Get Mystery Box with random crypto!

#ETHIOPIA ሚያዝያ 7/2009 ዓ.ም ኢትዮጵያ የተሰኘው የክቡር ዶ/ር አርቲስት ቴዎድሮስ ካ | Teddy Afro

#ETHIOPIA ሚያዝያ 7/2009 ዓ.ም

ኢትዮጵያ የተሰኘው የክቡር ዶ/ር አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) ነጠላ ዜማ በህጋዊ የዩትዩብ ቻናሉ ከተለቀቀ ዛሬ ስድስተኛ አመቱን ደፈነ። ይኼ ሙዚቃ ሚያዝያ 7/2009 ዓ.ም ምሽት ላይ ነበር የተለቀቀው። በተለቀቀ በሰዓታት ውስጥ ግን ድፍን አዲስ አበባ ውስጥ ሙዚቃው በመዳረሱ ከተማይቱ አዲስ ዘመንን የምታከብር ያህል በየ ስፍራው እንደ ባህላዊ ዘፈን ይኼ ሙዚቃ በስፋት ሲደመጥ አነጋ።

በዕለቱ በመዲናይቱ የተለያዩ ስፍራዎች እየተዘዋወርኩ ለሊቱን ሙሉ ስሜቱን ለማጣጣም የሞከርኩ ሲሆን በየ ቦታው የሚታየው የህዝቡ ስሜት እጅግ ልዩ ነበር።

ይህ ኢትዮጵያ የተሰኘ ተወዳጅ ሙዚቃ ከተለቀቀ በስድስት አመታት ውስጥ ይሄንን መረጃ እስከ-ለጠፍንበት ሰዓት ድረስ በዩትዩብ ብቻ ሀያ አራት ሚልየን ዘጠኝ መቶ አርባ ሶስት ሺ አንድ መቶ አድማጮችን አግኝቷል። ይኼ ደግሞ በኢትዮጵያ የሙዚቃ ታሪክ ያለ ተንቀሳቃሽ ምስል እጀባ ብዙ ተመልካቾችን ያገኘ የመጀመሪያው ነጠላ ዜማ ነው። በተጨማሪም ባለፉት አመታቶች ውስጥ በዓለም አቀፍ ደረጃ በተለያዩ የሙዚቃ ሰንጠረዦች ላይ ክብረ-ወሰኖችን የሰበረ የዓለማችን ተወዳጅ ሙዚቃ ለመሆን በቅቷል።

ይኽ ሙዚቃ በወቅቱ በፈጠረው ትልቅ የሚዲያ ንቅናቄ የዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ከወትሮው በተለየ መልኩ ለቴዲ አፍሮ ትልቅ ትኩረት እንዲሰጡት ያስቻለ ከመሆኑም በላይ ዛሬም ድረስ BBC, CNN, Al Jazeera, CGTN Africa, BBC Africa, የቻይናው CC TV እና ሌሎችም ዓለም አቀፍ የመገናኛ ብዙሃኖች ቴዲ አፍሮ በአፍሪካ እና በዓለም ላይ በሚገኙ አድናቂዎቹ ባለው ሰፊ ተቀባይነት ምክኒያት ስለሱ መዘገብ አትራፊ መሆኑን ተረድተው ስለሱ አዳዲስ መረጃዎችን መዘገብ ቀጥለዋል።

@TataAfro_official (ነፃ ብዕር)