Get Mystery Box with random crypto!

“በሰው ዘንድ የማይቻል በእግዚአብሔር ዘንድ ይቻላል።” — ሉቃስ 18፥27 ••• በሕይወታችን ውስጥ | Shega info

“በሰው ዘንድ የማይቻል በእግዚአብሔር ዘንድ ይቻላል።”
— ሉቃስ 18፥27
•••
በሕይወታችን ውስጥ የሚያጋጥመን ችግርና መከራ ምን ያህል እንደሚጎዳና ምን ያህል ከባድ እንደሆነ አውቃለሁ። ችግር ደስታን ይነጥቃል፣ እንቅልፍ ይነሳል እንዲሁም እረፍት ያሣጣል።

ነገር ግን በፍጹም አትጨነቅ ከእንግዲህ ወዲህ አይቆይም እግዚአብሔር ያየዋል፣ እርሱም የልብህን ጩኸት ሰምቶሃል። መከራው አንተን ሊሰራህ እንጂ ሊያጠፋህ አልመጣም።

እግዚአብሔር በሚያጋጥመን ማንኛውም መከራና ችግር ሁሉ እርሱ ከእኛ ጋር እንደሚሆንና እንደሚያሻግረን ቃል ገብቶልናል። ስለዚህ ችግርህን አትሰውር ይልቁንም ለፈጣሪህ ስጠው፣ በእራስህ ለመወጣት አትችልም ግን ሁሉን ቻዩ እግዚአብሔር ሁሉን ይችላል።

ህመምህ እይታህን ሰርቆት ሊሆን ይችላል ግን እግዚአብሔር በአፅናፈ አለሙ ሁሉ እና በእርሱም ውስጥ በሚሆነው ነገር ላይ ሁሉ ፍፁም ቁጥጥር አለው።

እግዚአብሔር እይታህን፣ ደስታህንና ጤናህን ይመልስልሃል፣ አሁን ስለ ህመሙ ማሰላሰልህን አቁምና ስለ እግዚአብሔር ታላቅነትና መልካምነት አስብ።

እግዚአብሔርን እመነው እርሱ የበለጠ ታላቅ ነገር እየሰራ ነው፣ አሁን ያለው ችግር እግዚአብሔር ወደ ታላቅ ደስታ ይለውጠዋል፣ ችግሩ ሊሰራህ እንጂ ሊያጠፋህ አልመጣም !
•••
“እግዚአብሔርንም ለሚወዱት እንደ አሳቡም ለተጠሩት ነገር ሁሉ ለበጎ እንዲደረግ እናውቃለን።”
— ሮሜ 8፥28
•••
☞ 🅢🅗🅐🅡🅔
@shegainfom