Get Mystery Box with random crypto!

የተደራጀ ውሸት። የክቡር ዶ/ር አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) እዮሪካ የተሰኘ አልበም | Teddy Afro

የተደራጀ ውሸት።

የክቡር ዶ/ር አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) እዮሪካ የተሰኘ አልበም ሊለቅ ነው የሚል የሀሰት ዜና Ethio Telecom ከ1.2 ሚሊየን በላይ ተከታይ ባለው በህጋዊ የፌስቡክ ገጹ ላይ ከለቀቀ በኋላ የተለያዩ ግለሰቦች ሀሳቡን እስከ አሁኗ ሰዓት ድረስ እየተቀባበሉት ይገኛሉ። እርግጥ ነው ቴዲ አፍሮ እጅግ የሚደንቁ ዘፈኖች የተከማቹበት ክር እያዘጋጀ መሆኑን አውቃለሁ። ከሰማኋቸው ዘፈኖች ውስጥ አብዛኛዎቹ አሁንም ድረስ በልቤ ውስጥ የሚሯሯጡትን ዜማዎቹን በማስብ ጊዜ፥ ልክ በረሃ ላይ ደክሜ እንደ ነብዩ ዮናስ ጥላ አግኝቼ ያረፍኩ ያህል ደስ እሰኛለሁ። ከዜማዎቹ ትዝታ ስላቀቅ ደግሞ ዳግም እንደ ጥላዋ መጠውለግ ስሜቴን ሁሉ ብል ይወረዋል።