘሚያዚያ #ሃያ (፳)        
              ✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥
656 views✞ ባሮክ ✞, edited  16:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-27 19:35:05 ✥•••••••••••••••••••●◉ ✞ ◉●•••••••••••••••••••✥

"ልብህን በእርጋታ አኑረው፤ የሁሉም መጨረሻ እና የሁሉም አገልጋይ ለመሆን በጣም ትጋ ለከንቱ ንግግር ዘገምተኛና ሰነፍ ሁን፤ ነገር ግን የቅዱሳት መጻህፍትን ቃል በማወቅ በመስማት ድኅነትን የሚሰጡ ናቸውና ብልህ ሁን"
ታላቁ ባስልዮስ ዘቂሳሪያ

ሚያዚያ ወር 
#በጠዋትና በማታ #የሚነበቡ የእየለታት #የመጽሐፍ ቅዱስ #ክፍሎች

#ሚያዚያ


“ስለዚህ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ ሰው ሁሉ ለመስማት የፈጠነ ለመናገርም የዘገየ ለቍጣም የዘገየ ይሁን”
ያዕቆብ 1፥19

                መልካም ንባብ 

✥•••••••••••••••••••●◉ ✞ ◉●•••••••••••••••••••✥

Share   
           🇹 🇪  🇼 🇦  🇭 🇪 🇩 🇴
    ✥••┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈••✥

              
@Tewahedo12

      
@OrthodoxTewahedo12

   ✥••┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈••✥
711 views✞ ባሮክ ✞, 16:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-27 19:34:49 https://telegra.ph/ስንክሳር-ዘወርኀ-ሚያዝያ-04-25-3
603 views✞ ባሮክ ✞, 16:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ