Get Mystery Box with random crypto!

#ሺ_ዓመት_አይኖር ብዙ ጊዜ ለስንፍናችን ምክንያት ወይም ተስፋ ለመቁረጥ ሰበብ ከሚሆኑን ነግሮች | Shega info

#ሺ_ዓመት_አይኖር

ብዙ ጊዜ ለስንፍናችን ምክንያት ወይም ተስፋ ለመቁረጥ ሰበብ ከሚሆኑን ነግሮች አንዱ "ሺ ዓመት አይኖር" የሚለው አባባል ነው በእርግጥ በምድር ሺ ዓመት መኖር የቻለ የለም ረጅም ዓመት እንደኖረ የሚነገርለት ማቱሳላ እንኳን ሺ ዓመት አልኖረም ወዳጄ በተለይ እኛ ባለንበት በዚህ ዘመን ደግሞ እንኳን ሺ ዓመት ሊኖር ቀርቶ መቶ የሞላ እንኳን ቢገኝ የሚድያ የአንድ ወቅት የዜና ሽፋን መሆኑ የማይቀር ነው ስለዚህ ወደ ዘመናችን አባባሉን ማምጣት ከፈለግን መቶ ዓመት አይኖር በሚል ልንቀይረው ያስፈልጋል።

የሚያሳዝነው ሺ ዓመት አይኖር የምንለው ለመዝናናት ለመጨፈር ራስን ለመርሳት ፈቃደ ሥጋን እንደ ልብ ለመፈጸም ብቻ እንጂ ለመንፈሳዊ ሕይወት ለመሰናዳት አይደለም "አንቂ" የሚባሉ አካላት የዕድሜህን አጫርነት የሚነግሩህ ከሞት በኋላ ላለው ረጅሙ ዕድሜ በዚህች በአጭሯ የምድር ዕድሜህ በጎ ሰርተህ እንድታልፍ ሳይሆን እንዳትጨናነቅ ፈታ ብለህ(በእነርሱ አማርኛ) እንድትኖር ለማስታወስ ብቻ ነው።

ወዳጄ ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት ግን በምድር ስለምትኖርበት ዕድሜህ ሲነግርህ ቢበዛ(ቢበረታ) ሰማንያ ይልሃል ሺ ዓመት አይኖር ሲሉህ ቢበዛ ሰማንያ እርሱም በተገኘ በላቸው ታድያ በምድር የምትኖርበት ዕድሜህ ጥቂት ከሆነ ከዚያ በኋላ በሞት ይህን ምድር ከተሰናበትክ ከሞት በኋላ የት ትሄድ ይሆን?? የዚህ ምድር ኑሮህ በሞት ከተቋጨ በኋላ ሞተህ የምትቀር መስሎ እንዳይሰማህ ከሞት በኋላ ሕይወት አለህ ያውም እንደሰው ኖረህ ከሞትክ የምትነሳው እንደ ሰው ሆነህ የምትኖረውን ሕይወት ለመድገም

እንዳይመስልህ ከትንሣኤ በኋላ የምትኖረው እንደ መላእክት ነው “በትንሣኤስ እንደ እግዚአብሔር መላእክት በሰማይ ይሆናሉ”ማቴ 22፥30
ስለዚህ አስታውስ የምድር ኑሮህ ቢበዛ ሰማንያ ነው ያ ማለት ጥቂት ነው መጽሐፍ እንደሚነግርህ

“ሕይወታችሁ ምንድር ነው ጥቂት ጊዜ ታይቶ ኋላ እንደሚጠፋ እንፍዋለት ናችሁና”
ያዕ 4፥14

* ስለዚህ በምድር የምትቆየው ጥቂት ጊዜ ነውና:-*
ዛሬ የንስሐ አባት ያዝ
ዛሬ ንስሐ ግባ
ዛሬ ከተጣላሃቸው ታረቅ
ዛሬ ያስቀየምካቸውን ይቅር በል
ዛሬሥጋ ወደሙን ተቀበል

ነገ ሳይሆን ዛሬ መልካም ነገሮችህን ሁሉ ጀምር ምክንያቱም
“እነሆ፥ የመዳን ቀን አሁን ነው።”
2ኛ ቆሮ 6፥2
Join @shegainfom