Get Mystery Box with random crypto!

Teddy Afro

የቴሌግራም ቻናል አርማ teddyafronet — Teddy Afro T
የቴሌግራም ቻናል አርማ teddyafronet — Teddy Afro
የሰርጥ አድራሻ: @teddyafronet
ምድቦች: ሙዚቃ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 12.77K
የሰርጥ መግለጫ

ይህ በቴዲ አፍሮ አድናቂዎች የሚመራ የTelegram ድህረ ገፅ ነው። በFacebook በInstagram እንዲሁም በዚሁ በTelegram ሰፋ ያለ ተከታዮችን ያፈራው "Teddy Afro net" ሁሌም ስለቴዲ አፍሮ በታማኝነት ያገለግላሉ። በሁሉም የመገናኛ ብዙሃን /ድህረ-ገፆች/ ትልቅ ድርጅት ሆነን ስለምንወደው #ቴዲ_አፍሮ ለዓለም ህዝብ በቂ መረጃ ተደራሽ እናደርጋለን።
Admin @PoetTataafro

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 5

2022-07-19 20:05:29 https://vm.tiktok.com/ZMNHEttnj/?k=1

"Teddy Afro" የማይነካ አንበሳ...
6.7K views17:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 23:10:08 https://vm.tiktok.com/ZMNaD8ypj/?k=1
2.2K views20:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 13:20:15 በቅድሚያ ጀግናው ልጃችን ቴዲ አፍሮ፦ እንኳን ለኢትዮጵያ ልጇ፥ ለልጆቿም ወንድሞቿ ሆነህ ተወለድክልን። ብዙዎች በዚህ ዓለም ላይ "ከከባድ ነገሮች ውስጥ አንዱ ከባድ ነገር የሚወዱትን ሰው በሚመጥኑ ቃላቶች ለመግለጽ መሞከር ነው" ሲሉ አውቃለሁ። በዚህ ጉዳይ በተወሰነ መልኩ ብስማማም ልቤ ግን አንደበት ከሚገልጸው በላይ ተግባር የሚገልጸው ፍቅር ይልቃል ብሎ ስለሚያምን ይኼን ሰው ለመግለጽ ቸገረኝ ብሎ ከማውራቱ ይልቅ እሱን በእውነተኛ የመውደድ ስሜት መውደዴ ብቻ በቂ ሆኖ ይሰማኛል። እንደ ቴዲ አፍሮ በጀግንነት እና በእርሱ ጽናት ልክ ባይሆንም ጥቂት ነገሮቹን በመውረስ ለአንዲትም ሰከንድ ቢሆን ሀሳቡን ሳልቋወም ከ20 አመታቶች በላይ ከርሱ ጋ ተጉዣለሁ። ይኼ እና ያልገለጽኳቸው እውነታዎች በተግባር የተገለጸውን ፍቅሬን በመጠኑም ቢሆን ይልጻሉ ብዬ አምናለሁ።

ሰውን ለመውደድ ሰው ከመሆን የላቀ ምክኒያት ባያስፈልግም የሰዎች አፍ ግን ስለምን ወደድከው ሲል ዕልፍ ጊዜ ጠይቆኛል። በመጀመሪያ ሰው በመሆኑ እንደ ሁሉ ሰው እንደወደድኩህ በኩራት ተናገርኩ። በመቀጠልም የእርሱን ስብዕናዎች እንዲ እያልኩ መጥቀስ ጀመርኩ። ቴዲ አፍሮን በጣም የወደድኩት ከሌሎቹ በተለየ መልኩ በሙዚቃዎቹ ስለ ፍቅር በጽኑ መንፈስ ስለሚያቀነቅን ነው። እኔ ደግሞ የፍቅርን ኃያልነት የማምን ሰው ነኝ። ፍቅር በእግዚአብሔር ከመወደድ እና እግዚአብሔርን ከመውደድ ይጀምራል። እግዚአብሔርን የሚወድ ሁሉ ሌሎችን ይወዳል። ይኼ የፍቅር ሉዓላዊ /ነጻ/ ህግ ነው።

ታዲያ ስለፍቅር ሌልች አላዜሙም እንዴ ብሉኝ ነጥቤ እሱ አይደለምና ሃሳቤን እንዲህ ስል እቀጥላሉ። ፍቅር ማለት መውደድ ብቻ አይደለም። መፍራት እና ማክበርም ጭምር ነው። በመፍራት የሆነ ማክበር እና አምልኮ ለእግዚአብሔር፥ በማክበር የሆነ መፍራት ደግሞ ለሰው ልጆች እና ለፍጥረት ሁሉ ይገባል። ይኼን መንፈስ የተጎናጸፈ ሰው ደግሞ ታላቁንም ታናሹንም ያከብራል፣ ይወዳል ይፈራልም። መፍራት በሃይለ ቃል ላላመናገር ነው። መፍራት ከላይም ከታችም በማሃከልም ለቆመው ለመታዘዝ መፍቀድን እንደ ሆነ ልብ ይሏል። ከዚህ አንጻር በኪነጥበቡ ዘርፍ እንዲህ ሆኖ ያገኘሁት ይኼንን ሰው ነው። ይኼንን ሰው መውደድ፣ ማክበር፣ መታዘዝ እንዲሁም እንደ ታላቅ ወንድም ማየት ፍጹም ጤናማ ከሆነ ልብ እና አዕምሮ የሚመነጭ ነው። በእግዚአብሔርም ዘንድ መውደድ ለሰው ልጆች ሁሉ የቀረበ የክርስቶስ አዋጅ ነውና ይኼን ሰው በመውደዴ ደስተኛ ነኝ እላለሁ በኩራት።

በመጨረሻም ለኢትዮጵያ አገራችን እና ለወገኖቻችን ላበረከተው አስተዋጽኦ ከፍ ያለ ምስጋናዬን ለማቅረብ እወዳለሁ። የኪነጥበብ ሙያው እንዲከበርና እንዲታፈር ጭምር የእርሱ በዚህ ደረጃ መግዘፍ ዋናውን ሚና ተጫውቷል ለዚህም ትልቅ ክብርን እሰጠዋለሁ። ቴዲ አፍሮ በሚወዱት፣ በሚጠሉት፣ በሚተቹት /በሚቀኑበት/ ባለሙያዎች ልብ ውስጥ ሳይቀር ትልቅነቱ ሊገዝፍ የቻለው እግዚአብሔርን ይዞ በመቆሙ ስለሆነ እግዚአብሔር እስከ ፍጻሜው ድረስ አብሮት ይሆን ዘንድ መልካም ምኞቴ ነው።

ትንሽ ልከትብ ፈልጌ ብዕሬን አነሳሁት ግን ትልቅ ሰው ሆነብኝ እና በትንሽ አንቀጽ ልቋጨው ተሳነኝ። አሁንም ብዙ ጠልቄ መውጫው እንዳይጠፋኝ የልቤን ሀሳብ ገትቼ ምኞቴን ገልጬ ልተው። በእውነተኛ መውደድ የምወድህ የክቡር ዶ/ር አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን /ቴዲ አፍሮ/ መልካም ልደት ይሁንልህ። የሚወድህ ልቤ የጸነሰውን ሀሳብ በሚያከብርህ ብዕሬ እንዲህ ከተብኩት።

✎ #ታታ_አፍሮ /ነፃ ብዕር/
2.8K views10:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 23:11:09 መልካም ልደት ለቴዲ አፍሮ

https://vm.tiktok.com/ZMN5pCtTf/?k=1
3.2K views20:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 19:46:30
በክቡር ዶ/ር አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን /ቴዲ አፍሮ/ የህይወት ጉዞ ላይ የሚያውጠነጥን "ቴዎድሮስ እስኪነግሥ" የተሰኘ አዲስ መጽሐፍ ከሀምሌ 20/2014 ዓ.ም ጀምሮ ለአንባቢያን ይቀርባል።

ከመጽሐፉ...

"...ቴዲ በሥነ-ግጥሙ ዘርፍ የነበረው ሀሳብን በተመጠነ ቃል የመግለጽና ለሰዎች በድምጹ የማቅረብ ልምዱ አድጎና ጎልብቶ እዚህ ደረጃ መድረሱ እጅግ አስገርሞኛል፡፡ ስለ ኢትዮጵያ ህዝቦች በጋራ የመኖር ውበት የሚገልጽባቸው መንገዶች ልዩ ናቸው፡፡ አርቲስቱ ከፖለቲካ ነጻ መሆኑና ቀደምት ሀገሪቷን በከፍታ ላስጓዟት መሪዎች የሚሰጠው ክብር ከድምጻውያን መካከል በግንባር ቀደምትነት የሚያሰልፈው ነው፡፡"

የቴዲ አፍሮ የቀድሞ አማርኛ መምህር ስለሺ ከበደ
4.2K views16:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-22 16:05:01
የኢትዮጵያ ሙዚቃ በዓለም ጆሮዎች...

ድምጻችን በዓለም እየተሰማ ነው። "ናዕት" አርባ ሺ Subscribers፣ ከ90 ሺህ በላይ መውደዶች እና ከአንደ ሚሊየን በላይ ተመልካቾችን በአስራ ሰባት /17/ሰዓታት ውስጥ ብቻ አግኝቷል። ይኽ የህዝብ ድምጽ የሆነው የክቡር ዶ/ር ቴዎድሮስ ካሳሁን /ቴዲ አፍሮ/ አዲስ ሙዚቃ ዓለማችን ላይ በዚህን ሰዓት በስፋት እየተደመጡ ካሉ ሙዚቃዎች ውስጥ የሁለተኛ ደረጃነትን የያዘ ሲሆን በዘመናዊ የሙዚቃ ማድመጫ ድረገጽ /You Tube/ ላይ ከእራሱ ከቴዲ አፍሮ በቀር በኢትዮጵያ በዚህ ፍጥነት የተደመጠ ሙዚቃ በፍጹም የለም።

ናዕት /እያመመው ቁ፪/ ሙዚቃ ገና 24 ሰዓት ሳይሞላው በዚህ ፍጥነት በዓለም ደረጃ መዳረስ መቻሉ እጅግ ሊደነቅ የሚገባ ክስተት ነው። የህዝብ ድምጽ ሁሌም ኃያል ነው። ናዕት የኢትዮጵያውያን ድምጽ ነው። እንደ አገር ከገባንበት ማጥ ለመውጣት እንደ ዜጋ ከተረገጥንበት ትቢያ ለመነሳት እንዲህ ያሉ አስገምጋሚ ድምጾች ያሹናል። እንደ ሰማይ ማስገምገም እንደ ነጋሪት ጉሰማ የአምባ ገነኖችን ልብ የሚያሸብር የነፍስ ጩኸት።

✎ #ታታ_አፍሮ /ነፃ ብዕር/

አሁንም ከፍ ብሎ ይደመጥ

የሚያዜም ይመስላል ሲያጣጥር ተጨንቆ
ውስጡን ሲሰብቅለት ኡ... እያለ ማሲንቆ
ኡ...ኡ...



9.9K viewsedited  13:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-19 20:08:13
የክቡር ዶ/ር ቴዎድሮስ ካሳሁን /ቴዲ አፍሮ/ አንተ ጽኑ እና ጀግና አባት ነህ። ከአብራኮችህ ለወጡ ልጆችህ ብቻ ሳይሆን ለብዙዎች ምርጥ አባት ሆነህ በመቆምህ ከልብ እናመሰግንኃለን።

የአገሬ ማህጸን እንዳንተ አይነት ቅን ሰዎችን ስለምታፈራ ክብር ሊሰማት ይገባል።

መልካም የአባቶች ቀን ይሁንልህ!

በጽኑ መውደድ እ...ን...ወ...ድ...ኃ...ለ...ን!
9.5K views17:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-09 21:08:34
እናት ሀገራችን ኢትዮጵያ ሆይ አርማሽ ከፍ ብሎ ይውለብለብ! በዓለም አደባባዮች ሁሉ የድልሽ ዜና በድምቀት ይነገር! ውድቀትሽን ለመስማት የናፈቁ ጆሮዎች አሸናፊነትሽን ያድምጡ!!!
12.0K views18:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-09 20:08:47 ዋልያ
10.0K views17:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-09 20:08:07 "ባራ ባራ ሳተናው ዋልያ የኮረብታው ብርቁ
ከዳሽን ተራራ ጫፉ ላይ ያረገው ይታይ ሰንደቁ..."
9.6K viewsedited  17:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ