Get Mystery Box with random crypto!

'የሠራዊት ጌታ ከእኛ ጋር ነው፤ የያዕቆብ አምላክ መጠጊያችን ነው።” መዝሙር 46፥7 ••• በቅርብ | Shega info

"የሠራዊት ጌታ ከእኛ ጋር ነው፤ የያዕቆብ አምላክ መጠጊያችን ነው።” መዝሙር 46፥7
•••
በቅርብ ወራት ውስጥ ዓለም ላይ የምናያቸውና የምንሰማቸው ጭንቀቶች እና ሁካታዎች ከባድ ናቸው።

ስለ ወረርሽኙ፣ የሰዎች ሕይወት መጥፋት፣ የተፈጥሮ አደጋዎች እንዲሁም በማህበረሰቡ ውስጥ እየተፈጠሩ ስላሉና በዜና ላይ የምንሰማቸው ስፍር ቁጥር የሌላቸው አሳዛኝ ክስተቶችን ስናስብ ልባችን ያዝናል።

እንደዚህ ዓይነት ሽብር፣ ህመም፣ ስቃይና ከእኛ ቁጥጥር ውጭ የሆነ ነገር ስንሰማና ስናይ፣ ፍርሃት ሊሰማን ይችል ይሆናል። በአለማችን ላይ ምን እየሆነ ነው ያለው፣ ሕይወት ከቁጥጥር ውጭ የሆነው ለምንድን ነው፣ እናም መቼ ነው ደህንነት እና ሰላም እንደገና ልናገኝ የምንችለው ብለን እናስባለን?

እንደዚህ አይነት የፍርሃት ስሜት በሚሰማን ጊዝያት መዝሙር 46 ላይ ያሉትን የተስፋ ቃሎች በእርጋታ እናንብባቸው፣ ከዛም በምንም ነገር መፍራት እንደሌለብን እንረዳለን።

"አምላካችን መጠጊያችንና ኃይላችን፥ ባገኘን በታላቅ መከራም ረዳታችን ነው። ስለዚህ ምድር ብትነዋወጥ፥ ተራሮችም ወደ ባሕር ልብ ቢወሰዱ አንፈራም። ውኆቻቸው ጮኹ ተናወጡም፥ ተራሮችም ከኃይሉ የተነሣ ተናወጡ።"
— መዝሙር 46፥1-3

የትኛውም ዓይነት ፍርሃት አእምሯችንን
መቆጣጠር ሲፈልግ፣ መዝሙር 46ን እናስታውስ በሕይወታችን ውስጥ፣ በምንኖርበት ከተማ፣ በአገራችን ወይንም በዓለማችን ውስጥ ማንኛውም ነገር ቢከሰት እንኳን እግዚአብሔር ከእኛ ጋር መሆኑን የሚያሳየን ቆንጆ ማሳሰቢያ ነው።

እነዚህ የተስፋ ቃሎች እግዚአብሔር አሁንም መጠጊያችንና ረዳታችን መሆኑን ያረጋግጡልናል።

☞ ፍርሃትና ጭንቀት በሚሰማን ጊዝያት እንዲሁም አስቸጋሪ ጊዜያትን ለማለፍ ጥንካሬ እና ሰላም የምናገኝው በእግዚአብሔር ብቻ ነው ።
•••
☞ 🅢🅗🅐🅡🅔
•••
@shegainfom