Get Mystery Box with random crypto!

እስኪ አንድ ደስ የሚል ሀሳብ ላጫውታችሁ፤ አንድ ፋብሪካ ምርት ሲያመርት ምን እንዲሆን ነው? ብስኩ | Shega info

እስኪ አንድ ደስ የሚል ሀሳብ ላጫውታችሁ፤ አንድ ፋብሪካ ምርት ሲያመርት ምን እንዲሆን ነው? ብስኩትም ያምርት ዳቦ፣ ሞባይልም ያምርት መኪና አንድና ከዚያ በላይ ጥቅም እንዲሰጡ ታስቦ ነው።

እርግጠኛ መሆን የምንችለው የትኛውም ፋብሪካ እንዲሁ ምንም ጥቅም የማይሰጥ ምርት አያመርትም። ታዲያ የሰው ልጅ የፈጠረው ምርት ሁሉ ቢያንስ ለአንድ ምክንያት ከሆነ፤ ፈጣሪ እኛን ዝምብሎ ያለምክንያት አይፈጥረንም ማለት ነው።

እኔ አልረባም፣ አልጠቅምም የትም አልደርስም ልትል ትችላለህ ግን ፈጣሪ ከንቱ የሚሆን ምርት የለውም! ትንሽ ተረጋግተህ ማሰብ ነው የሚጠበቅብህ ያንተ መኖር በጣም የሚያስፈልጋቸው ብዙ ሰዎች አሉ።
ታስፈልጋለህ ወዳጄ! ታስፈልጊያለሽ እህቴ!
@Shegainfom
ፍቅር : ሰላም : ለምድራችን !