Get Mystery Box with random crypto!

Shega info

የቴሌግራም ቻናል አርማ shegainfom — Shega info S
የቴሌግራም ቻናል አርማ shegainfom — Shega info
የሰርጥ አድራሻ: @shegainfom
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 12.69K
የሰርጥ መግለጫ

▪ይህ የሸጋ info የቴሌግራም ቻናል ነዉ ▪ አስተማሪና ቁምነገር አዘል መረጃዎች በውብ አቀራርብ ለናንተ ይደርሳል #join በማረግ ቤተሰብ ይውኑን::

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2022-08-22 06:26:47 በ 2 ነገሮች ቀንህን ጀምር!

ሁሌም ቅድሚያ የምትሰጣቸው ነገሮች ህይወትህ ላይ ወሳኝ ናቸው። መጀመሪያ ለፈጣሪህ ቅድሚያ ስጥ ምክንያቱም እስካሁን እየተነፈስክ ነው፤ ስለዚህ ከእንቅልፍ እንደነቃህ አመስግነህ ፀሎትህን አድርስ።

ቀጥሎ ለራስህ ቅድሚያ ስጥ ምክንያቱም አንተ ስትኖር ነው ለምትወዳቸው ሁሉ የምትደርሰው፤ ስለዚህ ስለ ህልምህ በማሰብ፣ ስፖርት በመስራት፣ የሚጠቅምህን በማንበብ ቀንህን ጀምር።

በእነዚህ ሁለት ነገሮች ቀንህን ስትጀምር በዚህ አለም የሚገጥምህን የትኛውንም ችግር ታልፋለህ፤ ለምታውቃቸው ብቻ ሳይሆን ለማታውቃቸው ሁሉ ትተርፋለህ። ወዳጄ ቅድሚያ የምትሰጠውን እወቅ!

የተባረከ ማክሰኞ ተመኘንላችሁ
@shegainfom
ፍቅር : ሰላም : ለምድራችን !
4.6K views03:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-20 17:42:46
እስኪ አንድ ደስ የሚል ሀሳብ ላጫውታችሁ፤ አንድ ፋብሪካ ምርት ሲያመርት ምን እንዲሆን ነው? ብስኩትም ያምርት ዳቦ፣ ሞባይልም ያምርት መኪና አንድና ከዚያ በላይ ጥቅም እንዲሰጡ ታስቦ ነው።

እርግጠኛ መሆን የምንችለው የትኛውም ፋብሪካ እንዲሁ ምንም ጥቅም የማይሰጥ ምርት አያመርትም። ታዲያ የሰው ልጅ የፈጠረው ምርት ሁሉ ቢያንስ ለአንድ ምክንያት ከሆነ፤ ፈጣሪ እኛን ዝምብሎ ያለምክንያት አይፈጥረንም ማለት ነው።

እኔ አልረባም፣ አልጠቅምም የትም አልደርስም ልትል ትችላለህ ግን ፈጣሪ ከንቱ የሚሆን ምርት የለውም! ትንሽ ተረጋግተህ ማሰብ ነው የሚጠበቅብህ ያንተ መኖር በጣም የሚያስፈልጋቸው ብዙ ሰዎች አሉ።
ታስፈልጋለህ ወዳጄ! ታስፈልጊያለሽ እህቴ!
@Shegainfom
ፍቅር : ሰላም : ለምድራችን !
5.3K views14:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-20 11:24:30 ኢትዮጵያዊ(ግዕዝ) ስሞች ለልጆት ማውጣት ይፈልጋሉ ይምረጡ እስከ ትርጉሙ

1ማዕዶት፦መሻገሪያ ማለት ነው
2 ኖላዊ፦ጠባቂ ማለት ነው።
3 ማኅቶት፦ብርሃን ማለት ነው
4 ኂሩት፦በጎነት ማለት ነው።
5 ሜላት፦የሐር ግምጃ ማለት ነው።
6 ኅሩይ፦ምርጥ የተመረጠ ማለት ነው።ለሴት ኅሪት
7 ሮዛ፦ጽጌረዳ ማለት ነው።
8 ቀጸላ፦አክሊል ማለት ነው።
9 አስካል፦ፍሬ ማለት ነው።
10 በጽሐ፦ደረሰ ማለት ነው።
11 መሐሪ፦ይቅር ባይ ማለት ነው።
12 መንክር፦ልዩ ማለት ነው።
13 ሥሙር፦የተወደደ ማለት ነው።
14 ሐመልማል፦ለምለም ማለት ነው።
15 ነጸረ፦አየ ተመለከተ ማለት ነው።
16 ቅድስት፦ልዩ ምስጉን ማለት ነው።ቅዱስ ለወንድ ነው።
17 ይኄይስ፦ይሻላል ማለት ነው።
18 ጥዑም፦ጣፋጭ ማለት ነው
19 ግሩም፦የተፈራ ማለት ነው።
20 ተቅዋም፦መቅረዝ ማለት ነው።
21 ጸገየ፦አበበ ማለት ነው
22 ደምፀ፦ተሰማ ማለት ነው።
23 ጎሐጽባሕ፦የንጋት ኮከብ ማለት ነው።
24 ሐዋዝ፦መልካሙ ማለት ነው።
25 ሠናይ፦መልካሙ ማለት ነው።ሰናይት ለሴት ነው።
26 ፈታሒ፦ፈራጁ ማለት ነው።
27 መዓዛ፦ጥሩ ሽታ ማለት ነው።
28 መራሒ፦መሪ ማለት ነው።
29 ነጋሢ/ንጉሥ፦የነገሠ ማለት ነው።
30 ስቡሕ፦የተመሰገነ ማለት ነው።
31 ስብሐት፦ምስጋና ማለት ነው።
32 ብሩህ፦የበራ ማለት ነው።
33 ብርሃን፦ያው በቁሙ ብርሃን ማለት ነው።
34 ትጉህ፦የተጋ ማለት ነው።
35 አምኃ፦እጅ መንሻ ማለት ነው።
36 ልዑል፦ከፍ ያለው ማለት ነው።
37 ከሀሊ፦የሚችል ማለት ነው።
38 ዳግም፦ዳግመኛ ማለት ነው።
39 ማዕረር፦አዝመራ ማለት ነው።
40 ክቡር፦የተከበረ ማለት ነው።
41 አዕምሮ፦እውቀት ማለት ነው።
42 ደብሩ፦ተራራው ማለት ነው።
43 ምሥራቅ፦የፀሐይ መውጫ ማለት ነው።
44 ይባቤ፦እልልታ ማለት ነው።
45 ጥበቡ፦ብልሀተኛው ማለት ነው።
46 ሃይማኖት፦ሃይማኖት ማለት ነው።
47 ትሕትና፦ትሕትና ማለት ነው።
48 ተከሥተ፦ተገለጠ ማለት ነው።
49 በየነ፦ፈረደ ማለት ነው።
50 መኮንን፦ገዢ ማለት ነው።
51 ሐዳስ፦አዲሱ ማለት ነው።
52 ትንሣኤ፦መነሳት ማለት ነው።
53 ሢራክ፦ብልሀተኛ ማለት ነው።
54 ቡሩክ፦ምስጉን የተመሰገነ ማለት ነው።
55 ህላዌ፦መኖር ማለት ነው።
56 ማኅደር፦መኖሪያ ማለት ነው።
57 ሕይወት፦መኖር ማለት ነው።
58 ቤዛ፦መድኃኒት ማለት ነው። ቤዛዊት ለሴት ነው።
59 ኄራን፦ደጋጎች ማለት ነው።
60 መርዓዊ፦ሙሽራ ማለት ነው። መርዓዊት ለሴት ነው።
61 ተስፋ፦ተስፋ ማለት ነው።
62 ዜናዊ፦ነጋሪ ማለት ነው።
63 ጸዐዳ፦ነጭ ማለት ነው።
64 ጸጋ፦ስጦታ ማለት ነው።
65 ብሥራት፦የምሥራች ማለት ነው።
66 ኅሊና፦ማሰቢያ፥ሀሳብ እውቀት ማለት ነው።
67 ማህሌት፦ምስጋና ማለት ነው።
68 ሐሴት፦ደስታ ማለት ነው።
69 ፍሥሓ፦ደስታ ማለት ነው።
70 ትርሲት፦ሽልማት ማለት ነው። በተጨማሪ ስርጉት ማለት የተሸለመች ያጌጠች ማለት ነው።
71 ምዕራፍ፦ማረፊያ ማለት ነው።
72 መቅደስ፦ማመስገኛ፥ መመስገኛ ማለት ነው።
73 ዋካ፦ብርሃን ማለት ነው።
74 ረድኤት፦ እርዳታ ማለት ነው።
75 ጽጌ፦አበባ ማለት ነው።
76 ሠረገላ፦መኪና ማለት ነው።
77 አማን፦እውነት ማለት ነው።
78 አሜን፦ይሁንልኝ ይደረግልኝ ማለት ነው።
79 ተንከተም፦ድልድይ ማለት ነው። ሰዋስው መሰላል ነው።
80 ጸዳሉ፦ብርሃኑ ማለት ነው።
@shegainfom
ፍቅር : ሰላም : ለምድራችን !
4.7K views08:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-17 19:10:03
የ 2015 በዓላትና አጽዋማት
#ሼር
5.9K views16:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-17 07:51:53
ወዳጄ ሁሌም
━⊱✿⊰━
ከእንቅልፍህ ስትነሳ ተመስገን በል በዛው የቀሩ ስንት አሉና
ከአልጋቹህ ስትነሱ ተመስገን በል ስንት የአልጋ ቁራኛ አለና
ስትስቁ ተመስገን በል በችግር አንገቱን የደፋ አለና
ስትራመዱ ተመስገን በሉ መራመድ ያቃታቸው አሉና

#ወዳጄ ሆይ ስትወጣም ስትገባም ተመስገን በል እደወጣህ ባለ መቅረትህ እግዚአብሔርን አመስግን
ቅያሪ ልብስ ካለህ ተመስገን በል ስንት እራቁቱን የሚሄድ አለና
ስታወራ ተመስገን በል ስንቶች ማውራት የማይችሉ አሉና
ስትሰማ ተመስገን በል ስንት መልካሙን ነገር ለመስማት የሰው ድምፅ የናፈቃቸው አሉና

የሞቀ ቤት ውስጥ ላይ በመሆንህ ተመስገን በል
እግዚአብሔርን አመስግን ቤት አጥተው ጎዳና ላይ ወድቀው የሚያድሩ አሉና
ተመስገን ተመስገን
እንበል የእግዚአብሔር ምህረቱ ለዘላለም ነውና
•••
“ሃሌ ሉያ፤ ቸር ነውና፥ ምህረቱም ለዘላለም ነውና እግዚአብሔርን አመስግኑ።”
— መዝሙር 106፥1
•••
@Shegainfom
ፍቅር : ሰላም : ለምድራችን !
6.1K views04:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-12 07:42:19
ሳታልፍ በፊት ኑር!

በዚህ አለም የሚያረጋጋ ቃል ቢኖር አንዱ "ሁሉም ያልፋል" የሚለው ነው፤ ሀዘኑም ያልፋል፣ደስታውም ያልፋል፣ ንዴቱም ያልፋል፣ እርካታውም ያልፋል፤ ሌላውን ተወው አንተም እኔም እናልፋለን! በፍጥረት አለም ፀንቶ የሚኖር ነገር ቢኖር አምላክ ብቻ ነው።

ታዲያ ለሚያልፍ ችግር ለምን አብዝተህ ትጨነቃለህ? ለሚያልፍ ቀን ለምን ራስህን ትጎዳለህ? ህይወትህን ነብስ ዝራበት፤ የምትወደውን ስራ፣ የምትወዳትን የራስህ ለማድረግ ተዘጋጅ፣ መንፈሳዊነትህን ሳትለቅ የምድርን በረከት ሁሉ አጣጥም፤ ሳታልፍ በፊት ኑር ወዳጄ!

ድንቅ ቀን ተመኘንላችሁ
7.9K views04:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-10 17:41:10 ከባለፈዉ የቀጠለ የመፅሐፍ ቅዱስ ስሞች #ክፍል 2

1 ባሮክ ፡ ብሩክ ማለት ነዉ
2 ሮቤል፦እነሆ ወንድ ልጅ ማለት ነው።
3 ኤርምያስ፦እግዚአብሔር ከፍ ያደርጋል ማለት ነው።
4 ሮብዓም፦ሕዝብ ይብዛ ማለት ነው።
5 ማራናታ፦ጌታ ሆይ ና ማለት ነው።
6 ቤቴል፦የእግዚአብሔር ቤት ማለት ነው።
7 ቄርሎስ፦የተመረጠ ምርጥ ማለት ነው።
8 እስጢፋኖስ፦አክሊል ማለት ነው።
9 ሳውል/ሳኦል፦ከእግዚአብሔር የተለመነ ማለት ነው።
10 ሴዴቅያስ፦የእግዚአብሔር ጽድቅ ማለት ነው።
11 ፊቅጦር፦ኀዘኔን አራቀልኝ ማለት ነው።
12 ንፍታሌም፦ታጋይ የሚታገል ማለት ነው።
13 ዮርዳኖስ፦ወራጅ ውሃ ማለት ነው።
14 ዮአስ፦እግዚአብሔር ሰጥቷል ማለት ነው።
15 ገነት፦የአትክልት ስፍራ ማለት ነው።
16 ፊልድልፍያ፦የወንድማማች ፍቅር ማለት ነው።
17 ዲና፦ፈረደ ማለት ነው።
18 ማኑሄ፦እረፍት ማለት ነው።
19 መልሕቅ፦ከብረት የተሠራ የመርከብ ማቆሚያ
20 ራማ፦ከፍታ ማለት ነው።
21ቴዎድሮስ፦የእግዚአብሔር ስጦታ ማለት ነው።
22 ፊላታዎስ፦የአምላክ ወዳጅ ማለት ነው።
23 ሕርያቆስ፦ኅሩይ ምርጥ ማለት ነው።
24 ፊልጶስ፦ወንድም ወዳጅ ማለት ነው።
25 ቶማስ፦ፀሐይ ማለት ነው።
26 ታዴዎስ፦እሸቱ ማለት ነው።(ግብራዊ ትርጓሜ)
27 ማትያስ፦ፀሐይ ወይም ምትክ ማለት ነው።
28 ቀሌምንጦስ፦ግንብ ማለት ነው።
29 አቤል፦በግ ወይም ደመና ማለት ነው።
30 ኖኅ፦ደስታ ማለት ነው።
31 ሴም፦ተሾመ ማለት ነው።
32 ይሥሐቅ፦ደስታ አንድም ይሳቅ ማለት ነው።
33 ሙሴ፦የውሃ ልጅ ማለት ነው
34 አሮን፦የእግዚአብሔር ተራራ ማለት ነው።
35 ጌዴዎን፦እግዚአብሔር ኃያል ነው ማለት ነው።
36 እሴይ፦ዋጋየ ማለት ነው።
37 አሚናዳብ፦መንፈስቅዱስ ማለት ነው።
38 ዳዊት፦የተወደደ ልበ አምላክ ማለት ነው፣
39 ዕንባቆም፦ጠቢብ አዋቂ አስተዋይ ማለት ነው።
40 ሄኤሜን፦ምኞቴን አገኘሁ ማለት ነው።
41 አሞጽ፦እግዚአብሔር ጽኑ ነው ማለት ነው፣
42 ዮናስ፦ርግብ ማለት ነው።
43 ሐጌ፦የእግዚአብሔር መልእክተኛ ማለት ነው።
44 ራኄል፦በግዕት ማለት ነው።
45 ዕዝራ፦ረዳቴ ማለት ነው።
46 ሔርሜላ፦ከክብር ዘመድ የተገኘች ማለት ነው።
47 መርቆሬዎስ፦የአባት ወዳጅ ማለት ነው።
48 ኤጲፋንዮስ፦ምስጢር ገላጭ ማለት ነው።
49 ሜሮን፦የተባረከ ሽቱ ማለት ነው።
50 ሱላማጢስ፦ሰላማዊት ማለት ነው።
51 ሶምሶን፦ፀሐይ ማለት ነው።
52 ብንያም፦የቀኝ እጄ ልጅ ማለት ነው።
53 ማርታ፦እመቤት ማለት ነው።
54 ሊዲያ፦ፈራሂተ እግዚአብሔር ማለት ነው።
55 ኤፍሬም፦ፍሬያማ ፍሬው ማለት ነው።
56 ኤፍራታ፦ክብርት የተከበረች ማለት ነው።
57 ታዴዎስ፦ተወዳጅ ወይም ፍቁር ማለት ነው።(ቃላዊ ትርጓሜው)
58 ኢየሩሳሌም፦የሰላም ሀገር ማለት ነው።
59 ሄኖስ፦ሰው ማለት ነው።
60 ሰሎሜ፦ሰላም ማለት ነው።

ማስታወሻ፦ከላይ ከጻፍኳቸው ውስጥ አንዳንድ ስሞች ከ81ዱ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የማይገኙ ከሌሎች የታሪክ እና የገድል መጻሕፍት ውስጥ የሚገኙ ስሞች መሆናቸውን ማሳወቅ እፈልጋለሁ።

በትረማርያም
#ሼር

የ ሙሉ ትንተና ዮቲዮብ ቻናላችን ይቀላቀሉን
https://m.youtube.com/channel/UCHYsjv2HLu-K6e0C7MxxVmA/featured
7.4K views14:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-09 16:08:29 ከመፅሐፍ ቅዱስ የልጇት ስም ማውጣት ይፈልጋሉ እስከ ትርጉሙ

1 ሩሐማ፦ምሕረት ማለት ነው።
2 ዮዳሔ፦እግዚአብሔር ያውቃል ማለት ነው።
3 ቴዎፍሎስ፦የእግዚአብሔር ወዳጅ ማለት ነው።
4 ኑኃሚን፦ደስታየ ማለት ነው።
5 ናትናኤል፦የእግዚአብሔር ስጦታ ማለት ነው።
6 አዛሄል፦እግዚአብሔር ያያል ማለት ነው።
7 ኢዮስያስ፦እግዚአብሔር ይደግፋል ማለይ ነው
8 ኢዩኤል፦እግዚአብሔር አምላክ ነው ማለት ነው።
9 በርናባስ፦የመጽናናት ልጅ ማለት ነው።
10 ሶፎንያስ፦እግዚአብሔር ሰውሯል/ጠብቋል ማለት ነው።
11 ሕዝቅኤል፦እግዚአብሔር ብርታትን ይሰጣል ማለት ነው።
12 ኬልቅያስ፦እድል ፈንታየ እግዚአብሔር ማለት ነው
13 ሳሙኤል፦እግዚአብሔር ሰማኝ ማለት ነው።
14 ሚኪያስ፦ እንደ እግዚአብሔር ያለ ማን ነው! ማለት ነው።
15 ሆሴዕ፦እግዚአብሔር ያድናል ማለት ነው።
16 ሔዋን፦የሕያዋን ሁሉ እናት ማለት ነው።
17 ሕዝቅያስ፦እግዚአብሔር ኃይሌ ነው ማለት ነው።
18 መልከጼዴቅ፦የሰላም ንጉሥ ማለት ነው።
19 ሚልኪያስ፦መልእክተኛየ ማለት ነው።
20 ሣራ፦ልዕልት ማለት ነው።
21 ስምዖን፦ሰማ ማለት ነው።
22 ብንያም፦የቀኝ እጄ ልጅ ማለት ነው።
23 ናሆም፦መጽናናት ማለት ነው።
24 ናታን፦ እግዚአብሔር ሰጥቷል ማለት ነው።
25 አልዓዛር፦እግዚአብሔር ረድቷል ማለት ነው።
26 አስቴር፦ኮከብ ማለት ነው፣
27 አቤሜሌክ፦የንጉሥ አገልጋይ ማለት ነው።
28 አቤሴሎም፦አባቴ ሰላም ነው ማለት ነው።
29 አብድዩ፦የእግዚአብሔር አገልጋይ ማለት ነው።
30 አብራም፦ታላቅ አባት ማለት ነው።
31 አብርሃም፦የብዙዎች አባት ማለት ነው
32 አኪያ፦እግዚአብሔር ወንድሜ ነው ማለት ነው።
33 አክዐብ፦የአባት ወንድም ማለት ነው።
34 ባሮክ፦ቡሩክ ማለት ነው።
35 አዳም፦መልካሙ ማለት ነው።
36 ኢሳይያስ፦ እግዚአብሔር ደኅንነት ነው ማለት ነው።
37 ባርቅ፦መብረቅ ማለት ነው።
38 ኢያሱ፦እግዚአብሔር አዳኝ ነው ማለት ነው።
39 ኢዮሳፍጥ፦እግዚአብሔር ፈርዷል ማለት ነው።
40 ኢዮራም፦እግዚአብሔር ከፍ ከፍ አለ ማለት ነው።
41 ኢዮርብዓም፦ሕዝቡ እየበዛ ይሄዳል ማለት ነው።
42 ቤተልሔም፦የእንጀራ ቤት ማለት ነው።
43 ኢዮአስ፦እግዚአብሔር ሰጥቷል ማለት ነው።
44 ኢዮአቄም፦እግዚአብሔር አቆመ ማለት ነው።
45 ኢዮአብ፦እግዚአብሔር አባት ነው ማለት ነው።
46 ኢዮአታም፦እግዚአብሔር ፍጹም ነው ማለት ነው።
47 ኢዮአካዝ፦እግዚአብሔር ይዟል ማለት ነው።
48 ኤልሳዕ፦እግዚአብሔር ደኅንነት ነው ማለት ነው።
49 ኤልያስ፦እግዚአብሔር አምላክ ነው ማለት ነው።
50 ኤልያቄም፦እግዚአብሔር ያስነሳል ማለት ነው።
51 ኤዶም፦ቀይ ማለት ነው
52 እስራኤል፦ከእግዚአብሔር ጋር ይታገላል ያሸንፍማል ማለት ነው።
53 ኤልሳቤጥ፦እግዚአብሔር መሐላየ ነው ማለት ነው።
54 ኤልሻዳይ፦ሁሉን ቻይ አምላክ ማለት ነው።
55 ሀሌሉያ፦እግዚአብሔርን አመስግኑ ማለት ነው።
56 ሰሎሞን፦ሰላማዊ ማለት ነው።
57 ኬብሮን፦ኅብረት ማለት ነው
58 አዛርያስ፦እግዚአብሔር ረድቷል ማለት ነው።
59 ኤደን፦ደስታ ማለት ነው።
60 ዖዝያን፦እግዚአብሔር ኃይሌ ነው ማለት ነው።
61 ዘካርያስ፦እግዚአብሔር ያስታውሳል ማለት ነው።
62 ይሳኮር፦ ዋጋዬ ማለት ነው
63 ይዲድያ፦በእግዚአብሔር የተወደደ ማለት ነው።
64 ዮሐናን፦እግዚአብሔር ጸጋ ሰጪ ነው ማለት ነው።
65 ዮሐንስ፦እግዚአብሔር ጸጋ ነው ማለት ነው።
66 ዮሴፍ፦ይጨምር ማለት ነው።
67 ዮናስ፦ርግብ ማለት ነው።
68 ዮናታን፦እግዚአብሔር ሰጥቷል ማለት ነው።
69 ዮአኪን፦እግዚአብሔር ያቆማል ማለት ነው።
70 ዮካብድ፦እግዚአብሔር ክብር ነው ማለት ነው።
71 ምናሴ፦ማስረሻ ማለት ነው።
72 ዮፍታሔ፦እግዚአብሔር ይከፍታል ማለት ነው።
73 ዲቦራ፦ንብ ማለት ነው።
74 ዳንኤል፦እግዚአብሔር ፈራጅ ነው ማለት ነው።
75 ጎዶልያስ፦እግዚአብሔር ታላቅ ነው ማለት ነው።
76 ጽዮን፦አምባ ማለት ነው።
77 ጳውሎስ፦ብርሃን ማለት ነው።
78 ሴት፦ምትክ ማለት ነው።
79 ጴጥሮስ፦አለት ማለት ነው።
80 ሄኖክ፦ታደሰ ማለት ነው።
81 ኄራኒ፦ሰላም እና ፍቅር ማለት ነው።

@shegainfom
ፍቅር : ሰላም : ለምድራችን !
6.2K views13:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-08 18:46:04 #_ከንስር_የምንማራው_የአመራርነት_ጥበብ

ንስሮች ብቻቸውን በከፍተኛ ከፍታ ውስጥ ይበራሉ ። ከቁራዎችና ከትንንሽ ወፎች ጋር አይበሩም ።

#_ማለት_የተፈለገው ፦ ጥሩ አእምሮ ከሌላቸው ወይም ትንሽ አእምሮ ካላቸው ሰዎች ራቅ ። እነሱ ወደታች ይጎትቱሃል ። ንስር ከንስር ጋር ነው የሚበረው ። አንተም ጥሩ ጓደኛን ምረጥ ።

ንስሮች ትክክለኛ እይታ አላቸው ። ከ5 ኪሎ ሜትር የሆነ ነገር ላይ የማተኮር ችሎታ አላቸው ። ንስሩ ምንም አይነት እንቅፋት ቢገጥመው ትኩረቱ የፈለገውን እስከሚያገኝ ድረስ አይንቀሳቀስም ።

#_ማለት_የተፈለገው ፦ ራዕይ ይኑርህ እንቅፋት ቢገጥምምህም ውጤታማ ትሆናለህ ።
ንስር የሞተ ነገር አይበላም ። ሁሌም ትኩስ ነገር ነው የሚበላው ።

#_ማለት_የተፈለገው ፦ ባለፈው መንገድህ አትደገፍ ። ለማሸነፍ አዳዲስ የፊት ለፊት መንገዶችን ፈልግ ። ያለፈውን ባለበት ተወው ።

ንስሮች አውሎ ንፋሱን ይወዱታል ። ደመናው ሲመጣ ንስሩ ይደሰታል ምክንያቱም ደመናውን ተጠቅሞ እራሱን ከፍ ያደርግበታል ። አንዴ የወጀቡን ንፋስ ካገኘ ንስሩ አውሎ ንፋሱን ተጠቅሞ እራሱን ከደመና በላይ ከፍ ያደርጋል ። ይህ ንስሩን ክንፎቹ በቀላሉ እንዲበርና እንዲያርፍ ይረዳዋል ።

#_ማለት_የተፈለገው ፦ ችግሮችን ፊት ለፊት መጋፈጥ በስተመጨረሻ አሸናፊና ጠንካራ ያደርግሃል ። የህይወት ወጀብን ተጠቅመን ወደ ከፍታ መውጣት እንችላለን ።

ንስሮች ማደግ ሲጀምሩ ጎጆው የተሰራበትን ላባና ለስላሳ ሳሩን ይነሳና እሾሁ ብቻ ይቀራል ። በዚህም ጊዜ ወጣቶቹ ንስሮች ስለማይመቻቸው ይበራሉ ።

#_ማለት_የተፈለገው ፦ ከኮንፈርት ዞን ወይም ምቾት ቀጠና ውጣ ምክንያቱም እዚያ ውስጥ እድገት የለም ።

ንስሩ ሲያረጅ ላባዎቹ ደካማ ይሆኑና በፍጥነትና ከፍ ብሎ እንዳይበር ስለሚያደርገው ሊሞትም ይችላል ። ስለዚህ በተራሮች ውስጥ ብቻውን ተነጥሎ ይቀመጣል ።

በመጨረሻም ላባዎቹን ሁሉ ነቅሎ ቢኩን አፉን ከተራራ ላይ ወደታች በመውደቅ ሰብሮ አዲስ ላባና አዲስ ቢክ አብቅሎ እንደበፊቱ እስኪሆን እዚያው ይጠብቃል ።

#_ማለት_የተፈለገው ፦ የድሮ ልማዶቻችንን መተውና በህይወታችን ላይ ዋጋ የማይጨምሩት ሁሉ መጥፋት አለባቸው ።

ሼር ያድርጉ ፔጁን ይቀላቀሉ
Join @ortodoxslijoch
5.8K viewsedited  15:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-08 07:08:38 "የሠራዊት ጌታ ከእኛ ጋር ነው፤ የያዕቆብ አምላክ መጠጊያችን ነው።” መዝሙር 46፥7
•••
በቅርብ ወራት ውስጥ ዓለም ላይ የምናያቸውና የምንሰማቸው ጭንቀቶች እና ሁካታዎች ከባድ ናቸው።

ስለ ወረርሽኙ፣ የሰዎች ሕይወት መጥፋት፣ የተፈጥሮ አደጋዎች እንዲሁም በማህበረሰቡ ውስጥ እየተፈጠሩ ስላሉና በዜና ላይ የምንሰማቸው ስፍር ቁጥር የሌላቸው አሳዛኝ ክስተቶችን ስናስብ ልባችን ያዝናል።

እንደዚህ ዓይነት ሽብር፣ ህመም፣ ስቃይና ከእኛ ቁጥጥር ውጭ የሆነ ነገር ስንሰማና ስናይ፣ ፍርሃት ሊሰማን ይችል ይሆናል። በአለማችን ላይ ምን እየሆነ ነው ያለው፣ ሕይወት ከቁጥጥር ውጭ የሆነው ለምንድን ነው፣ እናም መቼ ነው ደህንነት እና ሰላም እንደገና ልናገኝ የምንችለው ብለን እናስባለን?

እንደዚህ አይነት የፍርሃት ስሜት በሚሰማን ጊዝያት መዝሙር 46 ላይ ያሉትን የተስፋ ቃሎች በእርጋታ እናንብባቸው፣ ከዛም በምንም ነገር መፍራት እንደሌለብን እንረዳለን።

"አምላካችን መጠጊያችንና ኃይላችን፥ ባገኘን በታላቅ መከራም ረዳታችን ነው። ስለዚህ ምድር ብትነዋወጥ፥ ተራሮችም ወደ ባሕር ልብ ቢወሰዱ አንፈራም። ውኆቻቸው ጮኹ ተናወጡም፥ ተራሮችም ከኃይሉ የተነሣ ተናወጡ።"
— መዝሙር 46፥1-3

የትኛውም ዓይነት ፍርሃት አእምሯችንን
መቆጣጠር ሲፈልግ፣ መዝሙር 46ን እናስታውስ በሕይወታችን ውስጥ፣ በምንኖርበት ከተማ፣ በአገራችን ወይንም በዓለማችን ውስጥ ማንኛውም ነገር ቢከሰት እንኳን እግዚአብሔር ከእኛ ጋር መሆኑን የሚያሳየን ቆንጆ ማሳሰቢያ ነው።

እነዚህ የተስፋ ቃሎች እግዚአብሔር አሁንም መጠጊያችንና ረዳታችን መሆኑን ያረጋግጡልናል።

☞ ፍርሃትና ጭንቀት በሚሰማን ጊዝያት እንዲሁም አስቸጋሪ ጊዜያትን ለማለፍ ጥንካሬ እና ሰላም የምናገኝው በእግዚአብሔር ብቻ ነው ።
•••
☞ 🅢🅗🅐🅡🅔
•••
@shegainfom
5.9K views04:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ