Get Mystery Box with random crypto!

Shega info

የቴሌግራም ቻናል አርማ shegainfom — Shega info S
የቴሌግራም ቻናል አርማ shegainfom — Shega info
የሰርጥ አድራሻ: @shegainfom
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 12.69K
የሰርጥ መግለጫ

▪ይህ የሸጋ info የቴሌግራም ቻናል ነዉ ▪ አስተማሪና ቁምነገር አዘል መረጃዎች በውብ አቀራርብ ለናንተ ይደርሳል #join በማረግ ቤተሰብ ይውኑን::

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-09-21 06:39:35 ትላንት አልፏል!

ፈጣሪ ጊዜን ከፈጠረበት አንዱ ምክንያት 'ድሮ' የሚባል ላጠፋሀቸው ጥፋቶች ሁሉ መቀበሪያ ጉድጓድ ለማዘጋጀት ነው። ታዲያ እዛ የመቃብር ስፍራ ምን ታረጋለህ ወዳጄ? ለምን ስለትላንት እያሰብክ ራስህን ታስጨንቃለህ?! ወዳጄ አሁንን መኖር ጀምር! አጠገብህ ያለውን በረከት እይና ተመስገን በል፤ ተደሰት!
3.0K views03:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-20 19:56:17 1 ሩሐማ፦ምሕረት ማለት ነው።
2 ዮዳሔ፦እግዚአብሔር ያውቃል ማለት ነው።
3 ቴዎፍሎስ፦የእግዚአብሔር ወዳጅ ማለት ነው።
4 ኑኃሚን፦ደስታየ ማለት ነው።
5 ናትናኤል፦የእግዚአብሔር ስጦታ ማለት ነው።
6 አዛሄል፦እግዚአብሔር ያያል ማለት ነው።
7 ኢዮስያስ፦እግዚአብሔር ይደግፋል ማለይ ነው
8 ኢዩኤል፦እግዚአብሔር አምላክ ነው ማለት ነው።
9 በርናባስ፦የመጽናናት ልጅ ማለት ነው።
10 ሶፎንያስ፦እግዚአብሔር ሰውሯል/ጠብቋል ማለት ነው።
11 ሕዝቅኤል፦እግዚአብሔር ብርታትን ይሰጣል ማለት ነው።
12 ኬልቅያስ፦እድል ፈንታየ እግዚአብሔር ማለት ነው
13 ሳሙኤል፦እግዚአብሔር ሰማኝ ማለት ነው።
14 ሚኪያስ፦ እንደ እግዚአብሔር ያለ ማን ነው! ማለት ነው።
15 ሆሴዕ፦እግዚአብሔር ያድናል ማለት ነው።
16 ሔዋን፦የሕያዋን ሁሉ እናት ማለት ነው።
17 ሕዝቅያስ፦እግዚአብሔር ኃይሌ ነው ማለት ነው።
18 መልከጼዴቅ፦የሰላም ንጉሥ ማለት ነው።
19 ሚልኪያስ፦መልእክተኛየ ማለት ነው።
20 ሣራ፦ልዕልት ማለት ነው።
21 ስምዖን፦ሰማ ማለት ነው።
22 ብንያም፦የቀኝ እጄ ልጅ ማለት ነው።
23 ናሆም፦መጽናናት ማለት ነው።
24 ናታን፦ እግዚአብሔር ሰጥቷል ማለት ነው።
25 አልዓዛር፦እግዚአብሔር ረድቷል ማለት ነው።
26 አስቴር፦ኮከብ ማለት ነው፣
27 አቤሜሌክ፦የንጉሥ አገልጋይ ማለት ነው።
28 አቤሴሎም፦አባቴ ሰላም ነው ማለት ነው።
29 አብድዩ፦የእግዚአብሔር አገልጋይ ማለት ነው።
30 አብራም፦ታላቅ አባት ማለት ነው።
31 አብርሃም፦የብዙዎች አባት ማለት ነው
32 አኪያ፦እግዚአብሔር ወንድሜ ነው ማለት ነው።
33 አክዐብ፦የአባት ወንድም ማለት ነው።
34 ባሮክ፦ቡሩክ ማለት ነው።
35 አዳም፦መልካሙ ማለት ነው።
36 ኢሳይያስ፦ እግዚአብሔር ደኅንነት ነው ማለት ነው።
37 ባርቅ፦መብረቅ ማለት ነው።
38 ኢያሱ፦እግዚአብሔር አዳኝ ነው ማለት ነው።
39 ኢዮሳፍጥ፦እግዚአብሔር ፈርዷል ማለት ነው።
40 ኢዮራም፦እግዚአብሔር ከፍ ከፍ አለ ማለት ነው።
41 ኢዮርብዓም፦ሕዝቡ እየበዛ ይሄዳል ማለት ነው።
42 ቤተልሔም፦የእንጀራ ቤት ማለት ነው።
43 ኢዮአስ፦እግዚአብሔር ሰጥቷል ማለት ነው።
44 ኢዮአቄም፦እግዚአብሔር አቆመ ማለት ነው።
45 ኢዮአብ፦እግዚአብሔር አባት ነው ማለት ነው።
46 ኢዮአታም፦እግዚአብሔር ፍጹም ነው ማለት ነው።
47 ኢዮአካዝ፦እግዚአብሔር ይዟል ማለት ነው።
48 ኤልሳዕ፦እግዚአብሔር ደኅንነት ነው ማለት ነው።
49 ኤልያስ፦እግዚአብሔር አምላክ ነው ማለት ነው።
50 ኤልያቄም፦እግዚአብሔር ያስነሳል ማለት ነው።
51 ኤዶም፦ቀይ ማለት ነው
52 እስራኤል፦ከእግዚአብሔር ጋር ይታገላል ያሸንፍማል ማለት ነው።
53 ኤልሳቤጥ፦እግዚአብሔር መሐላየ ነው ማለት ነው።
54 ኤልሻዳይ፦ሁሉን ቻይ አምላክ ማለት ነው።
55 ሀሌሉያ፦እግዚአብሔርን አመስግኑ ማለት ነው።
56 ሰሎሞን፦ሰላማዊ ማለት ነው።
57 ኬብሮን፦ኅብረት ማለት ነው
58 አዛርያስ፦እግዚአብሔር ረድቷል ማለት ነው።
59 ኤደን፦ደስታ ማለት ነው።
60 ዖዝያን፦እግዚአብሔር ኃይሌ ነው ማለት ነው።
61 ዘካርያስ፦እግዚአብሔር ያስታውሳል ማለት ነው።
62 ይሳኮር፦ ዋጋዬ ማለት ነው
63 ይዲድያ፦በእግዚአብሔር የተወደደ ማለት ነው።
64 ዮሐናን፦እግዚአብሔር ጸጋ ሰጪ ነው ማለት ነው።
65 ዮሐንስ፦እግዚአብሔር ጸጋ ነው ማለት ነው።
66 ዮሴፍ፦ይጨምር ማለት ነው።
67 ዮናስ፦ርግብ ማለት ነው።
68 ዮናታን፦እግዚአብሔር ሰጥቷል ማለት ነው።
69 ዮአኪን፦እግዚአብሔር ያቆማል ማለት ነው።
70 ዮካብድ፦እግዚአብሔር ክብር ነው ማለት ነው።
71 ምናሴ፦ማስረሻ ማለት ነው።
72 ዮፍታሔ፦እግዚአብሔር ይከፍታል ማለት ነው።
73 ዲቦራ፦ንብ ማለት ነው።
74 ዳንኤል፦እግዚአብሔር ፈራጅ ነው ማለት ነው።
75 ጎዶልያስ፦እግዚአብሔር ታላቅ ነው ማለት ነው።
76 ጽዮን፦አምባ ማለት ነው።
77 ጳውሎስ፦ብርሃን ማለት ነው።
78 ሴት፦ምትክ ማለት ነው።
79 ጴጥሮስ፦አለት ማለት ነው።
80 ሄኖክ፦ታደሰ ማለት ነው።
81 ኄራኒ፦ሰላም እና ፍቅር ማለት ነው።
91 ሐና፦ጸጋ ወይም ስጦታ ማለት ነው።
92 ሮቤል፦እነሆ ወንድ ልጅ ማለት ነው።
93 ኤርምያስ፦እግዚአብሔር ከፍ ያደርጋል ማለት ነው።
94 ሮብዓም፦ሕዝብ ይብዛ ማለት ነው።
95 ማራናታ፦ጌታ ሆይ ና ማለት ነው።
96 ቤቴል፦የእግዚአብሔር ቤት ማለት ነው።
97 ቄርሎስ፦የተመረጠ ምርጥ ማለት ነው።
98 እስጢፋኖስ፦አክሊል ማለት ነው።
99 ሳውል/ሳኦል፦ከእግዚአብሔር የተለመነ ማለት ነው።
100 ሴዴቅያስ፦የእግዚአብሔር ጽድቅ ማለት ነው።
join @shegainfom
3.4K views16:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-20 07:09:26 #ውጤታማ_የሚያደርጉህ_3ቱ_ምላሾች

የተፈጠረውን ነገር መቀየር ሲያቅትህ የምትሰጠውን ምላሽ እንዴት አድርገህ መቀየር ትችላለህ?

#1_ባለህበት_የምትችለውን_አድርግ

ባለህበት ቦታ ላይ ለመሆን የምትችለውን ሁሉ ነገር አድርግ፡፡ ምክንያቱም ብዙውን ጊዜ የደስታ እና የሠላም ምስጢሩ አሁን ያለውን ሁኔታ እንዲህ ነው ሊሆን የሚገባው ብሎ ከማሰብ ፈንታ እንደሆነ ይሁን ብሎ በመተው ከሁኔታው የቻሉትን ያህል መጠቀም ነው፡፡

#2_ፈጽሞ_አትጸጸት

ለተሳሳቱ ሰዎች ባሳየኻቸው ደግነት እና ክብር ሳቢያ ፈጽሞ እንዳትጸጸት፡፡ የአንተ ባህሪ ስለ አንተ ሁሉንም ነገር ሲናገር፣ የእነርሱ ባህሪ ስለ እነርሱ ከበቂ በላይ ይናገራል፡፡ በግርማ . . . ቀና ብለህ አንተ ወደፊት ቀጥል. . .

#3_መልቀቅን_ተማር፡፡

የተጋበዝከው ክርክር ላይ ሁሉ መታደም አይገባህም፡፡ ለጊዜህ፣ ለእውነተኛ ግንኙነቶችህ እና ከሀሉም በላይ ለአእምሮህ ሰላም ዋጋ የምትሰጥበትን ቦታ ለራስህ ስጥ፡፡ ምክንያቱም ሌላው ሌላው ነገር ውሎ አድሮ ብዙም ትርጉም የለውም፡፡

እውነቱ ይነገር ካልክ ያለፈ አጸፋዊ ምላሽ ያለመስጠት ችሎታ፣ ወይም ነገሮችን በግል እንደተቃጣ ጥቃት አድርጎ ባለመውሰድ፣ አእምሮን ሁሌም ንጹህ በማድረግ እና ልብን በሰላም ላይ በማሳረፍ ሊቆጣጠሯቸው በማይችሏቸው ሁኔታዎች ውስጥ ሳይቀር ጽኑ አቋምን እንደያዙ ለመዝለቅ ይረዳል፡፡

#የስኬት_አቡጊዳ መጽሐፍ
3.5K views04:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-19 18:06:58 #ወዳጄ_ሆይ ..
#ከምትፈልገው_ይልቅ_የተሰጠህ_ይበልጣል !

የሰው ልጅ ከመመኘትና ከመፈለግ የቦዘነበት የአፍታ ንቃተ-ህሊና ህይወት ኖሮት አያውቅም! ሰው በፍላጎቱ ዛቢያ ብቻ የሚሽከረከር ፍጡር ነው!

የምትፈልገውን ነገር ለአምላክህ በዕምነት ሰጥተኸው እንደሚሰራለህ አምነህ ዞር አትልም!ያለማቋረጥ መጠየቅን እንጂ በተቀበልከው መደሰትና ማመስገንን ረስተሃል! ወዳጄ ሆይ የተሰጠህን አስተውል !

#ወዳጄ_እውነቱን_ልንገርህ ......
የጥያቄህ ብዛት ስጦታህን ጋርዶብህ እንጂ፣ ያለህን አመስጋኝ ሳይሆን የሌለህን ናፋቂ ሆነህ እንጂ፣የፍላጎትህ ባህር የበረከትህን ውቂያኖስ አስንቆህ እንጂ፣ከምኞትህ ግልቢያ ለአፍታ ቆም ብለህ ብታስብ...

#ከምትፈልገው_ይልቅ ....
#የተሰጠህ_እንደሚበልጥ_ማስተዋል_ከባድ_አይሆንብህ
ም !

እራስህን እንደማትወደው እንደማታከብረውና እንደማትሆነው ስታስብ ከማይመረመረው ፈጣሪ ጋር እየተደራደርክ ነውና ቆም ብለህ አስብ።

ሰዎች ከሚሉህ በላይ ፈጣሪ ሲፈጥርህም ምክንያት አለውና የሌለህን ትተህ ያለህን ዋጋ ስጥ። በሌለህ ነገር ስለምታገኘው ሳይሆን ባለህ ነገር ስለምትለውጠው ተመራመር።

በሌለህና ባልተጨበጠው ነገር ትልቅ ነገር ለመስጠት ከማሰብ ይልቅ
ባለህ ነገር ትንሽ ነገር ለመስጠት ሞክር። ያኔ አንተ ውስጥ የተደበቀው ከሌሎች የተለየው ድንቅ ፍልቃቂ ማበብ ይጀምራል።

ብርሀንህ በዓለም ሁሉ ይሰፋል።በምድር ላይ በኖርክበት ዘመን ሁሉ ዘመንህ የጣፈጠ ይሆንልሀል።
ፈጣሪ ሆይ... የማግኘት ምስጢሩ ማመስገ

join @shegainfom
3.9K views15:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 07:24:58
ያንተ ተስፋ ማነው?!

እንደ አንተ ጭንቀትና ሀሳብ ቢሆን ዛሬን ማየት የማይታሰብ ነበር፤ ያንን ጊዜ ማለፍ ቅዠት ነበር፤ ግን አለፍከው፤ ያልገመትከው ሁሉ ሆነ አንተ ተስፋ ቆርጠህ ስትጨርስ ፈጣሪ ጀመረ። ያንተ ተስፋ የዚህ አለም ተለዋዋጭ ነገር አይደለም! ያንተ ተስፋ የማይለወጠው፣ በዘመናት የማያረጀውና የማያልፈው ፈጣሪህ ነው!

አስደሳች ሰንበት ተመኘንላችሁ
@shegainfom
2.8K views04:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 19:12:28 ደም ለማን ይስጡ፤ ከማንስ ይቀበሉ?

የደም አይነት: A+
※ለ A+, AB+ ይሰጣል።
※ከ A+, A-, O+, O- ይቀበላል።

የደም አይነት: O+
※ለ O+, A+, B+, AB+ ይሰጣል።
※ከ O+, O- ይቀበላል።

የደም አይነት: B+
※ለ B+, AB+ ይሰጣል።
※ ከ B+, B-, O+, O- ይቀበላል።

የደም አይነት: AB+
※ ለ AB+ ብቻ ይሰጣል።
※ ከሁሉም ይቀበላል።

የደም አይነት: A-
※ ለ A+, A-, AB+, AB- ይሰጣል።
※ከ A-, O- ይቀበላል።

የደም አይነት: O-
※ ለሁሉም ይሰጣል።
※ከ O- ይቀበላል።

የደም አይነት: B-
※ለ B+, B-, AB+, AB- ይሰጣል።
※ከ B-, O- ይቀበላል።

የደም አይነት: AB-
※ ለ AB+, AB- ይሰጣል።
※ ከ AB-, A-, B-, O- ይቀበላል።
አንብባችሁ ሼርርርር
@shegainfom
ፍቅር : ሰላም : ለምድራችን
3.4K views16:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 20:42:32 ▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰
የ2015 ዓ.ም የአጽዋማትና የበዓላት ማውጫ
▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰
፩. ዘመን፡ ዘመነ ሉቃስ
፪. አዲስ ዓመት፣ ርዕሰ ዓውደ ዓመት፡ እሁድ መስከረም 1
፫. በዓለ መስቀል፡ ማግሰኞ መስከረም 17
፬. ጾመ ጽጌ፡ ሐሙስ መስከረም 26
፭. ጾመ ነቢያት (ጾመ ልደት)፡ ሐሙስ ኅዳር 15
፮. በዓለ ልደት፡ ቅዳሜ ታህሳስ 29
፯. ጾመ ገሃድ (ጋድ፣ ጾመ ድራር ጥምቀት)፡ ረቡዕ ጥር 10
፰. በዓለ ጥምቀት፡ ሐሙስ ጥር 11
፱. ጾመ ነነዌ፡ ሰኞ ጥር 29
፲. ዐቢይ ጾም፡ ሰኞ የካቲት 13
፲፩. በዓለ ደብረ ዘይት፡ እሁድ መጋቢት 10
፲፪. በዓለ ሆሳዕና፡ እሁድ ሚያዝያ 1
፲፫. በዓለ ስቅለት፡ ዓርብ ሚያዝያ 6
፲፬. በዓለ ትንሳኤ፡ እሁድ ሚያዝያ 8
፲፭. ርክበ ካህናት፡ ረቡዕ ግንቦት 2
፲፮. በዓለ ዕርገት፡ ሐሙስ ግንቦት 17
፲፯. በዓለ ጰራቅሊጦስ፡ እሁድ ግንቦት 27
፲፰. ጾመ ሐዋርያት፡ ሰኞ ግንቦት 28
፲፱. ጾመ ድኅነት፡ ረቡዕ ግንቦት 30
፳. ጾመ ፍልሰታ፡ ሰኞ ነሐሴ 1
፳፩. በዓለ ደብረ ታቦር፡ ቅዳሜ ነሐሴ 13
፳፪. የእመቤታችን በዓለ ዕርገት፡ ማግሰኞ ነሐሴ 16
፳፫. የወርኃ ጳጉሜን ዕለታት ብዛት፡ 5
▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰

የዘመናት ባለቤት ቅዱስ አምላካችን ልዑል እግዚአብሔር ቀሪዎቹን ዕለታት በሰላምና በጤና አስፈጽሞና አሳልፎ ከዘመነ ማርቆስ ወደ ዘመነ ሉቃስ፣ ከ2014 ዓ.ም ወደ 2015 ዓ.ም በሰላምና በጤና ያሻግረን፤ አሜን። ለይኩን።
Join @shegainfom
3.8K viewsedited  17:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 20:36:41
“በሰው ዘንድ የማይቻል በእግዚአብሔር ዘንድ ይቻላል።”
— ሉቃስ 18፥27
•••
በሕይወታችን ውስጥ የሚያጋጥመን ችግርና መከራ ምን ያህል እንደሚጎዳና ምን ያህል ከባድ እንደሆነ አውቃለሁ። ችግር ደስታን ይነጥቃል፣ እንቅልፍ ይነሳል እንዲሁም እረፍት ያሣጣል።

ነገር ግን በፍጹም አትጨነቅ ከእንግዲህ ወዲህ አይቆይም እግዚአብሔር ያየዋል፣ እርሱም የልብህን ጩኸት ሰምቶሃል። መከራው አንተን ሊሰራህ እንጂ ሊያጠፋህ አልመጣም።

እግዚአብሔር በሚያጋጥመን ማንኛውም መከራና ችግር ሁሉ እርሱ ከእኛ ጋር እንደሚሆንና እንደሚያሻግረን ቃል ገብቶልናል። ስለዚህ ችግርህን አትሰውር ይልቁንም ለፈጣሪህ ስጠው፣ በእራስህ ለመወጣት አትችልም ግን ሁሉን ቻዩ እግዚአብሔር ሁሉን ይችላል።

ህመምህ እይታህን ሰርቆት ሊሆን ይችላል ግን እግዚአብሔር በአፅናፈ አለሙ ሁሉ እና በእርሱም ውስጥ በሚሆነው ነገር ላይ ሁሉ ፍፁም ቁጥጥር አለው።

እግዚአብሔር እይታህን፣ ደስታህንና ጤናህን ይመልስልሃል፣ አሁን ስለ ህመሙ ማሰላሰልህን አቁምና ስለ እግዚአብሔር ታላቅነትና መልካምነት አስብ።

እግዚአብሔርን እመነው እርሱ የበለጠ ታላቅ ነገር እየሰራ ነው፣ አሁን ያለው ችግር እግዚአብሔር ወደ ታላቅ ደስታ ይለውጠዋል፣ ችግሩ ሊሰራህ እንጂ ሊያጠፋህ አልመጣም !
•••
“እግዚአብሔርንም ለሚወዱት እንደ አሳቡም ለተጠሩት ነገር ሁሉ ለበጎ እንዲደረግ እናውቃለን።”
— ሮሜ 8፥28
•••
☞ 🅢🅗🅐🅡🅔
@shegainfom
3.5K views17:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-24 07:19:35
#ወዳጀ .....
"ሰዎች በአንተ ላይ የዘጉብህን በር አትመልከት፣
በፈጣሪ እጅ ያለውን ቁልፍ ተመልከት፡፡"

ይህን ስትወጣ ተስፋ የተሞላበት ጉዞህም ብሩህ ይሆናልና፡፡
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
ዛሬ ያስለቀሰህ ሰው ነገ የሚያስለቅሰው ሰው አያጣም
ዛሬ የጎዳህ ነገ እሱንም የሚጎዳው
ሰው አያጣም
ምድር ትዞራለች አንተ የሚጠበቅብህ በትዕግስት
መኖር ብቻ ነው።

ሰው የዘራውን ነው የሚያጭደውና የዋህነት አይጎዳም
ስኬት የደስታ ቁልፍ ናት

#ወዳጀ ሆይ ......

እኖራለሁ ብለህ ሥራ፤ እሞታለሁ ብለህ ኑር› ሲባል አልሰማህም?
መውረድን የረሳ ባለ ሥልጣን፣ ሕመምን የረሳ ጤነኛ፣ ድህነትን የረሳ ሀብታም፣ ሞትን የረሳ ነዋሪ፣

ድቀትን የረሳ ጻድቅ፣ ውርደትን የረሳ ክቡር፣

#ወደረሳው ነገር ለመጓዝ እንዴት ይፈጥናል መሰለህ?

ድቅድቁ ጨለማ ያለው ከሻማው ሥር ነው፡፡

"እየጠሉ የወደዱ መስለው ከሚቀርቡ ሀሰተኛ ሰዎች ጋር ከመኖር ብቸኝነት ይሻላል!!!
መልካም ቀን
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°

ሼር፣በማድርግ ብቻ ቤተሰብ ይሁኑ
@Shegainfom
4.4K viewsedited  04:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-22 07:22:13
የአትሌት ሺአለቃ ኃይሌ ገ/ሥላሴ አጭር መልዕክት እናዳምጥ
/ከማኅበረ ቅዱሳን ቲቪ የተወሰደ

"በአትላንታና በሲድኒ ኦሎምፒክ ያገኘሁትን ሜዳልያ ለእንጦጦ ኪዳነ ምህረት ነው የሰጠሁት።
ለኪዳነምህረት ነግሬያት ነው ያሸነፍኩት። ትዳሬንም በተክሊል ያገባሁት ኪዳነ ምህረት ነው።
እመቤቴ በህይወቴ በትዳሬ በስራዬ ሁሌ ብዙ ነገር አድርጋልኛለች። ያሸነፍኳቸው ድሎች ሁሉ የአምላክ እናትና የልጇ የእግዚአብሔር ነው!"
ታላቁ አትሌት ኃይሌ ገብረ ሥላሴ በማህበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን
#መልካም #ኪዳነምህረት
@shegainfo
4.9K views04:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ