Get Mystery Box with random crypto!

Teddy Afro

የቴሌግራም ቻናል አርማ teddyafronet — Teddy Afro T
የቴሌግራም ቻናል አርማ teddyafronet — Teddy Afro
የሰርጥ አድራሻ: @teddyafronet
ምድቦች: ሙዚቃ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 12.77K
የሰርጥ መግለጫ

ይህ በቴዲ አፍሮ አድናቂዎች የሚመራ የTelegram ድህረ ገፅ ነው። በFacebook በInstagram እንዲሁም በዚሁ በTelegram ሰፋ ያለ ተከታዮችን ያፈራው "Teddy Afro net" ሁሌም ስለቴዲ አፍሮ በታማኝነት ያገለግላሉ። በሁሉም የመገናኛ ብዙሃን /ድህረ-ገፆች/ ትልቅ ድርጅት ሆነን ስለምንወደው #ቴዲ_አፍሮ ለዓለም ህዝብ በቂ መረጃ ተደራሽ እናደርጋለን።
Admin @PoetTataafro

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 6

2022-05-26 11:16:01 @
12.5K views08:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-26 11:15:46
"…የምንኖርባት ጊዜ ከዘለዓለማዊ ህይወት ላይ ተቀንሳ በቅንፍ ውስጥ የተቀመጠች በጣም ትንሽ ጊዜ ናት። በዚህች ጊዜ ውስጥ በህይወታችን ስንኖር መረዳዳትን፤ መቀራረብን እና መተባበርን መልመድ አለብን።"

Teddy Afro
12.2K views08:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-15 21:09:39 @
13.7K views18:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-15 21:09:25 ቴዲ አፍሮ ከእስር ከተፈታ በኋላ ጥቁር ሰው የተሰኘ ግዙፍ አልበም ነበር የገነባው። ይህ ድንቅ አልበም ሚያዝያ 6/2004 ዓ.ም በገበያ ላይ የዋለው። ሚያዝያ 6/2014 ዓ.ም ይህ አልበም 10ኛ አመቱን ደፍኗል። እልፍ ሰዎች በጉጉት ሲጠብቁት የነበረው አርቲስት ቴዲ አፍሮ ከሰባት አመት ቆይታ በኋላ ነበር አልበም ይዞ ብቅ ያለው። በመሆኑም በኢትዮጵያ እና በመላው ዓለም ለሚገኙ ኢትዮጵያውያን እና ለሌሎች የሙዚቃ አፍቃሪያን እንዲሁም የአርቲስቱ የኪነ ጥብብ ቱርፋት ወዳጅ ለሆኑ ሁሉ ይኽ አልበም መለቀቁ እጅግ አስደሳች ዜና ሲሆን በአልበሙ የተካተቱት ሙዚቃዎችም ተወዳጅ ነበረ። በወቅቱ ትልቅ የገበያ መነቃቃትን የፈጠረው ጥቁር ሰው አልበም በአገር ውስጥ እና በዓለም ዙሪያ ሁሉ ታላላቅ ኮንሰርቶች እንዲዘጋጁ ትልቅ እድልን ያመቻቸ ነበር። ጥቁር ሰው አልበም እንደሌሎቹ የአርቲስቱ የጥበብ ቱርፋቶች ዛሬም ድረስ እንደ አዲስ ዜማ ይደመጣል። እንደ ወይን እያደር ጣዕሙ ይጎመራል።

#Ethiopia

ኢትዮጵያ የተሰኘው ነጠላ ዜማ በቴዲ አፍሮ ህጋዊ የዩትዩብ ቻናል ከተለቀቀ ዛሬ አምስተኛ አመቱን ደፈነ። ይኼ ሙዚቃ ሚያዝያ 7/2009 ዓ.ም ምሽት ላይ ነበር የተለቀቀው። በተለቀቀ በሰዓታት ውስጥ ግን ድፍን አዲስ አበባ በዚህ ሙዚቃ ዳንኪራ ስትረግጥ አምሽታለች። ከተማይቱ አዲስ ዘመንን የምታከብር ያህል በየ ስፍራው እንደ ብሔራዊ መዝሙር ይኼ ሙዚቃ ብቻ ሲደመጥ አነጋ... በዕለቱ በተለያዩ ስፍራዎች እየተዘዋወርኩ ለሊቱን ሙሉ ስሜቱን ለማጣጣም የሞከርኩ ሲሆን በየ ቦታው የሚታየው የህዝቡ ስሜት እጅግ ልዩ ነበር። የአገር ፍቅር ልኩ የገባው የአገሬ ሰው ዛሬም ድረስ በዚህ ሙዚቃ ኢትዮጵያን ከፍ ከፍ ያደርጋታል። ዘፈኑ ከተለቀቀ በአምስት አመታት ውስጥ በዩትዩብ ብቻ 23 ሚልየን አድማጭን አግኝቷል። በተጨማሪም ይኼው ሙዚቃ በምስል ተቀናብሮ በአርቲስቱ ህጋዊ የዩትዩብ ቻናል ላይ 5.7 ሚሊየን ጊዜ መታየት ችሏል። በጥቅሉ ኢትዮጵያ የተሰኘው ነጠላ ዜማ በዩትዩብ ብያ ከ28.7 ሚሊየን በላይ አድማጮችን አግኝቷል። ይኼ ደግሞ በኢትዮጵያ ያለ ተንቀሳቃሽ ምስል ተለቆ ብዙ አድማጮችን ያገኘ የመጀመሪያው ነጠላ ዜማ ነው።

✎ #ታታ_አፍሮ /ነፃ ብዕር/

Teddy Afro ደረጃቸውን ስለጠበቁ ውብ የሙዚቃ አልበሞችህ ከልብ እናመሰግናለ
12.7K views18:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-15 21:09:04
#ጥቁር_ሰው እና #ኢትዮጵያ
9.2K views18:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-05 16:28:36
የመልካም ልደት መግለጫ!

ውዷ አምለሰት ሙጬ እንኳን ተወለድሽ! እንኳንም በሰላምና በጤና ለዚህች ዕለት አደረሰሽ! ኤሚዬ ብሩ እና መልካም ልደት ይሁንልሽ። ቀሪው ዘመንሽ በደስታና በብዙ በረከቶች የተሞላ ይሁን። የልጆችሽን ወግ ማዕረግ የባለቤትሽንም የስኬት ጥግ በዘመንሽ እንዲያሳይሽና የልብሽም መሻቶች በዘመንሽ የተፈጸሙ እንዲሆኑልሽ እመኛለሁ።

ከአክባሪ ወንድምሽ ✎ #ታታ_አፍሮ /ነፃ ብዕር/
11.3K views13:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-02 10:00:16 @
10.8K views07:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-02 10:00:05
ሆነሽ በመልክሽ ሰው ገዳይ የውበት አርበኛ
ማሰብ አቃተን ባንቺ ተማርከን እኛ
10.1K views07:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-23 10:21:34
ክቡር ዶክተር አርቲስት ቴዎድሮስ ካሣሁን (ቴዲ አፍሮ)

ቤተልሔም፣ ኒው ኢራ እና የካቲት 12 የተማረባቸ ትመህርት ቤቶች ናቸው፡፡ ክስተቶችን፣ ስሜቶችን፣ እውነቶችን ኹሉ ይዘፍናቸዋል ብቻም ሳይኾን ይተርካቸዋል፣ ይሰንዳቸዋልም። ለበርካታ ድምፃውያንም ግጥም እና ዜማ ደርሶ አበርክቷል። በአቡጊዳ፣ በያስተሠርያል እና በጥቁር ሰው (በ 2004 ዓ/ም በለዛ ምርጥ አድማጮች ምርጫ፥ የዓመቱ ምርጥ አልበም ተሸላሚ ነበር።) ኢትዮጵያ የተሰኘው አልበሙም ባለፈው ዓመት በለዛ ምርጥ አድማጮች ምርጫ፥ የዓመቱ ምርጥ አልበም ተሸላሚ ነበር።) ከላይ የተዘረዘሩት ክቡር ዶክተር አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን የሠራቸው የአልበሞች ስያሜዎች ናቸው፡፡ በ2007 ዓ/ም ደግሞ የዓመቱ ምርጥ ነጠላ ዜማ በሚል ዘርፍ በሰባ ደረጃ ተሸላሚም ነበር። ዘንድሮም የሁለት አመት ሙዚቃዎች በአንድ ተሰብስበው ለውድድር ሲቀርቡ እጩ ሆኖ የቀረበው ደሞ በአባይ የተሰኘው ነጠላ ዜማው ነው።

የአመቱ ምርጥ ነጠላ ዜማ በሚል ዘርፍ እጩ ሆኖ የቀረበውን ቴዲ አፍሮን እዚህ ይምረጡ

https://vote.lezashow.com/
13.6K views07:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-22 16:56:03
ዜና ኪነጥበብ

የክቡር ዶ/ር አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን /ቴዲ አፍሮ/ ከሐምሌ 1/2011 ዓ.ም - ሰኔ 30/2013 ዓ.ም ድረስ ከወጡ ነጠላ ዜማዎች ጋ በለዛ አዋርድ ላይ 'ምርጥ ነጠላ ዜማ' በሚል ዘርፍ "ደሞ በአባይ" የተሰኘው ነጠላ ዜማው እጩ ሆኖ ቀርቧል። ስለሆነም ከታች በተቀመጠው ማስፈንጠሪያ እየገባችሁ ድምጻችሁን ለቴዲ አፍሮ እንድትሰጡት ለመጠቆም እንወዳለን።

#ማሳሰቢያ
አንድ ሰው በአንድ ዘርፍ ከታጩ ሙዚቃዎች ውስጥ ከአንድ ጊዜ በላይ መምረጥ ስለማይችል ስለአመራረጥ ሂደቱ ግልጽ ያልሆነ ነገር ከገጠምዎ ከአንድ ደቂቃ በታች የሆነ የአመራረጥ ሂደቱን የሚያስረዳ ቪዲዮ ከሰዓታት በኋላ ስለምናደርስዎ እንዲጠብቁን እንጠቁማለን።

https://vote.lezashow.com/
9.5K views13:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ