Get Mystery Box with random crypto!

Shega info

የቴሌግራም ቻናል አርማ shegainfom — Shega info S
የቴሌግራም ቻናል አርማ shegainfom — Shega info
የሰርጥ አድራሻ: @shegainfom
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 12.69K
የሰርጥ መግለጫ

▪ይህ የሸጋ info የቴሌግራም ቻናል ነዉ ▪ አስተማሪና ቁምነገር አዘል መረጃዎች በውብ አቀራርብ ለናንተ ይደርሳል #join በማረግ ቤተሰብ ይውኑን::

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-07-06 07:37:35 #ሺ_ዓመት_አይኖር

ብዙ ጊዜ ለስንፍናችን ምክንያት ወይም ተስፋ ለመቁረጥ ሰበብ ከሚሆኑን ነግሮች አንዱ "ሺ ዓመት አይኖር" የሚለው አባባል ነው በእርግጥ በምድር ሺ ዓመት መኖር የቻለ የለም ረጅም ዓመት እንደኖረ የሚነገርለት ማቱሳላ እንኳን ሺ ዓመት አልኖረም ወዳጄ በተለይ እኛ ባለንበት በዚህ ዘመን ደግሞ እንኳን ሺ ዓመት ሊኖር ቀርቶ መቶ የሞላ እንኳን ቢገኝ የሚድያ የአንድ ወቅት የዜና ሽፋን መሆኑ የማይቀር ነው ስለዚህ ወደ ዘመናችን አባባሉን ማምጣት ከፈለግን መቶ ዓመት አይኖር በሚል ልንቀይረው ያስፈልጋል።

የሚያሳዝነው ሺ ዓመት አይኖር የምንለው ለመዝናናት ለመጨፈር ራስን ለመርሳት ፈቃደ ሥጋን እንደ ልብ ለመፈጸም ብቻ እንጂ ለመንፈሳዊ ሕይወት ለመሰናዳት አይደለም "አንቂ" የሚባሉ አካላት የዕድሜህን አጫርነት የሚነግሩህ ከሞት በኋላ ላለው ረጅሙ ዕድሜ በዚህች በአጭሯ የምድር ዕድሜህ በጎ ሰርተህ እንድታልፍ ሳይሆን እንዳትጨናነቅ ፈታ ብለህ(በእነርሱ አማርኛ) እንድትኖር ለማስታወስ ብቻ ነው።

ወዳጄ ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት ግን በምድር ስለምትኖርበት ዕድሜህ ሲነግርህ ቢበዛ(ቢበረታ) ሰማንያ ይልሃል ሺ ዓመት አይኖር ሲሉህ ቢበዛ ሰማንያ እርሱም በተገኘ በላቸው ታድያ በምድር የምትኖርበት ዕድሜህ ጥቂት ከሆነ ከዚያ በኋላ በሞት ይህን ምድር ከተሰናበትክ ከሞት በኋላ የት ትሄድ ይሆን?? የዚህ ምድር ኑሮህ በሞት ከተቋጨ በኋላ ሞተህ የምትቀር መስሎ እንዳይሰማህ ከሞት በኋላ ሕይወት አለህ ያውም እንደሰው ኖረህ ከሞትክ የምትነሳው እንደ ሰው ሆነህ የምትኖረውን ሕይወት ለመድገም

እንዳይመስልህ ከትንሣኤ በኋላ የምትኖረው እንደ መላእክት ነው “በትንሣኤስ እንደ እግዚአብሔር መላእክት በሰማይ ይሆናሉ”ማቴ 22፥30
ስለዚህ አስታውስ የምድር ኑሮህ ቢበዛ ሰማንያ ነው ያ ማለት ጥቂት ነው መጽሐፍ እንደሚነግርህ

“ሕይወታችሁ ምንድር ነው ጥቂት ጊዜ ታይቶ ኋላ እንደሚጠፋ እንፍዋለት ናችሁና”
ያዕ 4፥14

* ስለዚህ በምድር የምትቆየው ጥቂት ጊዜ ነውና:-*
ዛሬ የንስሐ አባት ያዝ
ዛሬ ንስሐ ግባ
ዛሬ ከተጣላሃቸው ታረቅ
ዛሬ ያስቀየምካቸውን ይቅር በል
ዛሬሥጋ ወደሙን ተቀበል

ነገ ሳይሆን ዛሬ መልካም ነገሮችህን ሁሉ ጀምር ምክንያቱም
“እነሆ፥ የመዳን ቀን አሁን ነው።”
2ኛ ቆሮ 6፥2
Join @shegainfom
2.9K viewsedited  04:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-05 07:17:25 መሞታችን አይቀርምና ከእነዚሁ ሁሉ እንራቅ

አትቅና እንደ ቃየል ወንድምህን
ትገላላህ።    ዘፍጥረት 4÷1
ቃየል ወንድሙን የገደለው ስግብግብነት ነበር

ክፋ ባልንጅራን አትያዝ እንደ ሶምሶን በጠላት እጅ ትወድቃለህ። ፦ መጽሐፈ ምሳሌ 16÷ 15

ዘፍጥረት 3÷1-8 በአባትህ አትሳቅ እንደ ካም ትረገማለህ። እንደ ሴምና ያፌት እንሁን   ዘፍጥረት 9÷20 -21

አትመኝ፦እንደ አዳም የዲብሎስ ባሪያ ትሆናለህ።ዘፍጥረት 3÷1-8

እግዚአብሔር ለእኛ አንድ ነገር ሲሰጠን ወይም ሲያድርግልን እንደሚጠቅመን ያውቃል አወቆም ይሰጠናል

እኛ ግን ያለን ትተን የሌለን እንመኛለን ከንቱነት

በሐሰት አትመስክር፦ እንደ ሐማ ባዘጋጀኸው ጉድጓድ ትገባለህ።
፦ መጽሐፈ አስቴር 7÷1

አትስከር አዕምሮ አሳጥቶ የማይገባ ሥራ ትሠራለህ።  ዘፍጥረት 19÷30-38

አትዘሙት እንደ ሰሎሞን አምላክህን አስረስቶ ጣዖትን እንድታመልክ ያደርግሃል። ከዚህ ይሰውረን መጽሐፍ ነገሥት ካልዕ 1 11÷1-8

ትዕቢተኛ አትሁን ፦እንደ ሰናክሬም ትወድቃለህ።መጽሐፈ ነገሥት
ካልዕ 2 19÷35

ገንዘብን አትውደድ እንደ ይሁዳ ጌታህን ያስክድሃል። ማቴዎስ ወንጌል፦ 26÷14-16

ቀንድ ነገር ቢሆንም ገንዘብ በመውደድ ከስንት ነገር ርቀናል ከሃገራችን ከቤተሰባችን ከጓደኞቻችን ከልጆቻችን ሞልቶ በማይ ሞላ ሂወታችን......

ሥልጣንን አትውደድ፦እንደ አቤሴሎም በአባትህ ላይ ትነሣለህ፦ መጽሐፈ ሳሙኤል ካልዕ 2 15÷13-17

ዓለምን አትመልክት፦እንደ ሎጥ ሚስት የጨው ዐምድ ሆነህ ትቀራለህ፦ ዘፍጥረት 19÷ 22-23 1ኛ ቆ.ስ 2፥5

ማመናችሁ በእግዚአብሔር ኃይል እንጂ በሰው ጥበብ እንዳይሆን።
1ኛ ቆ.ስ፦ 2፥15

‹‹. . . ሕይወት አዙሪት ናት፡፡ ረጅም ርቀት የተጓዝክ ቢመስልህም የምትጨርሰው ከጀመርክበት ነው፡፡ ራቁትክን ትወለዳለህ እርቃንህን ወደ መቃብር ትወርዳለህ፡፡

በጥርስ አልባው ድድህ እየጋጥክ ትጀምራለህ ፤ ጥርሱን ባረገፈው ድድህ እያልጎጠጎጥክ ትጨርሳለህ፡፡ ዘመንም ተምኔታዊ ነው፡፡ መስከረም ጥቅምት ብሎ ያስጀምርህና መስከረም ብሎ ያመጣብሀል፡፡

ሰኞ ማክሰኞ ብለህ ተጉዘህ እንደገና ሰኞ ትላለህ፡፡ ሕይወት አዙሪት ናት መጀመርያህ መጨረሻህ ነው፡፡ የጀመርክበት አትርሳ መጨረሻህ ነውና የጀመርክበትን አትናቀው፤ ትጨርስበታለህና፡፡

ተራ ሰው ሆነህ ትጀምራለህ ተምረህ ዕውቀት ብትጨምር ፣ ነግደህ ሀብት ብታገኝ ፣ ክቡረ ክቡራን ሆነህ የወርቅ ካባ ብትለብስ የምትጨርሰው እንደ ተራ ሰው አፈር ለብሰህ ነው፡፡››

‹‹ልብ በል! በማወቅ ትጀምራለህ በመዘንጋት ትጨርሳለህ፡፡ ዕውቀት አላመጣህምና ዕውቀት ይዘህ አትሔድም፡፡ በለቅሶ ትጀምራለህ በጭንቅ ትጨርሳለህ፡፡

በሰው እቅፍ ትጀምራለህ በሰው ሸክም ትጨርሳለህ፡፡ ልደትህ ከሞትህ በምን ይለያል? ሞትህስ ከልደትህ በምን ይከፋል?

ሕይወት መጀመርያና መጨረሻዋ አንድ ነው፡፡ ከፀሐይ በታች አዲስ ነገር የለም፡፡ ልብ በል የዓለም ከንቱነት ግን ውበቷ ነው፡፡

ዓለም አዲስ ነገር ቢኖራ እኛን እንዴት በጸጸተን፡፡
      @shegainfom
ፍቅር : ሰላም : ለምድራችን !
1.2K views04:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-15 15:35:13 #ሰናይ_ሰንበት
.ትዳር~ማለት 1 ወንድ አንድ ሴት
.ትዳር~ማለት 1 እምነት አንድ እዉነት
.ትዳር~ማለት 1 እሳት አንድ ዉሃ
.ትዳር~ማለት 1 ሙሉ አንድ ጎዶሎ
.ትዳር~ማለት 1 መጥፎ አንድ ጥሩ
.ትዳር~ማለት 1 ጉልቻ አንድ ድስት
.ትዳር~ማለት 1 ወንዝ አንድ ዉሃ

የሚቀዳ ቢሆንም ካልተሳሰቡ እና ካልተቻቻሉበት ሊደርቅ የሚችል ወራጅ ወንዝ ነዉ

#አስተዉሉ
ሴት ልጅን ባሏ ያመሰግናታል
የሕይወት ዘመኑም እጥፍ ይሆናል
ቅን ሴት ባሏን ደስ ታሰኘዋለች
ዘመኑም በሰላም ይጨርሳል
ደግ ሴት ዕድሏ ያማረ ነዉ።
እግዝአብሔርን የሚፈራ ሰዉንም ወደ ዕድሉ ታደርሰዋለች

#መፅሐፈ ሲራክ 26፥1_3
ፈጣሪ በፍቅር ያማረ ትዳር እና ሠላም ያለዉ ፍቅር ይስጣችሁ! ለዝህ ክብር ያልበቃችሁ እሱ ያብቃችሁ # እግዝአብሔር ያጣመረዉን ማንም አይለየዉም
@shegainfo
891 viewsedited  12:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-13 07:25:31 1 ሩሐማ፦ምሕረት ማለት ነው።
2 ዮዳሔ፦እግዚአብሔር ያውቃል ማለት ነው።
3 ቴዎፍሎስ፦የእግዚአብሔር ወዳጅ ማለት ነው።
4 ኑኃሚን፦ደስታየ ማለት ነው።
5 ናትናኤል፦የእግዚአብሔር ስጦታ ማለት ነው።
6 አዛሄል፦እግዚአብሔር ያያል ማለት ነው።
7 ኢዮስያስ፦እግዚአብሔር ይደግፋል ማለይ ነው
8 ኢዩኤል፦እግዚአብሔር አምላክ ነው ማለት ነው።
9 በርናባስ፦የመጽናናት ልጅ ማለት ነው።
10 ሶፎንያስ፦እግዚአብሔር ሰውሯል/ጠብቋል ማለት ነው።
11 ሕዝቅኤል፦እግዚአብሔር ብርታትን ይሰጣል ማለት ነው።
12 ኬልቅያስ፦እድል ፈንታየ እግዚአብሔር ማለት ነው
13 ሳሙኤል፦እግዚአብሔር ሰማኝ ማለት ነው።
14 ሚኪያስ፦ እንደ እግዚአብሔር ያለ ማን ነው! ማለት ነው።
15 ሆሴዕ፦እግዚአብሔር ያድናል ማለት ነው።
16 ሔዋን፦የሕያዋን ሁሉ እናት ማለት ነው።
17 ሕዝቅያስ፦እግዚአብሔር ኃይሌ ነው ማለት ነው።
18 መልከጼዴቅ፦የሰላም ንጉሥ ማለት ነው።
19 ሚልኪያስ፦መልእክተኛየ ማለት ነው።
20 ሣራ፦ልዕልት ማለት ነው።
21 ስምዖን፦ሰማ ማለት ነው።
22 ብንያም፦የቀኝ እጄ ልጅ ማለት ነው።
23 ናሆም፦መጽናናት ማለት ነው።
24 ናታን፦ እግዚአብሔር ሰጥቷል ማለት ነው።
25 አልዓዛር፦እግዚአብሔር ረድቷል ማለት ነው።
26 አስቴር፦ኮከብ ማለት ነው፣
27 አቤሜሌክ፦የንጉሥ አገልጋይ ማለት ነው።
28 አቤሴሎም፦አባቴ ሰላም ነው ማለት ነው።
29 አብድዩ፦የእግዚአብሔር አገልጋይ ማለት ነው።
30 አብራም፦ታላቅ አባት ማለት ነው።
31 አብርሃም፦የብዙዎች አባት ማለት ነው
32 አኪያ፦እግዚአብሔር ወንድሜ ነው ማለት ነው።
33 አክዐብ፦የአባት ወንድም ማለት ነው።
34 ባሮክ፦ቡሩክ ማለት ነው።
35 አዳም፦መልካሙ ማለት ነው።
36 ኢሳይያስ፦ እግዚአብሔር ደኅንነት ነው ማለት ነው።
37 ባርቅ፦መብረቅ ማለት ነው።
38 ኢያሱ፦እግዚአብሔር አዳኝ ነው ማለት ነው።
39 ኢዮሳፍጥ፦እግዚአብሔር ፈርዷል ማለት ነው።
40 ኢዮራም፦እግዚአብሔር ከፍ ከፍ አለ ማለት ነው።
41 ኢዮርብዓም፦ሕዝቡ እየበዛ ይሄዳል ማለት ነው።
42 ቤተልሔም፦የእንጀራ ቤት ማለት ነው።
43 ኢዮአስ፦እግዚአብሔር ሰጥቷል ማለት ነው።
44 ኢዮአቄም፦እግዚአብሔር አቆመ ማለት ነው።
45 ኢዮአብ፦እግዚአብሔር አባት ነው ማለት ነው።
46 ኢዮአታም፦እግዚአብሔር ፍጹም ነው ማለት ነው።
47 ኢዮአካዝ፦እግዚአብሔር ይዟል ማለት ነው።
48 ኤልሳዕ፦እግዚአብሔር ደኅንነት ነው ማለት ነው።
49 ኤልያስ፦እግዚአብሔር አምላክ ነው ማለት ነው።
50 ኤልያቄም፦እግዚአብሔር ያስነሳል ማለት ነው።
51 ኤዶም፦ቀይ ማለት ነው
52 እስራኤል፦ከእግዚአብሔር ጋር ይታገላል ያሸንፍማል ማለት ነው።
53 ኤልሳቤጥ፦እግዚአብሔር መሐላየ ነው ማለት ነው።
54 ኤልሻዳይ፦ሁሉን ቻይ አምላክ ማለት ነው።
55 ሀሌሉያ፦እግዚአብሔርን አመስግኑ ማለት ነው።
56 ሰሎሞን፦ሰላማዊ ማለት ነው።
57 ኬብሮን፦ኅብረት ማለት ነው
58 አዛርያስ፦እግዚአብሔር ረድቷል ማለት ነው።
59 ኤደን፦ደስታ ማለት ነው።
60 ዖዝያን፦እግዚአብሔር ኃይሌ ነው ማለት ነው።
61 ዘካርያስ፦እግዚአብሔር ያስታውሳል ማለት ነው።
62 ይሳኮር፦ ዋጋዬ ማለት ነው
63 ይዲድያ፦በእግዚአብሔር የተወደደ ማለት ነው።
64 ዮሐናን፦እግዚአብሔር ጸጋ ሰጪ ነው ማለት ነው።
65 ዮሐንስ፦እግዚአብሔር ጸጋ ነው ማለት ነው።
66 ዮሴፍ፦ይጨምር ማለት ነው።
67 ዮናስ፦ርግብ ማለት ነው።
68 ዮናታን፦እግዚአብሔር ሰጥቷል ማለት ነው።
69 ዮአኪን፦እግዚአብሔር ያቆማል ማለት ነው።
70 ዮካብድ፦እግዚአብሔር ክብር ነው ማለት ነው።
71 ምናሴ፦ማስረሻ ማለት ነው።
72 ዮፍታሔ፦እግዚአብሔር ይከፍታል ማለት ነው።
73 ዲቦራ፦ንብ ማለት ነው።
74 ዳንኤል፦እግዚአብሔር ፈራጅ ነው ማለት ነው።
75 ጎዶልያስ፦እግዚአብሔር ታላቅ ነው ማለት ነው።
76 ጽዮን፦አምባ ማለት ነው።
77 ጳውሎስ፦ብርሃን ማለት ነው።
78 ሴት፦ምትክ ማለት ነው።
79 ጴጥሮስ፦አለት ማለት ነው።
80 ሄኖክ፦ታደሰ ማለት ነው።
81 ኄራኒ፦ሰላም እና ፍቅር ማለት ነው።
91 ሐና፦ጸጋ ወይም ስጦታ ማለት ነው።
92 ሮቤል፦እነሆ ወንድ ልጅ ማለት ነው።
93 ኤርምያስ፦እግዚአብሔር ከፍ ያደርጋል ማለት ነው።
94 ሮብዓም፦ሕዝብ ይብዛ ማለት ነው።
95 ማራናታ፦ጌታ ሆይ ና ማለት ነው።
96 ቤቴል፦የእግዚአብሔር ቤት ማለት ነው።
97 ቄርሎስ፦የተመረጠ ምርጥ ማለት ነው።
98 እስጢፋኖስ፦አክሊል ማለት ነው።
99 ሳውል/ሳኦል፦ከእግዚአብሔር የተለመነ ማለት ነው።
100 ሴዴቅያስ፦የእግዚአብሔር ጽድቅ ማለት ነው።
join @shegainfom
1.5K views04:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-11 14:15:29 #የጋብቻ_ሕግጋት_ ~~~ #ሼርርርርርርርር

1.ከተጋቡ በኅላ አንድ አካል ናቸው። (ማቴ 19:4-6
2.መፋታት ክልክል ነው። (ሚል2:14)
3.አንድ ወንድ ለአንድ ሴት ። 1ኛ ቆሮ 7:2
4.የሚገባቸውን ሁሉ ማድረግ።
5.ባልም ለሚስትም በራሳቸሁ ሥልጣን የላቸሁም። 1ኛ ቆሮ 7:4
6.ኃላፊነትን መወጣት። ኤፌ5:20-23 ቆላ 3:18
7.ለጾምና ለጸሎት ካልሆነ አለመለያየት 1ኛ ቆሮ7:5
8.ሥጋዊ ጌጥ አለማብዛት ።1ኛ ጴጥ 3:1-4
9.ድንገተኛ ግጭት ቢከሰት ወዲያው መታረቅ።1ኛ ቆሮ 7:10-11
10.በሞት ካልሆነ አለመለያየት።1ኛ ቆሮ 7:39 እናሮሜ 7:2-3
ከሥጋዊ መንፈሳዊ የጋብቻ ዘመድ አለማግባት።ዘሌ 18:6-20 ዘሌ20:16-21፣ማር 6:17።

: #አታግባ
የህይወት ምንነት ሳታውቅ አታግባ
የትዳርን ምንነት ሳታውቅ አታግባ
የትዳር አጋርህን ሀቅ (መብት) ሳታዘጋጅ አታግባ
በችግር ሰዓት ህይወትን አብረህ ልትገፋ ምትችል ሴት ሳታገኝ አታግባ
ኃላፊነትህን እንዴት መወጣት እንዳለብህ ሳታቅ አታግባ
ለልጆችህ ተምሳሌት መሆን ሳትችል አታግባ

#ትዳር
ትዳር ማለት 1ወንድ አንድ ሴት
ትዳር ማለት 1እምነት አንድ እውነት
ትዳር ማለት 1እሳት አንድ ውሃ
ትዳር ማለት 1 ሙሉ አንድ ጎዶሎ
ትዳር ማለት 1መጥፎ አንድ ጥሩ
ትዳር ማለት 1 ጉልቻ አንድ ድስጥ
ትዳር ማለት 1ወንዝ አንድ ውሃ የሚቀዳ ቢሆንም
ካልተንከባክበውና ካልተቻቻልንበት ሊደርቅ የሚችል #ወራጅ

#ወንዝ ነው።
ደግ ሴትን ባሏ ያመሰግናታል፤
የሕይወት ዘመኑም እጥፍ ይሆናል።
ቅን ሴት ባሏን ደስ ታሰኘዋለች፤
ዘመኑንም በሰላም ይጨረሳል።
የደግ ሴት ዕድሏ ያማረ ነው፤
እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰውንም ወደ
ዕድሉ ታደረሰዋለች
መፀሐፈ ሲራክ 26:1~3

በፍቅር ያማረ ትዳር ሠላም ያለው እውነተኛ ፍቅር ፈጣሪ ይስጠን! አሜን
@shegainfom
ፍቅር : ሰላም :ለምድራችን !
1.6K views11:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-10 21:17:46 የቲክቶክ ቻናላችንን ይቀላቀሉ
         
https://vm.tiktok.com/ZMF3tx8oJ/
879 views18:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-10 07:58:54 «ከትዳር በፊት ማወቅ የሚገባን ነጥቦች በጥቂቱ»!

1.አትቆጣ፣-ቁጣ ትዳርን ይገላል።
2.እምነት ይኑርህ፣-እምነት ማጣት ትዳርን ያፈርሳል።

3.ድክመት አይኑርህ፣- ድክመት ትዳርን ያቀዘቅዛል።
5.የሰው ወሬ አትስማ፣-የሰው ወሬ ትዳርን ያፈርሳል።

6.ቸልተኝነት አይኑርህ፣-ቸልተኝነት ትዳርን ይገላል።
7.እኔ ብቻ ያልኩት ይሁን አትበል፣-እኔ ብቻ ያልኩት ይሁን ማለት ትዳርን ያቀዘቅዛል።
8.ለሚስትህ እንክብካቤ ይኑርህ፣-ለሚስትህ እንክብካቤ አለማድረግ ትዳርን ያቀዘግዛል።

9.ገንዘብን አታባክን፣- ገንዘብ ማከን ትዳር ውስት እንከን ይፈጥራል።
10.የጓደኛ ብዛት አይኑርህ ፣-የጓደኛ ብዛት ትዳር ውስጥ ችግር ይፈጥራል።
11.አትቅና፣-መቅናት ትዳርን ይገላል።

12.ራስ ወዳድነት አትሁን፣-ራስ ወዳድነት ትዳርን ያፈርሳል
13.የሚስትህን ፍላጎት አዳምጥ፣-የሚስትን ፍላጎት አለማዳመጥ ትዳርን ያፈርሳል።
14.ሱስ አይኑርህ፣-ሱስነት ትዳርን ይገድላል።

15.የራስህን ፍላጎት አትከተል፣-የራስን ፍላጎት መከተል ትዳርን ያፈርሳል።
16.ከሚስትህ ጋር የምክክር ሰዓት ይኑርህ፣-ከሚስትህ ጋር የምክክር(የንግግር)ሰዓት አለመኖር ትዳርን ይገላል።

17.ከልክ በላይ የዋህ አትሁን፣-ከልክ በላይ የዋህነት ትዳርን ያቀዘቅዛል።
ከወረት የጸዳ ፍቅር እግዚአብሔር ለሁላችንም ይስጠን!
Join @shegainfo
1.4K viewsedited  04:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-09 08:48:07 በትምህርቱ የተመሰገነው ወጣት ለቤተሰቦቹ ከ 10 ልጆች 6ኛ ሲሆን ከቅዱስ ዮሴፍ ትምህርት ቤት ሲመረቅ ውጤቱ 4.00 ነበር እናም አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲን ተቀላቅሎ ሕግ አጠናና ለሶስት ዓመታት በሕግ ባለሞያነት በአገር ውስጥ አገልግሎ ወደ አገረ አሜሪካ ተጓዘ፡፡

እዚያም የተለያየ ስራዎችን ሲሰራ ቆይቶ ሁለተኛ ዲግሪውን በ Non-profit management and development አገኘ...

በ 1970ዓ.ም ከ እናቱ ጽጌ በቀለ እና ከአባቱ በለጠ አዲስ በአዲስ አበባ የተወለደው እና “ሰውን ለመርዳት ሰው መሆን ብቻ በቂ ነው…” በሚለው መሪ ቃሉ የምናውቀው ሜቄዶንያ የአረጋውያን መርጃ ድርጅት መስራች እና የሰብአዊ አገልግሎት ሰጪ ግልሰብ ነው፡፡

የሜቄዶንያው ቢኒያም በለጠ (የክቡር ዶ/ር)
ይሄ ደግ ሰው የአረጋውያን መውደቂያ ማጣት ከዚያም በላይ በየመንገዱ መውደቅ ጧሪ ቀባሪ ማጣት ያሳስበው ነበርና በአገረ አሜሪካ የተማረውን እውቀት እና ያጠራቀመውን ገንዘብ ይዞ አስታዋሽ ላጡ ሊደርስ የቅንጦት እና የምቾት ሕይወቱን ትቶ ወደ አገር-ቤት ተመለሰ፡፡

እናም በ1992/93 ዓ.ም መቄዶንያ የተሰኘ የአረጋዊያን መርጃ ማዕከል በመክፈት 20 ደጋፊ ያጡ ሰዎችን በወላጆቹ ቤት ማኖር ጀመረ፡፡ መቄዶንያ አሁን ትልቅ የሰብአዊ እርዳታ አገልግሎት መስጫ ሆኖ ከ 4,000 በላይ ሰዎችን ይረዳል…

ይህ ሰው ዘመናዊ ህይወቱን ትቶ ለተጎዱ እና አጋዥ ለሌላቸው እንዲሁም የአካል ጉዳት ላለባቸው አረጋውያን ድጋፍ እየሰጠ ነው፡፡ ያደለው ሁሉ ያረጃል፤ እድሜ ጸጋ ነው፡፡

ግን ስናረጅ ያዘጋጀነው ሀብት ከሌለን ወይም የሚጦረን ቤተሰብ ካላፈራን አወዳደቃችን አያምርም… ይሄ የአደባባይ ምስጢራችን ነው…
ቢኒያም በአገራችን ካሉ በጎ ሰዎች ውስጥ አንዱ ነው፤በሱ መኖር የብዙዎች ሕይወት ተቃንቷል…
በሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች በዘመናቸው ማምሻ ላይ ከማልቀስ ድነዋል፤ በክብር በኖሩበት ዓለም ከማፈር ተረፈዋል ፡፡

መማሩን፤ ማንበቡን፤ ማስተዋሉን ለመልካም ያዋለ ለሁላችን አርአያ መሆን የሚችል ቅን ሰው…
ማንበብ እና መማራችን ለበጎነት እንደዚህ ሲውል ያስደስታል።

ስንቶቻችን የተደላደለ ኑሯችንን እንዳናጣ ስንቱን እንበድላለን፤ እሱ ግን ምቾቱን ለብዙ ደሃዎች ሰጠ…

እውነትም “ሰውን ለመርዳት ሰው መሆን ብቻ በቂ ነው…”

Join @shegainfo
1.5K views05:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-23 15:58:14 የመጽሐፍ ቅዱስ ስሞች......"ለልጅዎ ስም
ማውጣት ይፈልጋሉ
ከዚህ ይመረጡ"
1. ዮሐንስ ፡- የእግዚአብሔር ፀጋ (ሀሴት፣ ፍስሀ)
2. ዳንኤል ፡- እግዚአብሔር ፈራጅ ነው
3. ኤልሳዕ ፡- እግዚአብሔር ደህንነት
4. አሞን ፡- የወገኔ ልጅ
5. እስራኤል ፡- የእግዚአብሔር ህዝቦች
6. ማርያም ፡- የእግዚአብሔር ስጦታ
7. ሀና ፡- ፀጋ
8. ሩሀማ ፡- ምህረት የሚገባት
9. ኢያሱ ፡- እግዚአብሔር አዳኝ ነው፣ መድሃኒት
10. ጌርሳም፡- ከሌላ ምድር ስደተኛ ነኝ
11. እዮሳፍጥ፡- እግዚአብሔር ፈርዷል
12. እዮአም ፡- አዳኝ
13. ኢዮሲያስ፡- ከፍ ከፍ አለ
14. ኤልሳቤጥ፡- እግዚአብሔር መሀላዬ ነው
15. አብርሃም ፡- የብዙሃን አባት
16. ኢሊዲያ (ይድድያ)፡- በእግዚአብሔር የተወደደ
17. ኤዶንያስ ፡- እግዚአብሔር ጌታዬ ነው
18. ኦዶኒራም ፡- ጌታየ ከፍ ያለ ነው አለ
19. ሆሴዕ፡- እግዚአብሔር መድኃኒት ነው
20. ሕዝቅያዝ ፡- እግዚአብሔር ሀይሌ ነው
21. ጴጥሮስ፡- መሰረት
22. ሴት ፡- ምትክ
23. ሙኤል ፡- እግዚአብሔርን ለምኜዋለው
24. አቤል ፡- የህይወት እስትንፋስ
25. ጎዶሊያስ ፡- እግዚአብሔር ታላቅ ነው
26. ስጥና ፡- ተዘጋ
27. ማቴዎስ ፡- ሞገስ
28. ፌቨን፡- የእግዚአብሔር አገልጋይ
29. ሚኪያስ ፡- እንደ እግዚአብሔር ያለ ማን አለ
30. ይሁዳ፡- አማኝ (የአማኝ ልጅ)
31. ወንጌል ፡- የምስራች
32. ኤርሚያስ ፡- እግዚአብሔር ከፍ ከፍ ያደርጋል
33. ህዝቅኤል ፡- እግዚአብሔር ብርታት ይሰጣል
34. ማራናታ፡- እግዚአብሔር ቶሎ ና
35. ሆሴዕ ፡- እግዚአብሔር ያድናል
36. አሞፅ ፡- ሀይል
37. ኤሴቅ ፡- የተጣላሁብሽ
38. ሚኪያስ ፡- እግዚአብሔር የሚመስል ማን ነው
39. ኢዮኤል፡- እግዚአብሔር አምላክነው
40. አብድዩ፡- የእግዚአብሔር አገልጋይ
41. ዮናስ ፡- ርግብ (የዋህ፣እሩሩህ)
42. እምባቆም ፡- እቅፍ
43. ሶፎኒያስ ፡- እግዚአብሔር ጠብቋል
44. ሀጌ፡- በሀላዊ ወይም በበዓል የተወለደ
45. ዘካርያስ ፡- እግዚአብሔር ያስታውሳል
46. ሚልክያስ ፡- መልክተኛዬ
47. ናታኔም ፡- የእግዚአብሔር ጠራጊ
48. አቤኔዘር ፡- ምስጋናዬን ለእግዚአብሔር አቀርባለው
3.6K views12:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-22 20:09:19
#ነገ_የሚባል_ቀን_የለም!

የአንተን ሕይወት የሚመለከት ነገር ስታነብና ሲነካህ ያነበብከውን ነገር ተቀብለህ ወዲያውኑ ተግብረው፡፡ ወዲያውኑ ወደ ተግባር ግባ፡፡ በቃ ጊዜ አትፍጅ፡፡ ሲጋራህን ጣል፤ ቢራ ተው፤ ጂም ግባ፤ ይቅርታ ጠይቅ… ወዘተ፡፡

ከእንደነዚህ አይነት ነገሮች ውስጥ አንዳንዶቹ ከሌሎቹ የበለጠ ከባድ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ የትኞቹም ቀላል ናቸው እያልኩኝ ግን አይደለም፡፡ እንደዚያ እንዳልሆነ አውቃለሁ፤ ግን ይቻላል - ለእኔም ለአንተም፡፡ እናም አሁን አድርገው፤ ነገን አትጠብቅ፡፡

ቁጭ ብለህ እያሰብክ ነገን አትጠብቅ፡፡ ሲጀመርም ነገ ስለመኖሩ ምንም ማረጋገጫ የለህም፡፡ ነገ ሚባል ቀን እንደሌለ አውቀህ ዛሬን ኑር፡፡ አእምሮህ ስለ ነገ እያሰበ ሰፊውን ጊዜህን እንዲወስድብህ እድል አትስጠው፡፡ ያለ እረፍት በአእምሮህ ውስጥ እየተንቀዋለለ የሚረብሽህ ነገር ካለ የማትወስንና የተወዛገብክ እንድትሆን ያደርግሃል፡፡

አእምሮህ ለምን ስለ ለውጥ መጨነቅ እንደሌለብህ፣ ለምን እንደማይሰራልህና እንዴት ከባድ እንደሆነ እየነገረ ወደ ኋላ ሊጎትትህ ይሞክራል። አንተ ግን አታዳምጠው። አሁን ጊዜው የሕይወት ውጥንቅጦችን መልክ መልክ የማስያዣ ጊዜ ነው!

ዛሬን በአግባቡ ኑረው፡፡

#በልኬት_ወደ_ስኬት መጽሐፍ
2.2K views17:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ