Get Mystery Box with random crypto!

ወዳጄ ሁሌም ━⊱✿⊰━ ከእንቅልፍህ ስትነሳ ተመስገን በል በዛው የቀሩ ስንት አሉና ከአልጋቹህ | Shega info

ወዳጄ ሁሌም
━⊱✿⊰━
ከእንቅልፍህ ስትነሳ ተመስገን በል በዛው የቀሩ ስንት አሉና
ከአልጋቹህ ስትነሱ ተመስገን በል ስንት የአልጋ ቁራኛ አለና
ስትስቁ ተመስገን በል በችግር አንገቱን የደፋ አለና
ስትራመዱ ተመስገን በሉ መራመድ ያቃታቸው አሉና

#ወዳጄ ሆይ ስትወጣም ስትገባም ተመስገን በል እደወጣህ ባለ መቅረትህ እግዚአብሔርን አመስግን
ቅያሪ ልብስ ካለህ ተመስገን በል ስንት እራቁቱን የሚሄድ አለና
ስታወራ ተመስገን በል ስንቶች ማውራት የማይችሉ አሉና
ስትሰማ ተመስገን በል ስንት መልካሙን ነገር ለመስማት የሰው ድምፅ የናፈቃቸው አሉና

የሞቀ ቤት ውስጥ ላይ በመሆንህ ተመስገን በል
እግዚአብሔርን አመስግን ቤት አጥተው ጎዳና ላይ ወድቀው የሚያድሩ አሉና
ተመስገን ተመስገን
እንበል የእግዚአብሔር ምህረቱ ለዘላለም ነውና
•••
“ሃሌ ሉያ፤ ቸር ነውና፥ ምህረቱም ለዘላለም ነውና እግዚአብሔርን አመስግኑ።”
— መዝሙር 106፥1
•••
@Shegainfom
ፍቅር : ሰላም : ለምድራችን !