Get Mystery Box with random crypto!

ትምህርት በቤቴ🔝

የቴሌግራም ቻናል አርማ temhert_bebete — ትምህርት በቤቴ🔝
የቴሌግራም ቻናል አርማ temhert_bebete — ትምህርት በቤቴ🔝
የሰርጥ አድራሻ: @temhert_bebete
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.20K
የሰርጥ መግለጫ

A channel created for sharing
🔺study tips,
🔺short notes,
🔺tutorials,
🔺educational news,
🔺life tips and some motivational quotes ...
For comment @Tmhert_bebete_info_bot
Buy ads: https://telega.io/c/temhert_bebete

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 16

2022-08-30 08:13:33 አሸናፊ ነህ!

ሰው ምንድነው ቢሉ ደጋግሞ ያሰበውን ነው ይባላል፤ ስለዚህ ለማን ብለህ ነው አብዝተህ የጎደለህን ከሰው ያሳነሰህን የምታስበው?!

በቃ ተዓምር መስራት እንደምትችል ባንተ ምክንያት መጀመሪያ የራስህ ከዛ የቤተሰቦችህ ህይወት እንደሚቀየር አስብ እሱን እውነት ለማድረግ የምትችለው ጥግ ድረስ ጣር የቀረውን ለፈጣሪ ተወው!

@temhert_bebete
@temhert_bebete
5.7K viewsedited  05:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 16:56:40 የወልድያ ዩኒቨርሲቲ ባደረባቸው በስጋት ምክንያት ግቢያቸውን ለቀው የወጡ ተማሪዎችን በሚመለከት ውሳኔ ወሳለፈ።

ዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች በ22/12/2014 ዓ.ም ባደረባቸው ስጋት ምክንያት የተነሳ ግቢውን ለቀው መውጣታቸውን ገልጿል።

በዚህ የሚከተሉትን ውሳኔዎች አስተላልፏል፡፡

1ኛ. የመደበኛ መርሀ ግብር ተማሪዎች በሙሉ ወደ ዩኒቨርሲቲው መመለሻ ጊዜ #በቀጣይ_ዓመት ጥሪ በሚደረግበት ጊዜ ይሆናል።

2ኛ. የክረምት መርሀ ግብር ተማሪዎች በሙሉ የተጀመረውን ትምህርትና ፈተና ለማጠናቀቅ ወደ ዩኒቨርሲቲው መመለሻ ጊዜ መስከረም 03/2015 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የትምህርት በቤቴ ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ!

https://t.me/temhert_bebete
https://t.me/temhert_bebete
4.2K viewsedited  13:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 12:24:01
የአማራ ክልል የ2014 ዓ.ም. የ8ኛ ክፍል መቁረጫ ነጥብ ይፋ ሆኗል።በዚህ መሠረት በ2014 ዓ.ም የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ማለፊያ ውጤት ለወንዶች 39%፣ ለሴቶች ደግሞ 38% እንዲሁም ለአካል ጉዳተኞች 37% እንዲሆን ተወስኗል።

፨ዝርዝሩን ከፎቶው ይመልከቱ

ምንጭ፡የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ትምህርት ቢሮ

@Temhert_Minister
@Temhert_Minister
5.4K views09:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 09:52:15
ለ2015 የትምህርት ዘመን የተማሪ ምዝገባ ከነሐሴ 23-ፃጉሜ 4/2014ዓ.ም ድረስ ባሉት ቀናት ይካሄዳል የአማራ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ

ልጆችን ማስተማር የዜግነት ግዴታን መወጣት መሆኑን በመረዳት ዕድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ህፃናትን ወደ ትምህርት ቤት ልከው ዛሬውኑ ያስመዝግቡ ይላል ትምህርት ቢሮው።

መረጃው የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ነው

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የትምህርት በቤቴ ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ!

https://t.me/temhert_bebete
https://t.me/temhert_bebete
5.9K views06:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 08:25:19 የምን መፍዘዝ ነው!

በህይወትህ ስለሆነው፣ እየሆነ ስላለው ወደ ፊትም ለሚሆነው ሁሉ ፈጣሪ የተመሰገነ ይሁን! ቀን ቢያስጎነብሰን ቀና የሚያደርገን በፈጣሪ ላይ ያለን እምነት ነው። አሁን ከአልጋህ ተነስ የምን መፍዘዝ ነው!

@temhert_bebete
@temhert_bebete
5.9K viewsedited  05:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 20:28:37 አዲስ የ motivation ቻናል ከፍተናል የምትፈልጉትን ሕይወት ማሳካት ከፈለጋችሁ ተቀላቀሉን

https://t.me/daily_inspiree
6.9K views17:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 12:02:12
የተማሪዎች መማሪያ ደብተር እስከ 80 ብር እየተሸጠ ነው ተባለ

በአዲስ አበባ ራዲካል ተብሎ የሚጠራው ባለሃምሳ ገፅ አንድ ደብተር እስከ 80 ብር የሚሸጥ ሲሆን፣ በክፍለ አገር ከተሞች መጠነኛ ቅናሽ እንዳለው አዲስ ማለዳ ዘግባለች። 32 ገፅ ያላቸው መማሪያ ደብተሮችም እንደጥራት ደረጃቸው ከ30 እስከ 60 ብር መሸጫ ዋጋቸው ሆኗል።

ባለፈው ዓመት የትምህርት ዘመን መጀመሪያ እስከ 40 ብር ይሸጥ የነበረ ደብተር ነው በዚህ ዓመት ከእጥፍ በላይ የጨመረው ተብሏል። በዚህም የተማሪ ቤተሰቦች በተማሪዎች መማሪያ ቁሳቁስ አላግባብ የዋጋ መወደድ ቅሬታቸውን እየገለፁ ይገኛሉ።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የትምህርት በቤቴ ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ!

https://t.me/temhert_bebete
https://t.me/temhert_bebete
9.8K views09:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 07:40:18 አንዳንዴ የውስጥህን ድምፅ የሚያፍኑ ውስጫዊ ጫጫታዎች ይበዛሉ፤ የምትፈልገውን እንዳትሆን በራስህ መንገድ እንዳትጓዝ የሚያደርጉ ጫናዎች ይበረታሉ፤ ፅናት ማለት ህልምህን ለመኖር የሚከፈለውን መስዋዕትነት ሁሉ ከፍሎ ሳያቆሙ መቀጠል ነው።

ያማረ ቀን ይሁንላችሁ

@temhert_bebete
@temhert_bebete
8.9K viewsedited  04:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 15:56:09 በ2014 በጀት ዓመት የተለያዩ የህግ ጥሰት ፈፅመዋል ከተባሉ የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት መካከል 222 ያህሉ ተማሪዎቻቸውንም እንዲበትኑ ውሳኔ ተላለፎባቸዋል ተባለ፡፡

በትምህርት ተቋማቱ ይማሩ የነበሩ በሺዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎች እጣ ፋንታ ምን ይሆን?

ሸገር ሬድዮ የትምህርትና ስልጠና ባለስልጣንን አነጋግሯል የድምፅ ፋይሉን ያዳምጡ

#የትምህርትና_ስልጠና_ባለስልጣን

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የትምህርት በቤቴ ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ!

https://t.me/temhert_bebete
https://t.me/temhert_bebete
9.9K views12:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 06:30:47
የደቡብ ክልል እና የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የ8ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ይፋ መሆኑ ዛሬ ተገልጿል።

በሁለቱ ክልሎች ውሳኔ መሰረት የማለፊያ ነጥብ ፦

ለወንዶች 41፣
ለሴቶች 40 እና
ለአይነ ስውራን 39 ሆኖ ተወስኗል።

በዚህ መሰረት ፦ በ2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በሁለቱም ክልሎች ለፈተና ከተቀመጡ ከ257 ሺህ በላይ ተማሪዎች 187 ሺህ 500 በላይ ተማሪዎች ወደቀጣይ ክፍል የሚያሳልፋቸውን ውጤት አምጥተዋል።

ለፈተና ከተቀመጠው አጠቃላይ ተማሪ ቁጥር ሲታይ ከ73 በመቶ በላይ ተማሪዎች አልፈዋል።

በተለየ መልኩ ከጸጥታ ጋር በተያያዘ በአሉታዊ ጫና ውስጥ ሆነው የተማሩና ለፈተና የተቀመጡ የደራሼ ልዩ ወረዳ ተማሪዎችን ውጤት በተለየ መልኩ ታይቷታ።

በዚህም መሰረት ፦

ለወንዶች 39፣
ለሴቶች 38 እና
ለአይነ ስውራን 37 ሆኖ ተወስኗል።

የሁለቱ ክልሎች ተማሪዎች ውጤታቸውን ከነገ ጀምሮ መውሰድ ይችላሉ ተብሏል።

የደራሼ ልዩ ወረዳ ተማሪዎች ግን ውጤታቸው በእጅ የሚሰራ በመሆኑ የ1 ሳምንት ጊዜ ዘግይቶ ይደርሳል እስከዛው በትዕግስት እንዲጠባበቁ መልዕክት ተላልፏል።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የትምህርት በቤቴ ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ!

https://t.me/temhert_bebete
https://t.me/temhert_bebete
9.8K views03:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ