Get Mystery Box with random crypto!

መሞታችን አይቀርምና ከእነዚሁ ሁሉ እንራቅ አትቅና እንደ ቃየል ወንድምህን ትገላላህ።    ዘፍጥ | Shega info

መሞታችን አይቀርምና ከእነዚሁ ሁሉ እንራቅ

አትቅና እንደ ቃየል ወንድምህን
ትገላላህ።    ዘፍጥረት 4÷1
ቃየል ወንድሙን የገደለው ስግብግብነት ነበር

ክፋ ባልንጅራን አትያዝ እንደ ሶምሶን በጠላት እጅ ትወድቃለህ። ፦ መጽሐፈ ምሳሌ 16÷ 15

ዘፍጥረት 3÷1-8 በአባትህ አትሳቅ እንደ ካም ትረገማለህ። እንደ ሴምና ያፌት እንሁን   ዘፍጥረት 9÷20 -21

አትመኝ፦እንደ አዳም የዲብሎስ ባሪያ ትሆናለህ።ዘፍጥረት 3÷1-8

እግዚአብሔር ለእኛ አንድ ነገር ሲሰጠን ወይም ሲያድርግልን እንደሚጠቅመን ያውቃል አወቆም ይሰጠናል

እኛ ግን ያለን ትተን የሌለን እንመኛለን ከንቱነት

በሐሰት አትመስክር፦ እንደ ሐማ ባዘጋጀኸው ጉድጓድ ትገባለህ።
፦ መጽሐፈ አስቴር 7÷1

አትስከር አዕምሮ አሳጥቶ የማይገባ ሥራ ትሠራለህ።  ዘፍጥረት 19÷30-38

አትዘሙት እንደ ሰሎሞን አምላክህን አስረስቶ ጣዖትን እንድታመልክ ያደርግሃል። ከዚህ ይሰውረን መጽሐፍ ነገሥት ካልዕ 1 11÷1-8

ትዕቢተኛ አትሁን ፦እንደ ሰናክሬም ትወድቃለህ።መጽሐፈ ነገሥት
ካልዕ 2 19÷35

ገንዘብን አትውደድ እንደ ይሁዳ ጌታህን ያስክድሃል። ማቴዎስ ወንጌል፦ 26÷14-16

ቀንድ ነገር ቢሆንም ገንዘብ በመውደድ ከስንት ነገር ርቀናል ከሃገራችን ከቤተሰባችን ከጓደኞቻችን ከልጆቻችን ሞልቶ በማይ ሞላ ሂወታችን......

ሥልጣንን አትውደድ፦እንደ አቤሴሎም በአባትህ ላይ ትነሣለህ፦ መጽሐፈ ሳሙኤል ካልዕ 2 15÷13-17

ዓለምን አትመልክት፦እንደ ሎጥ ሚስት የጨው ዐምድ ሆነህ ትቀራለህ፦ ዘፍጥረት 19÷ 22-23 1ኛ ቆ.ስ 2፥5

ማመናችሁ በእግዚአብሔር ኃይል እንጂ በሰው ጥበብ እንዳይሆን።
1ኛ ቆ.ስ፦ 2፥15

‹‹. . . ሕይወት አዙሪት ናት፡፡ ረጅም ርቀት የተጓዝክ ቢመስልህም የምትጨርሰው ከጀመርክበት ነው፡፡ ራቁትክን ትወለዳለህ እርቃንህን ወደ መቃብር ትወርዳለህ፡፡

በጥርስ አልባው ድድህ እየጋጥክ ትጀምራለህ ፤ ጥርሱን ባረገፈው ድድህ እያልጎጠጎጥክ ትጨርሳለህ፡፡ ዘመንም ተምኔታዊ ነው፡፡ መስከረም ጥቅምት ብሎ ያስጀምርህና መስከረም ብሎ ያመጣብሀል፡፡

ሰኞ ማክሰኞ ብለህ ተጉዘህ እንደገና ሰኞ ትላለህ፡፡ ሕይወት አዙሪት ናት መጀመርያህ መጨረሻህ ነው፡፡ የጀመርክበት አትርሳ መጨረሻህ ነውና የጀመርክበትን አትናቀው፤ ትጨርስበታለህና፡፡

ተራ ሰው ሆነህ ትጀምራለህ ተምረህ ዕውቀት ብትጨምር ፣ ነግደህ ሀብት ብታገኝ ፣ ክቡረ ክቡራን ሆነህ የወርቅ ካባ ብትለብስ የምትጨርሰው እንደ ተራ ሰው አፈር ለብሰህ ነው፡፡››

‹‹ልብ በል! በማወቅ ትጀምራለህ በመዘንጋት ትጨርሳለህ፡፡ ዕውቀት አላመጣህምና ዕውቀት ይዘህ አትሔድም፡፡ በለቅሶ ትጀምራለህ በጭንቅ ትጨርሳለህ፡፡

በሰው እቅፍ ትጀምራለህ በሰው ሸክም ትጨርሳለህ፡፡ ልደትህ ከሞትህ በምን ይለያል? ሞትህስ ከልደትህ በምን ይከፋል?

ሕይወት መጀመርያና መጨረሻዋ አንድ ነው፡፡ ከፀሐይ በታች አዲስ ነገር የለም፡፡ ልብ በል የዓለም ከንቱነት ግን ውበቷ ነው፡፡

ዓለም አዲስ ነገር ቢኖራ እኛን እንዴት በጸጸተን፡፡
      @shegainfom
ፍቅር : ሰላም : ለምድራችን !