Get Mystery Box with random crypto!

Teddy Afro

የቴሌግራም ቻናል አርማ teddyafronet — Teddy Afro T
የቴሌግራም ቻናል አርማ teddyafronet — Teddy Afro
የሰርጥ አድራሻ: @teddyafronet
ምድቦች: ሙዚቃ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 12.77K
የሰርጥ መግለጫ

ይህ በቴዲ አፍሮ አድናቂዎች የሚመራ የTelegram ድህረ ገፅ ነው። በFacebook በInstagram እንዲሁም በዚሁ በTelegram ሰፋ ያለ ተከታዮችን ያፈራው "Teddy Afro net" ሁሌም ስለቴዲ አፍሮ በታማኝነት ያገለግላሉ። በሁሉም የመገናኛ ብዙሃን /ድህረ-ገፆች/ ትልቅ ድርጅት ሆነን ስለምንወደው #ቴዲ_አፍሮ ለዓለም ህዝብ በቂ መረጃ ተደራሽ እናደርጋለን።
Admin @PoetTataafro

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2023-03-11 21:13:42
1.8K views18:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-08 22:14:17 የቴዲ አፍሮ እና የኢትዮጵያ ህዝብ ቁርኝት ክፍል (፩)

በኢትዮጵያ እንደ ክቡር ዶ/ር አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) ለወገኖቹ የወገነ ፖለቲከኛም ሆነ የኪነጥበብ ሰው የለም። በተለያዩ ወቅቶች ለህዝባቸው ድጋፍ ለመሆን እና በኢትዮጵያውያን ላይ እየደረሱ ያሉ መድሎዎችን ለመቋወም የተነሱ ግለሰቦች እና ተቋሞች በሚደርስባቸው ጫና አልያም በጥቅም የጀመሩትን ሳይጨርሱ የውሃ ሽታ ሆነው ቀርተዋል። ከሀገር ውጪ ይኖሩ የነበሩ የሰብዓዊ መብት ተሟጓቾችም ሆኑ ጭቁኑን አገዛዝ በመሳሪያም በዲፕሎማሲም እንገረስሳለን ያሉ የግንቦት ሰባት ዋና አመራሮች ሳይቀሩ ትግሉ ተጠናቋል ብለው የገዢው ፓርቲ አገልጋይ ሆነው ህዝባቸውን የራስህ ጉዳይ ካሉት አመታቶች ተቆጠሩ። ቴዲ አፍሮ ግን ያለፉትን 20 አመታቶች ያለማንገራገር ከምስኪን ወገኖቹ ጋ ጸንቶ በመቆሙ ብዙ ከባድ የሆኑ መስዋዕትነቶችን ለብቻው ተጋፍጧል።

ቴዲ አፍሮ በልዩ ሁኔታ በግል ህይወቱ ላይ አልያም በስራዎቹ ዙሪያ የሚፈጠሩ አልመግባባቶችን ተጎድቶም ቢሆን በጊዜ የመቋጨት ልማድ ያለው ብልህ ሰው ነው። በወገኖቹ ላይ የሚደርሱ በመንግስታዊ እና በሌሎች በተደራጁ ቡድኖች የሚደርሱ መድሎዎችን፣ ዘር ተኮር ማፈናቀሎችን፣ ማንነት ላይ ያተኮሩ ጭፍጨፋዎችን፣ ኢሰብአዊ ድርጊቶችን፣ ህገመንግስታዊ ስህተቶችን ብሎም የመብት ጥሰቶችን በግልጽ እና በቀዳሚነት በመቋወሙ ለአመታቶች ብቻውን ሲጨቆንና ኢፍትሃዊ የሆኑ ድርጊቶች በገዢው ቡድን ሲፈጸሙበት ቆይቷል። ከነዚህም ውስጥ በሀሰት ክስ ለ18 ወራቶች በእስር መቆየት፣ በሀገር ውስጥ የሚደረጉ የኮንሰርት ስራዎቹን ያለበቂ ምክኒያት መከልከል፣ በሚዲያዎች ላይ የኪነጥበብ ስራዎቹ እንዳይተላለፉ ማገድ፣ ከሀገር ለስራ የመውጣት መብቱን በመንፈግ በተደጋጋሚ ከኤርፖርት መመለስ እንዲሁም የአልበም የምረቃ ስነስርዓቱን እንዳይፈጽም ፍቃድ የለህም በሚል አግባባዊ ባልሆነ አካሄድ በዕለቱ (በምረቃው ዕለት) ቦታው ላይ በመገኘት በሀይል መሰረዝና በየመንገዱ እየተከታተሉ ድንገተኛ ፍተሻ ማድረግ ብሎም የስነልቦና ጉዳት ለማድረስ እና ውስጡን ሞቾት እንዲነሳው በማሰብ በሚንቀሳቀስባቸው ስፍራዎች ሁሉ የተለያዩ መከናዎችን በመመደብ ማንነታቸው ያልታወቁ ሰዎች እንዲከታተሉት ማድረግ እና የመሰሉ መንግስታዊ ውንብድናዎች ለአብነት የሚጠቀሱ ናቸው።

እንደ ሚታወቀው በቴዲ አፍሮ ልክ ግዙፍ ኮንሰርቶችን በኢትዮጵያ ያዘጋጀ አርቲስትም ሆነ መንግስታዊ ተቋም አልያም ሌሎች በዘርፉ የተሰማሩ ፕሮሞተሮች የሉም። የቴዲ አፍሮ ኮንሰርቶች በአገር ቤት በሚዘጋጁበት ወቅት በተለያዩ ዓለማት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ኮንሰርቱን ለመታደም በማሰብ ወደ ኢትዮጵያ ይጓዛሉ። እንዲሁም ከክፍለ ሀገርም ኮንሰርቱ ወደተዘጋጀበት ከተማ ይጓዛሉ። ይሄ ደግሞ የከተማውን ገበያ የሚያነቃቃ ትልቅ አጋጣሚ ነው። ለምሳሌ ባህርዳር ላይ ተዘጋጅቶ በነበረው ኮንሰርት ላይ ከተለያዩ የዓለም ሀገራት ከመጡ ኢትዮጵያውያን በተጨማሪ ከአዲስ አበባ፣ ከጎንደር፣ ከኦሮሚያ ክልል እንዲሁም ከተለያዩ አከባቢዎች ወደ ከተማዋ በመግባታቸው በከተማዋ የሚገኙ ሆቴሎች በሙሉ አልጋቸው ለተከታታይ ሶስት ቀናት ተይዞ ቆይቷል። የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎችም በልዩ ሁኔታ ሲንቀሳቀሱ ነበር። የምግብ ሰጪ ድርጅቶችም ከወትሮው በተለየ መልኩ በሰዎች ተሞልተው ነበር። ይኼንን በወቅቱ ቦታው ላይ ተገኝቼ አስተውያለሁ። እንዲሁም አዲስ አበባ ላይ ባዘጋጃቸው መድረኮችም ተመሳሳይ ነገሮች ተፈጥረዋል። ልጁ ለአንድ አዳጊ ሀገር ትልቅ ሀብት ነው። ሆኖም ግን ይኼንን ውድ ሀብት ጨቋኞች አምርረው ተጣሉት። ከነርሱ የሚፈልገው አንዳች ቢኖር ድሃ ወገኖቹን ሠላም ሰጥተው፣ መብታቸውን አክብረው ዲሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ እንዲያኖሩለት ብቻ ነው።

ቴዲ አፍሮ ሀገር ውስጥ ሊያዘጋጃቸው አስቦ የተሰረዙበት ኮንሰርቶች በቅድሚያ አስፈላጊውን ነገር ሁሉ አሟልቶ ፍቃድ ተሰጥቶት ብዙ ሚሊዮኖችን ወጪ ካደረገባቸው በኋላ በድንገት ከሚመለከተው አካል የሚደረጉ የኮንሰርት ክልከላዎች ቴዲ አፍሮን ምን ያህል እንዳከሰሩት ላሰላ ሰው በግለሰብ ደረጃ ይሄንን ሁሉ ኪሳራ መቋቋም በጣም ከባድ እንደሆነ ይረዳል። ቴዲ አፍሮ ግን በዚህ ሲያማርርና ሲቆጣ ተስተውሎ አያውቅም። ተደጋጋሚ ኪሳራዎች ደርሰውበትም ለህዝቤ ስል ያጣሁን ገንዘብ በካሴት ሽያጭ አገኘዋለሁ ብሎ በማሰብ እንኳን ካሴቱ ላይ የሁለት ብር ጭማሪ አድርጎ አያውቅም። ይልቁንም አንድ ጀማሪ ሙዚቀኛ በሚያከፋፍልበት ዋጋ ነው ስራውን ገበያ ላይ የሚበትነው። እሱማ ቢቻለው ለሁሉ በነጻ ቢያደል ደስታው ነበር። ኮንሰርቶቹንም ስንመለከት ከሱ በታች ተከታይ ያላቸው የሀገራችን ሙዚቀኞች የመግቢያ ዋጋቸውን ለመደበኛ 600 ብር ለVIP ደግሞ እስከ 3000 ብር ድረስ ሲያስከፍሉ አስተውለናል። ቴዲ አፍሮ ግን መደበኛ የመግቢያ ዋጋ 300 ብር የVIP ደግሞ 500 ብር ነበር ትልቁ የትኬት መሸጫ ዋጋው። ይኼም በዛ ብሎ ከአዘጋጆች ጋ ሲከራከር ነበር። ምን ያህል ህዝቡን ቢረዳው እና ቢወደው ነው ኪሱ የሚገባው ብር ሳያጓጓው በጣም እርካሽ በሚባል ዋጋ ያንን የመሰለ የመድረክ ስራን የሚያቀርብልን ብዬ ሳስብ አንዴ ጅማ ለኮንሰርት ሄዶ የተናገራት አንዲት ቃል ትዝ አለችኝ። "በከፈላችሁት ልክ ሳይሆን በምወዳችሁ ልክ ነው የምዘፍንላችሁ" ሲል ሙዚቃውን ሊታደሙ ለመጡ አድናቂዎቹ ተናግሮ ነበር። እውነትም በሚወደን ልክ አዜመልን። በሚወደን ልክ በመከራችን ወቅት ለምን ብሎ ቆመልን። በያንዳዷ የችግራችን ወቅት ፊትአውራሪ ሆነልን። አንደበታችን ተይዞ አቅማችን ተዳክሞ ተስፋ በቆረጥን ጊዜ እሱ ጉልበት ሆነን። ቴዲ አፍሮ ሸክማችንን እንደ ግል ሸክሙ ቆጥሮ ጨቋኞችን ተጋፈጠ።

ክፍል ሁለት ነገ በተመሳሳይ ሰዓት ይለጠፋል

✎ #ታታ_አፍሮ /ነፃ ብዕር/
1.2K views19:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-27 18:45:56
የክቡር ዶ/ር አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) ቦረና ላይ በድርቅ የተጎዱ ወገኖቻችን ለመደገፍ "127ኛውን የአድዋ የድል በዓልን ለቦረና" በሚል መርህ እየተደረገ ባለው የእርዳታ ማሰባሰቢያ በኩል ለቦረና ወገኖቻችን ይውል ዘንድ የአንድ ሚሊየን ብር ድጋፍ በማድረግ ግንባር ቀደም ሆኗል። ይኼ ተግባር ለድርጅቶችና ለሌሎች አካላቶች ትልቅ የቤት ስራ ጥሎ የሚያልፍ ከመሆኑም በላይ የተጠቀሱትንም ያልተጠቀሱትንም አካሎች የሚያነቃቃ ትልቅ ተግባር መሆኑ ግልጽ ነው።

ሁሌም ለመስጠት የሚጣደፍ እጅ ከአመታቶች በፊት ካቴና ገብቶበት ነበር። ሁሌም ለወገኔ የሚለው ይኽ ሰው ከአመታቶች በፊት ኦሮሞ ጠል ተብሎ ነበር። ዛሬ ግን እሱ ከሁሉ ቀድሞ ለገሰ። ሁሌም ካልሰጠሁ የሚለው ይህ ሰው በሰሜን በደቡብ በምስራቅ በምዕራብ ሰው ተራበ ቢሉት ከኔ ወገን አይደለም ብሎ ዘግይቶ አያውቅም። ስስ ልቡ ለሁሉ እኩል ያዝናል! ለጋስ እጁ ለሁሉ ይዘረጋል።

✎ #ታታ_አፍሮ /ነፃ ብዕር/
1.4K views15:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-21 18:26:13
ይህ የዘዳዊት ቴዎድሮስ መልክ ነው...
እነሆ ከተወለደ ዛሬ አንድ ወር ከሰባት ቀን ሆነው!
553 views15:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-27 19:02:46
ለውዴ ውዱ ነሽ

በጎደለ ሞልተሽ በጠፋው ተክተሽ
ሲዝል አበርትተሽ ግራውን ደግፈሽ
የብቸኝነት ጉዞውን በጥንድ ቀይረሽ
ባብሮነትሽ አጅበሽ፤
ሙሉ አደረግሽው መልኩን አሳቅፈሽ
እራሱን ደግመሽ፣
እራስሽን ደግመሽ።

መኑ ከመ ሄዋን እንደ ሚካኤል እናት፣
መኑ ከመ ሄዋን እንደ የማርያም እናት፣
መኑ ከመ ሄዋን እንደ የማሁስ እናት፣
መኑ ከመ ሄዋን እንደ ዘዳዊት እናት?
ሁሌም አብራው ያለች እየሆነችው ብርታት
ለብላቴናው ክብሩ ለልቡም ዘውድ ናት።

እንደ ግጥሜ ርዕስ እንደ ስንኝ ቋጠሮ
እንደ ጠቢብ ቅኔ እንደ ፀሐይ ኑሮ፤
ልብሽ ብሩህ ነው ዘውትር የሚፈካ
መልክሽ በለስ ነው ውዴ ባንቺ 'ረካ።

የሰጠሽው ፀጋ እንደ ሰማይ መና፤
እንደ ምድር ሃመልማል የፈካ ነውና
ልቡን ፍቅር ሞላው ደስታውም አበበ
ለውዴ ውዱ ነሽ በመልክሽ ተዋበ!

እንደ ከዋክብ ብዙ እንደ ጀምበር ውብ
አንድ ሰው እልፍ ነው ከተቸረው ልብ!!
አንድ ሳለሽ ብዝተሽ ሁሉን የሆንሽለት፤
ጤና ይስጥሽ አምላክ ዘለዓለም ኑሪለት!

እንደ ምድር አሸዋ እንደ አባይ ጅረት
አንድ ሰው ብዙ ነው ፍቅር ከሞላበት
በዝተሽ አበዛሽው በርተሽ አፈካሽው
ከፊትም ከኋላም በሁሉም ከበሽው።

✎ #ታታ_አፍሮ /ነፃ ብዕር/

የክቡር ዶ/ር ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) እና የአርቲስት አምለሰት ሙጬ የአብራክ ክፋይ የሆኑት ልጆች 4 ሲሆኑ ሁለት ወንድ እንዲሁም ሁለት ሴቶች ናቸው። ስማቸውም እንደየ የውልደት ቅደም ተከተላቸው፦ ሚካኤል ቴዎድሮስ፣ የማርያም ቴዎድሮስ፣ የማሁስ ቴዎድሮስ እና ዘዳዊት ቴዎድሮስ ይባላሉ።
994 views16:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-07 16:43:31
ከክብር ዶ/ር አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን (Teddy Afro) የተላለፈ የሀዘን መግለጫ።

"በአንጋፋው እና በተወዳጁ የግጥምና የዜማ ደራሲ የክብር ዶክተር አርቲስት አሊ መሐመድ ቢራ ሕልፈተ ሕይወት የተሰማኝን ሐዘን ስገልጽ ጥልቅ በሆነ የሐዘን ስሜት ነው!

የክብር ዶክተር አርቲስት አሊ መሐመድ ቢራ ላለፉት ሃምሳ አመታት በቆየበት የሙዚቃ ሕይወቱ እጅግ በርካታና ተወዳጅ በሆኑ ዘመን ተሻጋሪ ስራዎቹ እና እንዲሁም በአስደናቢ የአዘፋፈን ስልቱ በብዙዎች ዘንድ አድናቆትንና ተወዳጅነትን አትርፏል።

በተለያዪ ጊዚያት ለሌሎች ድምጻዊያን ከሰጣቸው ስራዎቹ መካከል የአንጋፋው ድምጻዊ የክብር ዶክተር ማህመድ አህመድ (ትዝ ትዝ እያለኝ) የተሰኘው ተወዳጅ ሙዚቃው ይጠቀሳል።

ድምጻዊ አሊ ቢራ በስፋት በሚታወቅበት የኦሮሚኛ ሙዚቃ ስልት አጨዋወቱ እስካሁን ወደር ያልተገኘለትና አረብኛን ጨምሮ በተለያዩ ቋንቋዎች የመጫወት ችሎታው ቋንቋውን የማይረዱትን አድማጮቹን ሳይቀር ቀልብ መግዛት የቻለ ሀገራችን ካፈራቻቸው ስመ ጥር አንጋፋ ድምጻዊያን መካከል አንዱ ነበር።

በትላንትናው እለትም በተሰማው ሕልፈተ ሕይወቱ በተፈጠረው ሐዘን ለቤተሰቦቹ፣ ለወዳጅ ዘመዶቹ እንዲሁም ለመላው አድናቂዎቹ መጽናናትን እየተመኘው ፈጣሪ ነፍሱን በአፀደ ገነት እንዲያሳርፍልን ከልብ እመኛለሁ።"

ቴዎድሮስ ካሳሁን
(ቴዲ አፍሮ)
1.6K views13:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-27 20:51:51
1.5K views17:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-27 17:57:29 https://vm.tiktok.com/ZMF8mdCb2
1.9K views14:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-27 16:55:10
በአርቲስት ማዲንጎ አፈወርቅ ድንገተኛ ህልፈተ ህይወት የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን ለመግለጽ እንወዳለን። ከአገራችን ግንባር-ቀደም ሙዚቀኞች መሃል ማዲንጎ አወርቅ አንዱ ነበር። ሳንጠግበው ተለየን። እየወደድነው አጣነው። ባልጠበቅነው ሁኔታ ለሀዘን ዳረገን። ልባችንን ሀዘን ወረሰው። የተከበርክ አርቲስት ማዲንጎ አፈወርቅ ነፍስህን ልዑል እግዚአብሔር ከጻድቃን ጎን ያሳርፍልን።
ለቤተሰቦቹ፣ ለወዳጅ ዘመዶቹ፣ ለመላው የኪነጥበብ አፍቃሪያን፣ ለሙያ ባልደረቦቹ እንዲሁም ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ መጽናናትን እንመኛለን።

ነፍሥ ይማር!
2.1K views13:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-26 20:56:08
እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሠላም አደረሰን።

መስቀል ሀይልነ
መስቀል ፅንእነ
መስቀል ቤዛነ
መስቀል መድሀኒተ ነፍስነ
አይሁድ ክህዱ ንህነሰ
አመነ ወእለ አመነ
በሀይለ መስቀሉ ድህነ።

‹‹መስቀል ኃይላችን ነው፤ መስቀል ጽንአታችን (ጥንካረያችን) ነው፤ መስቀል ቤዛችን ነው፤ መስቀል የነፍሳችን መድኃኒት ነው፤ አይሁድ ካዱ፣ እኛ ግን አመንን፣ ያመነውም በመስቀሉ ኃይል ዳንን›› በማለት የመስቀልን ኃይልነት፣ ፅንዕነት፣ ቤዛነትና መድኃኒትነት ቤተ ክርስቲያናችን አስተምራናለች። ኢትዮጵያዊው ሊቅ ቅዱስ ያሬድም ‹‹መስቀል መልዕልተ ኩሉ ነገር ያድኅነነ እምፀር›› በማለት መስቀል ከሁሉም ነገር በላይ እንደሆነና ከሥጋዊ (ዓለማዊ) ጠላትም ሆነ ከመንፈስ ጠላታችን ከዲያብሎስ ሊያድነን እንደሚችል አስተምሮናል። በዚህም መሠረት ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዓለሙን ሁሉ ከኃጢአት፣ ከፍዳ፣ ከመርገም፣ ለማዳንና ነፃ ለማውጣት ከሰማየ ሰማያት ወርዶ ከቅድስት ድንግል ማርያም ተወልዶ በለበሰው ሥጋ ተሰቅሎ ክቡር ደሙን ያፈሰሰበትን ቅዱስ መስቀል እናከብረዋለን፣ እንወደዋለን፣ እናገነዋለን፣ እንሳለመዋለን፣ በመባረክና በማማተብ ረቂቃን አጋንንትን እናርቅበታለን፣ በመታሸት ከደዌ ሥጋ፤ ከደዌ ነፍስ እንፈወስበታለን፣ የሰውነታችንን ልዩ ልዩ ክፍሎችም በመስቀል ቅርጽ በመነቀስና፣ በሌላውም ቦታ ሁሉ በእንጨትና፣ በድንጋይ ቅርጽ የመስቀል ምልክት በማድረግ የክርስትና እምነት ተከታዮችና፣ በመስቀሉ የምናምን መሆናችንን እንገልጽበታለን። ማቴ፥ ፲፣ ፴፰ እንደተጠቀሰው እኛፐክርስቲያኖች መስቀልን በዚህ መልኩ የምንሸከመውም የጌታችን የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ፍለጋ ለመከተል ነው።  
887 views17:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ