Get Mystery Box with random crypto!

ቀኑ ደርሶ በሀገር አንጻራዊ ሰላም ነግሶ ይኼንን የሙዚቃ ክር ከክቡር ዶ/ር አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳ | Teddy Afro

ቀኑ ደርሶ በሀገር አንጻራዊ ሰላም ነግሶ ይኼንን የሙዚቃ ክር ከክቡር ዶ/ር አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) እስክንታደል ድረስ የኔም ጉጉት ትልቅ ነው። ቴዲ አፍሮም መቼ እንደሚለቅ በጠየኩት ጊዜ የሀገራችን ሁኔታ ጥሩ በሆነ ጊዜ ነበር ያለኝ። ቴዲ አፍሮን በተመለከተ ለሌላው ጊዜ እንዲህ ያሉ መረጃዎች ከየትም በኩል ብትሰሙ ታማኝ ምንጮችን እንድትፈትሹ፥ በተለይም የቴዲ አፍሮን ህጋዊ የፌስቡክ ገጽ እና Teddy Afro Net የተሰኘውን ገጾች እንድትከታተሉ በትህትና ለመጠቆም እወዳለሁ።

ወደ ኢትዮ ቴሌኮም እንመለስ። ስለ ቴዲ አፍሮ አልበም የጠቀሰውን ዜና ከሰዓታት በኋላ ከገጹ ላይ ያስወገደ ቢሆንም ከድርጅቱ እንዲህ ያሉ የሀሰት ዜናዎች በሀገር ደረጃ ሲያሰራጩ ይኽ የመጀመሪያው ባይሆንም ህዝብ በሚያከብረው እና ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ባለው አርቲስት ስም አንደ የሀገር በቀል ድርጅት የሀሰት ዜናውን ሀላፊነት በጎደለው መልኩ ማሰራጨቱ ትልቅ ነውር መሆኑን ለድርጅቱ የበላይ አመራሮች እና ለሚመለከተው አካል ስጠቁም ተግባራቸው እንደየ ሁልጊዜ ህዝብን ያላከበረ በመሆኑ በድርጅቱ ዳግም የሆነ ትልቅ ሀፍረት እንደተሰማኝ በመጠቆም ጭምር ነው። ሌላ አማራጭ ቢኖረንና ከዚህ ተቋም ጋ ለዘለዓለም ደንበኝነታችንን ብናቋርጥም በተለየ መልኩ ትልቅ ደስታ እንደሚሰማኝ በዚሁ ለመጠቆም እወዳለሁ።

በስተ-መጨረሻም በሰዋሰው መልቲሚዲያ ሙዚቃዎቻቸውን ለለቀቁ የሀገራችን ዘፋኞች በጠቅላላ እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት እወዳለሁ። ከዚሁ ጋ በማያያዝ ቴዲ አፍሮ እገሌ ላይ አልበም ደረበ (ሊደርብ ነው) የሚል ስጋት ያደረባችሁ ግለሰቦችም ሆናችሁ ሌሎች አካሎች ይኼንን የሀሰት መረጃ በማመናችሁ ብቻ ይሄ ስጋት ሊሰማችሁ እንደቻለ በመረዳት ያሞኛችሁን ድርጅት ወቅሳችሁ የሀገሬ ክር እስኪለቀቅ በእጃቹ የደረሱትን ዘፈኖች አድምጡ ስል እመክራለሁ።

#ታታ_አፍሮ (ነፃ ብዕር)