Get Mystery Box with random crypto!

#ወዳጀ ..... 'ሰዎች በአንተ ላይ የዘጉብህን በር አትመልከት፣ በፈጣሪ እጅ ያለውን ቁልፍ ተመል | Shega info

#ወዳጀ .....
"ሰዎች በአንተ ላይ የዘጉብህን በር አትመልከት፣
በፈጣሪ እጅ ያለውን ቁልፍ ተመልከት፡፡"

ይህን ስትወጣ ተስፋ የተሞላበት ጉዞህም ብሩህ ይሆናልና፡፡
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
ዛሬ ያስለቀሰህ ሰው ነገ የሚያስለቅሰው ሰው አያጣም
ዛሬ የጎዳህ ነገ እሱንም የሚጎዳው
ሰው አያጣም
ምድር ትዞራለች አንተ የሚጠበቅብህ በትዕግስት
መኖር ብቻ ነው።

ሰው የዘራውን ነው የሚያጭደውና የዋህነት አይጎዳም
ስኬት የደስታ ቁልፍ ናት

#ወዳጀ ሆይ ......

እኖራለሁ ብለህ ሥራ፤ እሞታለሁ ብለህ ኑር› ሲባል አልሰማህም?
መውረድን የረሳ ባለ ሥልጣን፣ ሕመምን የረሳ ጤነኛ፣ ድህነትን የረሳ ሀብታም፣ ሞትን የረሳ ነዋሪ፣

ድቀትን የረሳ ጻድቅ፣ ውርደትን የረሳ ክቡር፣

#ወደረሳው ነገር ለመጓዝ እንዴት ይፈጥናል መሰለህ?

ድቅድቁ ጨለማ ያለው ከሻማው ሥር ነው፡፡

"እየጠሉ የወደዱ መስለው ከሚቀርቡ ሀሰተኛ ሰዎች ጋር ከመኖር ብቸኝነት ይሻላል!!!
መልካም ቀን
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°

ሼር፣በማድርግ ብቻ ቤተሰብ ይሁኑ
@Shegainfom