#_ከንስር_የምንማራው_የአመራርነት_ጥበብ ንስሮች ብቻቸውን በከፍተኛ ከፍታ ውስጥ ይበራሉ ። ከቁራዎችና ከትንንሽ ወፎች ጋር አይበሩም ። #_ማለት_የተፈለገው ፦ ጥሩ አእምሮ ከሌላቸው ወይም ትንሽ አእምሮ ካላቸው ሰዎች ራቅ ። እነሱ ወደታች ይጎትቱሃል ። ንስር ከንስር ጋር ነው የሚበረው ። አንተም ጥሩ ጓደኛን ምረጥ ። ንስሮች ትክክለኛ እይታ አላቸው ። ከ5 ኪሎ ሜትር የሆነ ነገር ላይ የማተኮር ችሎታ አላቸው ። ንስሩ ምንም አይነት እንቅፋት ቢገጥመው ትኩረቱ የፈለገውን እስከሚያገኝ ድረስ አይንቀሳቀስም ። #_ማለት_የተፈለገው ፦ ራዕይ ይኑርህ እንቅፋት ቢገጥምምህም ውጤታማ ትሆናለህ ። ንስር የሞተ ነገር አይበላም ። ሁሌም ትኩስ ነገር ነው የሚበላው ። #_ማለት_የተፈለገው ፦ ባለፈው መንገድህ አትደገፍ ። ለማሸነፍ አዳዲስ የፊት ለፊት መንገዶችን ፈልግ ። ያለፈውን ባለበት ተወው ። ንስሮች አውሎ ንፋሱን ይወዱታል ። ደመናው ሲመጣ ንስሩ ይደሰታል ምክንያቱም ደመናውን ተጠቅሞ እራሱን ከፍ ያደርግበታል ። አንዴ የወጀቡን ንፋስ ካገኘ ንስሩ አውሎ ንፋሱን ተጠቅሞ እራሱን ከደመና በላይ ከፍ ያደርጋል ። ይህ ንስሩን ክንፎቹ በቀላሉ እንዲበርና እንዲያርፍ ይረዳዋል ። #_ማለት_የተፈለገው ፦ ችግሮችን ፊት ለፊት መጋፈጥ በስተመጨረሻ አሸናፊና ጠንካራ ያደርግሃል ። የህይወት ወጀብን ተጠቅመን ወደ ከፍታ መውጣት እንችላለን ። ንስሮች ማደግ ሲጀምሩ ጎጆው የተሰራበትን ላባና ለስላሳ ሳሩን ይነሳና እሾሁ ብቻ ይቀራል ። በዚህም ጊዜ ወጣቶቹ ንስሮች ስለማይመቻቸው ይበራሉ ። #_ማለት_የተፈለገው ፦ ከኮንፈርት ዞን ወይም ምቾት ቀጠና ውጣ ምክንያቱም እዚያ ውስጥ እድገት የለም ። ንስሩ ሲያረጅ ላባዎቹ ደካማ ይሆኑና በፍጥነትና ከፍ ብሎ እንዳይበር ስለሚያደርገው ሊሞትም ይችላል ። ስለዚህ በተራሮች ውስጥ ብቻውን ተነጥሎ ይቀመጣል ። በመጨረሻም ላባዎቹን ሁሉ ነቅሎ ቢኩን አፉን ከተራራ ላይ ወደታች በመውደቅ ሰብሮ አዲስ ላባና አዲስ ቢክ አብቅሎ እንደበፊቱ እስኪሆን እዚያው ይጠብቃል ። #_ማለት_የተፈለገው ፦ የድሮ ልማዶቻችንን መተውና በህይወታችን ላይ ዋጋ የማይጨምሩት ሁሉ መጥፋት አለባቸው ። ሼር ያድርጉ ፔጁን ይቀላቀሉ Join @ortodoxslijoch 5.8K viewsedited 15:46