Get Mystery Box with random crypto!

#ነገ_የሚባል_ቀን_የለም! የአንተን ሕይወት የሚመለከት ነገር ስታነብና ሲነካህ ያነበብከውን ነገር | Shega info

#ነገ_የሚባል_ቀን_የለም!

የአንተን ሕይወት የሚመለከት ነገር ስታነብና ሲነካህ ያነበብከውን ነገር ተቀብለህ ወዲያውኑ ተግብረው፡፡ ወዲያውኑ ወደ ተግባር ግባ፡፡ በቃ ጊዜ አትፍጅ፡፡ ሲጋራህን ጣል፤ ቢራ ተው፤ ጂም ግባ፤ ይቅርታ ጠይቅ… ወዘተ፡፡

ከእንደነዚህ አይነት ነገሮች ውስጥ አንዳንዶቹ ከሌሎቹ የበለጠ ከባድ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ የትኞቹም ቀላል ናቸው እያልኩኝ ግን አይደለም፡፡ እንደዚያ እንዳልሆነ አውቃለሁ፤ ግን ይቻላል - ለእኔም ለአንተም፡፡ እናም አሁን አድርገው፤ ነገን አትጠብቅ፡፡

ቁጭ ብለህ እያሰብክ ነገን አትጠብቅ፡፡ ሲጀመርም ነገ ስለመኖሩ ምንም ማረጋገጫ የለህም፡፡ ነገ ሚባል ቀን እንደሌለ አውቀህ ዛሬን ኑር፡፡ አእምሮህ ስለ ነገ እያሰበ ሰፊውን ጊዜህን እንዲወስድብህ እድል አትስጠው፡፡ ያለ እረፍት በአእምሮህ ውስጥ እየተንቀዋለለ የሚረብሽህ ነገር ካለ የማትወስንና የተወዛገብክ እንድትሆን ያደርግሃል፡፡

አእምሮህ ለምን ስለ ለውጥ መጨነቅ እንደሌለብህ፣ ለምን እንደማይሰራልህና እንዴት ከባድ እንደሆነ እየነገረ ወደ ኋላ ሊጎትትህ ይሞክራል። አንተ ግን አታዳምጠው። አሁን ጊዜው የሕይወት ውጥንቅጦችን መልክ መልክ የማስያዣ ጊዜ ነው!

ዛሬን በአግባቡ ኑረው፡፡

#በልኬት_ወደ_ስኬት መጽሐፍ