Get Mystery Box with random crypto!

ትምህርት በቤቴ🔝

የቴሌግራም ቻናል አርማ temhert_bebete — ትምህርት በቤቴ🔝
የቴሌግራም ቻናል አርማ temhert_bebete — ትምህርት በቤቴ🔝
የሰርጥ አድራሻ: @temhert_bebete
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.20K
የሰርጥ መግለጫ

A channel created for sharing
🔺study tips,
🔺short notes,
🔺tutorials,
🔺educational news,
🔺life tips and some motivational quotes ...
For comment @Tmhert_bebete_info_bot
Buy ads: https://telega.io/c/temhert_bebete

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 15

2022-09-02 06:58:01   የሚጨመሩና የሚቀነሱ የትምህርት አይነቶች ይኖራሉ በ አዲሱ የሥርዓተ-ትምህርት

በአዲሱ  የሥርዓተ-ትምህርት ትግበራ  ከአንደኛ ደረጃ እስከ መሰናዶ ትምህርት ቤት ያሉ ትምህርቶች ላይ የሚቀነሱ እና እንደ አዲስ የሚጨመሩ የትምህርት አይነቶች መኖራቸው ተገለጸ።የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ምክትል  ኃላፊ አድማሱ ደቻሳ እንደገለጹት አዲሱ ሥርዓተ-ትምህርት በ2015 የትምህርት ዘመን በከፊል በተወሰኑ በቅድመ አንደኛ ደረጃ እና በአጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ  ትምህርት ቤቶች ላይ ይተገበራል።

በአዲሱ  የሥርዓተ-ትምህርት ትግበራ  ከአንደኛ ደረጃ እስከ መሰናዶ ትምህርት ቤት ያሉ ትምህርቶች ላይ የሚቀነሱ እና እንደ አዲስ የሚጨመሩ የትምህርት አይነቶች መኖራቸውን ተናግረዋል።በ7ኛ እና 8ኛ ክፍሎች ላይ ከዚህ በፊት ሦስቱ ሳይንሶች ተብለው ይሰጡ የነበሩት (ኬሚስትሪ፣ ፊዚክስና ባዮሎጂ) አሁን  አጠቃላይ ሳይንስ ተብለው በአንድ ይሰጣሉ ብለዋል።

  በ9ኛ እና 10ኛ ክፍል የኢኮኖሚክስ ትምህርት አሁን ላይ “ፐርፎርም ኤንድ ቪዥዋል አርት” በሚል መተካቱንም ጠቁመዋል።በተመሳሳይ በ11ኛ እና 12ኛ ክፍል በድጋሚ ከሚሰጡ የትምህርት አይነቶች በተጨማሪ ሥራና ቴክኒክ ላይ የሚያተኩሩ የማኑፋክቸሪንግና ኮንስትራክሽን  የትምህርት አይነቶች በየደረጃው ተለይተው መጨመራቸውን ገልጸዋል።
  
   በ2015 የትምህርት ዘመን የተማሪ ዩኒፎርሞችና የመማሪያ ቁሳቁሶች በፍጥነት ተደራሽ ለማድረግ ዝግጅት የተደረገ ሲሆን የትምህርት ቤቶችን አካባቢ ከአዋኪ ነገሮች ነፃ ማድረግም ትኩረት ተሰጥቶታል ተብሏል።ለአዲሱ ሥርዓተ-ትምህርት ስኬታማነት ከወላጆችና አጠቃላይ ከትምህርት ማኅበረሰቡ ጋር እየተሰራ መሆኑን አንስተዋል።

ለዚህም ስኬታማነት በትምህርት ቢሮ በኩል የተለያዩ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን ነው የገለጹት።በየደረጃው ካሉ የወላጅ ኮሚቴዎች፣ የትምህርት አመራሮችና የግል ትምህርት ቤቶችን ጨምሮ የተለያዩ መድረኮችን በመፍጠር ሰፊ ውይይት ስለመደረጉም አብራርተዋል። አዲሱ ሥርዓተ-ትምህርት በ2016 ዓ.ም ወደ ሙሉ ትግበራ የሚገባ መሆኑም ታውቋል።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የትምህርት በቤቴ ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ!

https://t.me/temhert_bebete
https://t.me/temhert_bebete
8.2K views03:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 20:40:25 ጠቃሚ የስልክ ኮዶች :-

ስልክ ሲደወልሎት ይህ ቁጥር አገልግሎት አልዋለም እንዲልላቹ ከፈለጋችሁ

ብዙ ሰዉ የማያዉቃቸው የሞባይል ሚስጥራዊ ኮዶች፡
*21*900# ይደውሉ ወይም 1 ዲጂት በመቀነስ ወደ ራስዎ ስልክ ማድረግ! ለምሳሌ
ስልክ ቁጥርዎ 0954323411 ከሆነ ወደ
*21*095432341# ይደውሉ
ለማጥፋት ሲፈልጉ #21# ብለው ይደውሉ!

ሁሉም ጥሪዎችና መልእክች ወደ ሌላ ቁጥር ዳይቨርት ሲፈልጉ
*21*0943554433# በ0943554433 ቦታ የፈለጉትን የሞባይል ወይም መደበኛ ስልክ
ቁጥር ያስገቡ ከዘ ወደርሶ ሲደወል ወድ የስገባነው ቁጥር ይደወላል
ቀድሞ ወደ ነበረበት ለመመለስ ከፈለጉ #21# ብለው
ይደውሉ ማለትም ስልክዎ ዳይቨርት ከተደረገ #21# ሲደውሉ ወደ ኖርማል ይመለሳል ዳይቨርቱ ይጠፋል
*#21# ከሆነ ስልኩ ዳይቨርት ተደርገዋል ወይስ አልተደረገም የሚል መረጃ ይሰጠናል

. ስልክዎ ሲጨናነቅ(busy) ብቻ ሲሆን ዳይቨርት ለማድረግ
*67*የፈለጉትቁጥር# ብለው ይደውሉ! ይህንን ዳይቨርት ለማጥፋት #67# ይደውሉ
. ስልክዎ ካልተነሳ ብቻ ዳይቨርት
ለማደረግ *61*የፈለጉትቁጥር# ይደውሉ!
ይህንን ዳይቨርት ለማጥፋት #61# ይደውሉ

. ስልክዎ ከኔትዎርክ ዉጪ ብቻ ሲሆን ዳይቨርት ለማድረግ *62*የፈለጉትቁጥር# ይደውሉ! ይህንን ለማጥፋት ሲፈልጉ #62# ብለው ይደውሉ!

. ኮል ዌቲንግ አክቲቭ ለማደረግ ሲፈልጉ *43# ብለው ይደውሉ! ኮል ዌቲንግ
ለማጥፋት ሲፈልጉ #43# ብለው ይደውሉ! ኮል ዌቲንግ አክቲቬት መደረጉ ወይም አለመደረጉ ለማወቅ *#43# መደወል

. ሲደውሉ ስልክ ቁጥርዎ እንዳይታይ ወይም በሌላ ቁጥር ተክተው ለመደወል ሲፈልጉ
#31#"የሚደውሉት ቁጥር" ከዛ መደወል
.አንዳንድ ስልኮች #31# ከተደወለ በኀላ የምንደውለውን ቁጥር ስናስገባ በእኛ አገር ኔትዎርክ ላይሰራ ይችላል::

▬▬ Share ▬▬▬▬

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የትምህርት በቤቴ ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ!

https://t.me/temhert_bebete
https://t.me/temhert_bebete
20.9K views17:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 19:28:48
JOIN NOW https://t.me/+t8nDuOOiG0VlZmFl
1.2K views16:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 09:44:51 ህይወት በቀላሉ የሚገመት ቢሆን አጓጊ መሆኑ ያቆም ነበር፤ ስለዚህ ለምን እንደምፈልገው አልሆነም ብለህ አትዘን...ግን የምትፈልገው ነገር እስኪፈጠር ድረስ ጥረትህን አታቁም ምክንያቱም የተሸነፍከው ያቆምክ ዕለት ነው!

@temhert_bebete
@temhert_bebete
3.9K viewsedited  06:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 21:35:57 የኦሮሚያ ክልል የ8ተኛ ክፍል ውጤት ይፋ ሆኗል! ከስር ባለው ሊንክ ገብታችሁ ማየት ትችላላችሁ።

https://t.me/Temhert_Minister
https://t.me/Temhert_Minister
1.3K views18:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 20:09:30
" ውጤታቸውን በ https://oromia.ministry.et/#/home ላይ መመልከት ይችላሉ " - ኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ

የኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ በክልሉ የ8ኛ ክፍል ፈተና የወሰዱ ተማሪዎች ውጤታቸውን ከዛሬ ጀምሮ በኢንተርኔት ላይ ማየት ይችላሉ ብሏል።

ተማሪዎች ውጤታቸውን በኢንተርኔት የሚያዩበት አድራሻ ‘https://oromia.ministry.et/#/home መሆኑንም ቢሮው ገልጿል።

የክልሉ ትምህርት ቢሮ በሰጠው መረጃ ፦

451 ሺሕ 21 ተማሪዎች ለፈተና ተመዝግበው 98 ነጥብ 3 በመቶ ፈተናውን ወስደዋል።

የ9ኛ ክፍል የማለፊያ ውጤት ለወንዶች 50 በመቶ እና ለሴቶች 47 በመቶ ነው።

በአርብቶ አደር አካባቢ የ9ኛ ክፍል ማለፊያ ውጤት ለወንዶች 47 % ለሴቶች 44 % ሲሆን ለልዩ ፍላጎት ተማሪዎች ደግሞ ለወንዶች 44% እና ለሴቶች 41% ነው።

@Temhert_Minister
@Temhert_Minister
3.4K views17:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 10:23:19
#AmharaEducationBureau

በ2015 የትምህርት ዘመን በአማራ ክልል በሚገኙ የመንግስት ትምህርት ቤቶች የተማሪ መመዝገቢያ ክፍያ ጭማሪ ማድረግ #እንደማይፈቀድ የክልሉ ትምህርት ቢሮ አሳውቋል።

"የተወሰኑ የመንግስት ትምህርት ቤቶች የመመዝገቢያ ክፍያ ጭማሪ ማድረጋቸውን አረጋግጠናል" ያሉት የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ማተብ ታፈረ (ዶ/ር)፤ ተግባሩ ህገ-ወጥ መሆኑን ጠቁመዋል።

በመሆኑም ማንኛውም በክልሉ የሚገኝ የመንግስት ትምህርት ቤት ከባለፈው ዓመት የተለየ ምንም አይነት የመመዝገቢያ ክፍያ ጭማሪ ማድረግ ያልተፈቀደለት መሆኑን ኃላፊው አሳስበዋል።

በአማራ ክልል የ2015 የትምህርት ዘመን የተማሪዎች ምዝገባ ከነሐሴ 23/2014 ዓ.ም እስከ ጳጉሜን 04/2014 ዓ.ም እንደሚከናወን መገለጹ ይታወሳል።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የትምህርት በቤቴ ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ!

https://t.me/temhert_bebete
https://t.me/temhert_bebete
6.2K views07:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 18:55:26 እንግሊዘኛ በትንሹም ቢሆን ለምትችሉ እዚህ ቻናል ውስጥ እስካሁን ከሌላችሁ ቶሎ ተቀላቀሉ በየቀኑ ምርጥ ምርጥ አነቃቂ ጥቅሶች የሚለቀቁበት አንደኛ ቻናል ነው

3.1K views15:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 18:51:15
ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ለአንድ ደቂቃ 50 ሳንቲም የአገልግሎት በማስከፈል ላይ ይገኛል

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በቀጣዮቹ ስምንት ወራት ውስጥ በ25 ከተሞች አገልግሎት እጀምራለሁ አለ።

ከሁለት ዓመት በፊት በወጣ ዓለም አቀፍ የቴሌኮም ጨረታ መሰረት ወደ ኢትዮጵያ የገባው ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በው ዕለት የመጀመሪያውን የደንበኞች የቴሌኮም አገልግሎቱን በድሬዳዋ አስጀምሯል።

ኩባንያው በመነሻ ኮዱ 07 በድሬዳዋ ከተማ የደንበኞች የኔትወርክ ሙከራ በ2G፣ 3G እና 4G ኔትወርኮች አካሂዷል።

የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ መስመር የስልክ ቁጥሮች ለድሬዳዋ ደንበኞቹ በመሸጫ ሱቆች ይፋ ያደረገ ሲሆን ኔትወርኩን ለአንድ ወር የሚቆይ የሙከራ አገልግሎት ተጀምሯል።

ድርጅቱ የድምጽ አገልግሎቱን በደቂቃ ከሳፋሪ ኮም ስልክ ቁጥሮች ወደ ሳፋሪኮም እና ወደ ኢትዮ ቴሌኮም ሲም ካርዶች በደቂቃ 50 ሳንቲም የሚያስከፍል ሲሆን ለኢንተርኔት ደግሞ በ10 ብር 120 ሜጋ ባይት፣ 900 ሜጋ ባይቱን በ50 ብር እንዲሁም ሁለት ጌጋ ባይት መጠን ያለውን ኢንተርኔት ደግሞ በ100 ብር ለ30 ቀናት በመደበኛነት በመሸጥ ላይ ነው።

ኩባንያው አክሎም እስከ ቀጣዩ ሚያዝያ 2015 ድረስ ባሉት ስምንት ወራት ውስጥ በ25 የኢትዮጵያ ከተሞች የቴሌኮም አገልግሎቶችን እንደሚጀምር ለአልዓይን አስታውቋል።

አዲስ አበባ፣ ባህርዳር፣ ጎንደር፣ ደሴ ኮምቦልቻ፣ ሀረር፣ አዳማ፣ ሀዋሳ፣ጅማ፣ ጅግጅጋ እና ሌሎች ከተሞች በቀጣዮቹ ስምንት ወራት ውስጥ አገልግሎቶቹ ከሚጀመርባቸው አካባቢዎች ዋነኞቹ ናቸውም ተብሏል።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የትምህርት በቤቴ ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ!

https://t.me/temhert_bebete
https://t.me/temhert_bebete
3.2K views15:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 14:33:50 የ9ኛ እና 10ኛ ክፍል አዲሱ ሥርዓተ ትምህርት በበ2015 ዓመት ቀጣይ አመት ለሙከራ ይሰጣል!!

የ9ኛ እና 10ኛ ክፍል አዲሱ ሥርዓተ ትምህርት የሙከራ ትግበራ በተመረጡ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ላይ በ2015 ዓመት እንደሚጀመር የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ አስታውቋል።አዲሱ የስርዓተ ትምህርት ዝግጅት በርካታ ደረጃዎችን አልፎ ለሙከራ ትግበራ የደረሰ መሆኑን የስርዓተ ትምህርት ማበልፀጊያ መሪ ስራ አስፈፃሚ ዶክተር ቴዎድሮስ ሸዋርገጥ ለብስራት ሬድዮ ገልፀዋል ።

በስርዓተ ትምህርት ዝግጅቱ ላይ የተመረጡ የመማር ማስተማር የልህቀት ማዕከላት ዩኒቨርሲቲዎች እና ካምብሪጅ ዩኒቨርስቲ በአማካሪነት እንደተሳተፉበት ሥራ አስፈፃሚው ገልፀዋል ።ይህ ሥርዓተ ትምህርት ሀገር በቀል እውቀትን፣ ግብረ ገብነትን ፣ ሳይንስና ቴክኖሎጂን የተላበሰ እንዲሆን ተደርጎ የተዘጋጀ መሆኑን ገልፀዋል ።

በመሆኑም በዚህ የሙከራ ትግበራ ወቅት ከመምህራንና ከባለድርሻ አካላት በርካታ ግብዓቶች እንደሚሰበሰቡ ጠቅሰው ወላጆችና ሌሎችም አስተያየት እዲሰጡበት በድረ ገፅ ይለቀቃል ተብላል።በሙከራ ትግበራው ወቅት የሚመጡ አስተያየቶች ተካተው በ2016 ወደ ሙሉ ትግበራ እንደሚገባም ተገልጿል ።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የትምህርት በቤቴ ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ!

https://t.me/temhert_bebete
https://t.me/temhert_bebete
4.9K viewsedited  11:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ