Get Mystery Box with random crypto!

Teddy Afro

የቴሌግራም ቻናል አርማ teddyafronet — Teddy Afro T
የቴሌግራም ቻናል አርማ teddyafronet — Teddy Afro
የሰርጥ አድራሻ: @teddyafronet
ምድቦች: ሙዚቃ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 12.77K
የሰርጥ መግለጫ

ይህ በቴዲ አፍሮ አድናቂዎች የሚመራ የTelegram ድህረ ገፅ ነው። በFacebook በInstagram እንዲሁም በዚሁ በTelegram ሰፋ ያለ ተከታዮችን ያፈራው "Teddy Afro net" ሁሌም ስለቴዲ አፍሮ በታማኝነት ያገለግላሉ። በሁሉም የመገናኛ ብዙሃን /ድህረ-ገፆች/ ትልቅ ድርጅት ሆነን ስለምንወደው #ቴዲ_አፍሮ ለዓለም ህዝብ በቂ መረጃ ተደራሽ እናደርጋለን።
Admin @PoetTataafro

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-05-07 21:34:14 ቀኑ ደርሶ በሀገር አንጻራዊ ሰላም ነግሶ ይኼንን የሙዚቃ ክር ከክቡር ዶ/ር አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) እስክንታደል ድረስ የኔም ጉጉት ትልቅ ነው። ቴዲ አፍሮም መቼ እንደሚለቅ በጠየኩት ጊዜ የሀገራችን ሁኔታ ጥሩ በሆነ ጊዜ ነበር ያለኝ። ቴዲ አፍሮን በተመለከተ ለሌላው ጊዜ እንዲህ ያሉ መረጃዎች ከየትም በኩል ብትሰሙ ታማኝ ምንጮችን እንድትፈትሹ፥ በተለይም የቴዲ አፍሮን ህጋዊ የፌስቡክ ገጽ እና Teddy Afro Net የተሰኘውን ገጾች እንድትከታተሉ በትህትና ለመጠቆም እወዳለሁ።

ወደ ኢትዮ ቴሌኮም እንመለስ። ስለ ቴዲ አፍሮ አልበም የጠቀሰውን ዜና ከሰዓታት በኋላ ከገጹ ላይ ያስወገደ ቢሆንም ከድርጅቱ እንዲህ ያሉ የሀሰት ዜናዎች በሀገር ደረጃ ሲያሰራጩ ይኽ የመጀመሪያው ባይሆንም ህዝብ በሚያከብረው እና ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ባለው አርቲስት ስም አንደ የሀገር በቀል ድርጅት የሀሰት ዜናውን ሀላፊነት በጎደለው መልኩ ማሰራጨቱ ትልቅ ነውር መሆኑን ለድርጅቱ የበላይ አመራሮች እና ለሚመለከተው አካል ስጠቁም ተግባራቸው እንደየ ሁልጊዜ ህዝብን ያላከበረ በመሆኑ በድርጅቱ ዳግም የሆነ ትልቅ ሀፍረት እንደተሰማኝ በመጠቆም ጭምር ነው። ሌላ አማራጭ ቢኖረንና ከዚህ ተቋም ጋ ለዘለዓለም ደንበኝነታችንን ብናቋርጥም በተለየ መልኩ ትልቅ ደስታ እንደሚሰማኝ በዚሁ ለመጠቆም እወዳለሁ።

በስተ-መጨረሻም በሰዋሰው መልቲሚዲያ ሙዚቃዎቻቸውን ለለቀቁ የሀገራችን ዘፋኞች በጠቅላላ እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት እወዳለሁ። ከዚሁ ጋ በማያያዝ ቴዲ አፍሮ እገሌ ላይ አልበም ደረበ (ሊደርብ ነው) የሚል ስጋት ያደረባችሁ ግለሰቦችም ሆናችሁ ሌሎች አካሎች ይኼንን የሀሰት መረጃ በማመናችሁ ብቻ ይሄ ስጋት ሊሰማችሁ እንደቻለ በመረዳት ያሞኛችሁን ድርጅት ወቅሳችሁ የሀገሬ ክር እስኪለቀቅ በእጃቹ የደረሱትን ዘፈኖች አድምጡ ስል እመክራለሁ።

#ታታ_አፍሮ (ነፃ ብዕር)
2.8K views18:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-07 21:34:13
የተደራጀ ውሸት።

የክቡር ዶ/ር አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) እዮሪካ የተሰኘ አልበም ሊለቅ ነው የሚል የሀሰት ዜና Ethio Telecom ከ1.2 ሚሊየን በላይ ተከታይ ባለው በህጋዊ የፌስቡክ ገጹ ላይ ከለቀቀ በኋላ የተለያዩ ግለሰቦች ሀሳቡን እስከ አሁኗ ሰዓት ድረስ እየተቀባበሉት ይገኛሉ። እርግጥ ነው ቴዲ አፍሮ እጅግ የሚደንቁ ዘፈኖች የተከማቹበት ክር እያዘጋጀ መሆኑን አውቃለሁ። ከሰማኋቸው ዘፈኖች ውስጥ አብዛኛዎቹ አሁንም ድረስ በልቤ ውስጥ የሚሯሯጡትን ዜማዎቹን በማስብ ጊዜ፥ ልክ በረሃ ላይ ደክሜ እንደ ነብዩ ዮናስ ጥላ አግኝቼ ያረፍኩ ያህል ደስ እሰኛለሁ። ከዜማዎቹ ትዝታ ስላቀቅ ደግሞ ዳግም እንደ ጥላዋ መጠውለግ ስሜቴን ሁሉ ብል ይወረዋል።
2.7K views18:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-28 22:47:39
የቴዲ አፍሮ አራተኛ ልጅ የሆነው ዘዳዊት ቴዎድሮስ ከእናቱ ጋ…
5.1K views19:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-18 20:48:14
የቴዲ አፍሮ ሽማግሌ

ሚያዝያ 10/1965 ዓ.ም (የዛሬ 50 አመት) ሺ አለቃ አትሌት ኃይሌ ገብረሥላሴ የተወለደባት ዕለት ነች። ሀይሌ ገብረሥላሴ የኢትዮጵያን ሰንደቅ አላማ በዓለም ላይ ከፍ አድርጎ ያውለበለበ ታላቅ አትሌት ነው። ሩጫን ከጀመረባት ዘመን እስከ አሁኗ ቅጽበት ድረስ ኃይሌ ገብረሥላሴ በዓለም ላይ ያለው ክብር ወደር የማይገኝለት ሲሆን ኢትዮጵያን በዘመኑ በትልቅ ክብር ለዓለም ህዝብ አስተዋውቋል።

የዓለማችን ትልቁ የመገናኛ ብዙሃን ጣቢያ /DSTV/ ስለ ሺ አለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ ጀብድ በተደጋጋሚ ይዘግባል። ትልልቅ የዓለም መጽሔቶችም ኃይሌን አወድሰውታል። በተጨማሪም ኃይሌ ገብረሥላሴ ሽማግሌ ሆኖ ከዳራቸው ጥንዶች ውስጥ ቴዲ አፍሮ እና አምለሰት ሙጬ ተጠቃሽ ናቸው።

ሺ አለቃ አትሌት ኃይለ ገብረሥላሴ (የሀገር ሽማግሌ) አገርህን ያስከበርክ ሰንደቋንም ከፍ አድርገኽ ያውለበለብክ ታላቅ ሰው ነህና እንወድሃለን። በታላቅ ክብርም እናከብርሃለን።

ጥቁሩ የዓለማችን አንበሳ ሆይ እንኳን በምትወዳት ሀገርህ ላይ ተወለድክልን። መልካም ልደት።

"እዩት ንጉሡ ግርማ ሞገሱ
ዘውዱን ሸለመው ሰጠው ለአዲሱ"

@tataafro_official (ነፃ ብዕር)
908 views17:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-15 20:44:49
#ETHIOPIA ሚያዝያ 7/2009 ዓ.ም

ኢትዮጵያ የተሰኘው የክቡር ዶ/ር አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) ነጠላ ዜማ በህጋዊ የዩትዩብ ቻናሉ ከተለቀቀ ዛሬ ስድስተኛ አመቱን ደፈነ። ይኼ ሙዚቃ ሚያዝያ 7/2009 ዓ.ም ምሽት ላይ ነበር የተለቀቀው። በተለቀቀ በሰዓታት ውስጥ ግን ድፍን አዲስ አበባ ውስጥ ሙዚቃው በመዳረሱ ከተማይቱ አዲስ ዘመንን የምታከብር ያህል በየ ስፍራው እንደ ባህላዊ ዘፈን ይኼ ሙዚቃ በስፋት ሲደመጥ አነጋ።

በዕለቱ በመዲናይቱ የተለያዩ ስፍራዎች እየተዘዋወርኩ ለሊቱን ሙሉ ስሜቱን ለማጣጣም የሞከርኩ ሲሆን በየ ቦታው የሚታየው የህዝቡ ስሜት እጅግ ልዩ ነበር።

ይህ ኢትዮጵያ የተሰኘ ተወዳጅ ሙዚቃ ከተለቀቀ በስድስት አመታት ውስጥ ይሄንን መረጃ እስከ-ለጠፍንበት ሰዓት ድረስ በዩትዩብ ብቻ ሀያ አራት ሚልየን ዘጠኝ መቶ አርባ ሶስት ሺ አንድ መቶ አድማጮችን አግኝቷል። ይኼ ደግሞ በኢትዮጵያ የሙዚቃ ታሪክ ያለ ተንቀሳቃሽ ምስል እጀባ ብዙ ተመልካቾችን ያገኘ የመጀመሪያው ነጠላ ዜማ ነው። በተጨማሪም ባለፉት አመታቶች ውስጥ በዓለም አቀፍ ደረጃ በተለያዩ የሙዚቃ ሰንጠረዦች ላይ ክብረ-ወሰኖችን የሰበረ የዓለማችን ተወዳጅ ሙዚቃ ለመሆን በቅቷል።

ይኽ ሙዚቃ በወቅቱ በፈጠረው ትልቅ የሚዲያ ንቅናቄ የዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ከወትሮው በተለየ መልኩ ለቴዲ አፍሮ ትልቅ ትኩረት እንዲሰጡት ያስቻለ ከመሆኑም በላይ ዛሬም ድረስ BBC, CNN, Al Jazeera, CGTN Africa, BBC Africa, የቻይናው CC TV እና ሌሎችም ዓለም አቀፍ የመገናኛ ብዙሃኖች ቴዲ አፍሮ በአፍሪካ እና በዓለም ላይ በሚገኙ አድናቂዎቹ ባለው ሰፊ ተቀባይነት ምክኒያት ስለሱ መዘገብ አትራፊ መሆኑን ተረድተው ስለሱ አዳዲስ መረጃዎችን መዘገብ ቀጥለዋል።

@TataAfro_official (ነፃ ብዕር)
1.0K views17:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-14 21:06:31
ዕለተ ዓርብ፣ ዕለተ ስቅለት፣ መልካሙ ዓርብ

በዚህች ዕለት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዕፀ መስቀል የተሰቀለባት ዕለት ናትና “ዕለተ ስቅለት”የእግዚአብሔር መልካምነት ለሰው ልጅ ድኅነት በፍቃዱ ራሱን አሳልፎ ለሞት በመስጠቱ የተገለጠባት ናትና “መልካሙ ዓርብ” ይባላል።

ዓርብ ነግህ (ሲነጋ)

በዚህች ዕለት በነጋ ጊዜ የአይሁድ ሊቃነ ካህናት ኢየሱስን ወደ ፍርድ አደባባይ ሊያወጡት፣ ለጲላጦስ አሳልፈው ይሰጡት ዘንድ እንዲሁም በፍርድ አደባባይ ይሰቅሉት ዘንድ የተማከሩበት ዕለት ነው።

“ሲነጋም ጊዜ የካህናት አለቆችና የሕዝቡ ሽማግሎች ሁሉ ጌታችን ኢየሱስን ሊገድሉት ተማከሩ፤ አስረውም ወሰዱት፥ ለገዢው ለጰንጤናዊው ጲላጦስም አሳልፈው ሰጡት” እንዲል። (ማቴ.፳፯፥፩-፪)

መልካሙ ዐርብ
1.7K views18:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-07 18:43:30
የክብር ዶ/ር አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) እንዲህ ብሎ ነበር።

«የተማረ እንጂ የተባረከ መሪ ከለመንን ቆይተናል። የተማረ ከተገኘማ ጥሩ ነው የተባረከ ይሁን እንጂ። የተባረከ መሪ ግን ከተገኘ በጣም ጥሩ ነው ባይማርም እንኳን።»
1.4K views15:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-31 17:53:14
1.4K views14:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-27 19:20:49
2.2K views16:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-11 21:13:46 "ትግራይ ዮሐንስ ቢሰዋ
ይነሳል በአክሱም በሳባ"

ደርቡሾች የኢትዮጵያን ድንበር አልፈው እስከ ጎንደር ገብተው በርካታ አብያተክርስቲያናትን አቃጠሉ፤ ቀሳውስት እና ምእመናንን ገደሉ፤ የተረፈውንም ማርከው ወሰዱ። ይሄንንም ነገር አስመራ ሆነው የሰሙት አጼ ዮሐንስ ንጉሥ ተክለሃይማኖትን ጦራቸውን ይዘው ወደ መተማ እንዲዘምቱ አዘዙ።

ንጉሥ ተክለሃይማኖትም ትእዛዙን ተቀበለው በደርቡሽ ላይ ዘመቱ። ድልም አደረጉ ምርኮኛም ይዘው ተመለሱ። ወዲያውኑ ግን የደርቡሽን መሸነፍ የሰማው የሱዳኑ ገዢ ከሊፍ ዐብዱላሂ አቡ አንጋ ሌላ በቁጥሩ የበዛ ሰራዊት በድጋሚ ላከ። በዚኛው ጊዜ የንጉሥ ተክለሃይማኖት ጦር የጠላትን ጦር መቋቋም ስላልቻለ መሸሽን አማራጭ አደረገ።

ከወራት በኋላም አጼ ዮሐንስ የፈሰሰውን የኢትዮጵያውያንን ደም ሊበቀሉ ጦራቸውን አስከትለው ወደ መተማ ዘመቱ። በመተማም የነበረው የደርቡሽ ጦር የአጼ ዮሐንስን ጀግንነት ጠንቅቆ ያውቅ ስለነበር ከሰራዊቱ በተጨማሪ ገብሬና ነጋዴዎችን ሳይቀር መሳሪያ አሲይዞ ይጠብቅ ነበር።

ቅዳሜ መጋቢት 1 ቀን 1881 ዓ.ም ጦርነቱ ተጀመረ። የኢትዮጵያ ሰራዊት እየፎከረና እየሸለለ ደርቡሾቹ እስከመሸጉበት ድረስ በመግባት ቀኑን ሙሉ ሲዋጋ ዋለ። ሆኖም የኢትዮጵያ ሰራዊት ኃይል ከፍ ብሎ የደርቡሽ ሰራዊት መሸሽ ጀምሮ ሳለ አጼ ዮሐንስ ከበቅሏቸው ወርደው ከሰራዊታቸው መሐል ሆነው ይዋጉና ያዋጉ ስለነበር ሳይታሰብ በጥይት ተመትተው ወደቁ። በዚህም ጊዜ ከድሉ አፋፍ እየደረሰ የነበረው የኢትዮጵያ ሰራዊት የንጉሡን መመታት ሲሰማ ይደናገጥ ጀመር። የደርቡሽን ምሽግ ሰብሮ ገብቶ የነበረው ወታደርም መውጣትን መረጠ።

አጼ ዮሐንስም በነገሡ በ17 ዓመታቸው እሁድ መጋቢት 2 ቀን 1881 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ። በዚህም፦
"በጎንደር መተኮስ
በደንቢያ መታረድ አዝኖ ዮሐንስ፤
ደሙን አፈሰሰ እንደ ክርስቶስ።" ተብሎ ተገጠመ።

በአጼ ዮሐንስ ዙሪያ የነበሩ ወታደር ፣ መኳንንት እና ካህናትም የአጼ ዮሐንስን አስክሬን በሳጥን አድርገው በሰም በማሸግ ከመተማ መሸሽ ጀመሩ። የደርቡሽ ጦር መሪ የነበረው ዜኪ ግን ሰራዊቱን ይዞ ተከተላቸው። የአጼ ዮሐንስ ወታደሮች እና መኳንንትም የንጉሣችንን አስከሬን በሕይወት እያለን አናስነካም ብለው እስከመጨረሻው ተዋጉ ሆኖም ቁጥራቸው ትንሽ ነበርና ድል ሆኑ። ከዚህም በመቀጠል ደርቡሾች የአጼ ዮሐንስን አስከሬን ከሳጥኑ አውጥተው ራሳቸውን ቆርጠው በሱዳን ላለው ከሊፋ ላኩለት። ከሊፋውም የአጼ ዮሐንስን ራስ በእንጨት ሰክቶ በግመል አድርጎ ገበያ ለገብያ እያዞረ ሲያሳይ ዋለ። ይህንንም ያወቀው የኢትዮጵያ ሕዝብም እንዲህ ሲል ተቀኘ፦
"አጼ ዮሐንስ ይዋሻሉ
መጠጥ አልጠጣም ይላሉ፤
ሲጠጡ አይተናል በርግጥ፤
ራስ የሚያዞር መጠጥ።"

ምነጭ፥ የኢትዮጵያ ታሪክ ከአጼ ቴዎድሮስ እስከ አጼ ኃይለሥላሴ በተክለጻዲቅ መኩሪያ
1.8K views18:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ