Get Mystery Box with random crypto!

Shega info

የቴሌግራም ቻናል አርማ shegainfom — Shega info S
የቴሌግራም ቻናል አርማ shegainfom — Shega info
የሰርጥ አድራሻ: @shegainfom
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 12.69K
የሰርጥ መግለጫ

▪ይህ የሸጋ info የቴሌግራም ቻናል ነዉ ▪ አስተማሪና ቁምነገር አዘል መረጃዎች በውብ አቀራርብ ለናንተ ይደርሳል #join በማረግ ቤተሰብ ይውኑን::

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2022-08-03 07:00:22 𝓓𝓷:
አንድ ቅቤ አምራች ገበሬና ዳቦ
_____

አምራች ነጋዴ እንደ አጋጣሚ ድግስ ላይ ተገናኝተው ያወራሉ፡፡
በጨዋታቸው በጣም ስለተግባቡ ከዚህ በኋላ አጋጣሚ ፈጥረው ለመገናኘት ይስማማሉ፡፡ ነጋዴው
ጠዋት ጠዋት 300 ግራም ዳቦ ሲልክለት ገበሬው ደግሞ ማታ ማታ 300 ግራም ቅቤ ሊልክለት
ተስማሙ፡፡

በዚህ መልኩ ብዙ ጊዜ ከቆዩ በኋላ ነጋዴ የቅቤ መጠን እየቀነሰ መሄዱን አየ፡፡ በመጨረሻም ሚዛን
ላይ ሲያስቀምጠው 150 ግራም ሆኖ አገኘው፡፡ በዚህም በጣም አዘነ፤ ተበሳጨም፡፡ ገበሬውንም
አስጠራው፡፡ ሌሎች ሰዎች እንዲያዳምጡት አድርጎ
‹ከተስማማነው ውጭ የቅቤውን መጠን ለምን ቀነስከው?› ሲል ጠየቀው፡፡

ገበሬውም ‹እኔ ፈጽሞ አልቀነስኩትም› ሲል በአግራሞት መለሰ፡፡ ነጋዴውም ቅቤውን በሚዛን ለክቶ አሳየው፡፡ 150 ግራም ነው፡፡ ገበሬውም አዘነ፡፡ ‹እኔ ቤት ውስጥ የ300 ግራም
መለኪያ የለኝም፡፡ አንተ ጠዋት ዳቦውን ስትልክልኝ በእጅ ሚዛኑ አንደኛው ሰሐን ላይ አደርገዋለሁ፤
ከዚያም ቅቤውን በሌላኛው ሚዛን አስቀምጠዋለሁ፡፡ ልክ ከዳቦው ጋር እኩል ሲመዝኑ በዕቃ አዘጋጅቼ
እልክልሃለሁ› አለው፡፡ ወዲያውም ጠዋት የላከለትን ዳቦ አውጥቶ ሚዛኑ ላይ አስቀመጠው፡፡ ዳቦው 150 ግራም ነበር የሚመዝነው፡፡ ነጋዴው አፈረ፡፡

‹የምታገኘው ለሌላው ባደረግከው ልክ ነው፡፡ 150 ሰጥተህ 300 ልታገኝ አትችልም፤ እባብ ሰጥተህ
ርግብ፣ ድንጋይ ሰጥተህ ዳቦ፣ እሬት ሰጥተህ ማር ልታገኝ አትችልም፤ አንተ ብቻ ብልጥ ልትሆን አትችልም፤ ማሾውን አጥፍተህ ብርሃን ልታገኝ
አትችልም፤ ሌላው ገድለህ አንተ በሰላም ልትኖር አትችልም› አለው ገበሬው፡፡

ማንኛውም ድርጊት ተመሳሳይና ተመጣጣኝ የሆነ ምላሽ አለው፡፡ አንተ እዚህ ለብቻህ ቤትህ ውስጥ
ሆነህ ክፉ ስታደርግ ሌላውም በቤቱ ብቻውን ሆኖ ክፉውን ይመልስሃል፡፡ ‹እዛም ቤት እሳት አለ›እንዳሉት ነው አለቃ ገብረ ሐና፡፡
@shegainfom
8.0K views04:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-02 22:05:50 “ነገ ለራሱ ይጨነቃልና ለነገ አትጨነቁ፤ ለቀኑ ክፋቱ ይበቃዋል።” ማቴዎስ 6፥34

ብዙን ጊዜ በሕይወታችን ጤናችንን ፣ሰላማችንን ......ከሚነሱን ፣ከሚወስዱብን ነገሮች ትልቁን ድርሻ የሚወስደው አንዱ ፋይዳ የሌለው ጭንቀት ነው ።

በሕይወታችን አለኝ የምንለው ነገር ሲሰበር አብረን አንሰበር ፣ሲወድቅ አብረን አንውደቅ ።

አንዳንዳንዶቻችን በሆነውም ባለሆነውም ገና ለገና ይሆናል ባልነው ነገር አብዝተን እንጨነቃለን ።

በሕይወታችን ስለሁሉም ነገር ማሰብ ተገቢ ሆኖ ሳለ ግን ውጥረት ውስጥ መግባት ግን ሞኝነት ነው ።ምክኒያቱም መፅሐፍ “ከእናንተ ተጨንቆ በቁመቱ ላይ አንድ ክንድ መጨመር የሚችል ማን ነው?” ማቴዎስ 6፥27 ይለንና አቅማችንን ሲነግረን እንዲህ ይላል

“እንግዲህ ትንሹን ነገር ስንኳ የማትችሉ ከሆናችሁ፥
ስለ ምን በሌላ ትጨነቃላችሁ?” ሉቃስ 12፥26
በእውነት እኛ ብርቱ መሆን አቅቶን እንጂ አምና፣ካቻምና ፣ድሮ .......በምንለው በሕይወታችን ያለፈው ይብዛም ይነስ አስተምሮን፣መክሮን አለፏል።

እኛ ትዕግስታችን ይብዛ እንጂ ያስጨነቀን ሲጨነቅ ስንፈልገው የነበረ ሲፈልገን ስንመኘው የነበረ እጃችን ላይ ገብቶ .......ምን አለፋቹህ ታሪክ ሆኖ ይቀራል ወሳኙ ትዕግስት ነው ።
ክርስቶስ ከጭንቀት ዓለም ይገላግለን።
@Shegainfom
ፍቅር: ሰላም: ለምድራችን
6.7K views19:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-01 18:12:10
"ልጄን ፍቅር ሰጥቼ ማሳደግ እንድችል #አድኑኝ "

#አርክቴክት_ሳምራዊት
"ያለኝን ሁሉ አሟጥቼ አሁን ከአቅሜ በላይ ሆነብኝ

#እናት
ይህች ቆንጅዬ #ሳምራዊት_ደስታ ትባላለች!ወለጋ ዩንቨርስቲ በአርክቴክቸር ኢንጅነሪንግ ተመርቃለች!!

በቅርቡም ትዳር ይዛ የአንድ ልጅ እናት ሆናለች!!
አራስ ሆና በስራ ምክንያት አልጋ ላይ ብዙም ያልቆየችው ሳምሪ ድንገት ወገቧን ማመም ሲጀምራት የምትኖርበት አዳማ ህክምና ስታደርግ ኢንፌክሽን ነው ብለው ማስታገሻ ሰጧት!!

ለጊዜው ቢያስታግስላትም ህመሙ እየከፋባት አላስተኛና አላስቀምጥ ሲላት ለተሻለ ህክምና ወደ አዲስ አበባ መጣች!!

ሀሌሉያ ሆስፒታል"ህመምሽ የማህፀንበር ካንሰር ነው"ብለው ከባዱን መርዶ ነገሯት!ታማ ሆስፒታል ሄዳ የማታውቀው ሳምራዊትና እናቷ ያልጠበቁት ሆኖ ተደናግጠው ጥቁር አንበሳ እንደገና ስትመረመር "አዎ ካንሰር አለብሽ" ብለው አረጋገጡላት!!

ሁለት ጊዜም ቀዶጥገና አድርጋ በሀገር ውስጥ ህክምና
አልተሳካም!የህክምና ቦርዱም "ከአቅማችን በላይ ሆኗልና ውጪ ሄዳ መታከም አለባት"ብለው ወስነዋል

እናት ስለልጃቸው ያላቸውን ጨርሰዋል!!ህንድ ሄዳ ለማሳከም ምንም አቅም የላቸውም!! እባካችሁ
#ልጄን_አድኑልኝ " እያሉ እየተማፀኑ ነው!!የቻልነውን

እናግዛቸው ምንም ማድረግ ባንችል #እየፀለይን
#SHARE_ሼር በማድረግ ለደጋጎች እናዳርስላቸው
#አካውንት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
1000180776145_ገነት ጀምበሩ(እናት)
#ስልክ:-
0913379447-ገነት(እናት)
7.1K views15:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-28 16:37:46 #የጋብቻ_ሕግጋት_ ~~~ #ሼርርርርርርርር

1.ከተጋቡ በኅላ አንድ አካል ናቸው። (ማቴ 19:4-6
2.መፋታት ክልክል ነው። (ሚል2:14)
3.አንድ ወንድ ለአንድ ሴት ። 1ኛ ቆሮ 7:2
4.የሚገባቸውን ሁሉ ማድረግ።
5.ባልም ለሚስትም በራሳቸሁ ሥልጣን የላቸሁም። 1ኛ ቆሮ 7:4
6.ኃላፊነትን መወጣት። ኤፌ5:20-23 ቆላ 3:18
7.ለጾምና ለጸሎት ካልሆነ አለመለያየት 1ኛ ቆሮ7:5
8.ሥጋዊ ጌጥ አለማብዛት ።1ኛ ጴጥ 3:1-4
9.ድንገተኛ ግጭት ቢከሰት ወዲያው መታረቅ።1ኛ ቆሮ 7:10-11
10.በሞት ካልሆነ አለመለያየት።1ኛ ቆሮ 7:39 እናሮሜ 7:2-3
ከሥጋዊ መንፈሳዊ የጋብቻ ዘመድ አለማግባት።ዘሌ 18:6-20 ዘሌ20:16-21፣ማር 6:17።

: #አታግባ
የህይወት ምንነት ሳታውቅ አታግባ
የትዳርን ምንነት ሳታውቅ አታግባ
የትዳር አጋርህን ሀቅ (መብት) ሳታዘጋጅ አታግባ
በችግር ሰዓት ህይወትን አብረህ ልትገፋ ምትችል ሴት ሳታገኝ አታግባ
ኃላፊነትህን እንዴት መወጣት እንዳለብህ ሳታቅ አታግባ
ለልጆችህ ተምሳሌት መሆን ሳትችል አታግባ

#ትዳር
ትዳር ማለት 1ወንድ አንድ ሴት
ትዳር ማለት 1እምነት አንድ እውነት
ትዳር ማለት 1እሳት አንድ ውሃ
ትዳር ማለት 1 ሙሉ አንድ ጎዶሎ
ትዳር ማለት 1መጥፎ አንድ ጥሩ
ትዳር ማለት 1 ጉልቻ አንድ ድስጥ
ትዳር ማለት 1ወንዝ አንድ ውሃ የሚቀዳ ቢሆንም
ካልተንከባክበውና ካልተቻቻልንበት ሊደርቅ የሚችል #ወራጅ

#ወንዝ ነው።
ደግ ሴትን ባሏ ያመሰግናታል፤
የሕይወት ዘመኑም እጥፍ ይሆናል።
ቅን ሴት ባሏን ደስ ታሰኘዋለች፤
ዘመኑንም በሰላም ይጨረሳል።
የደግ ሴት ዕድሏ ያማረ ነው፤
እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰውንም ወደ
ዕድሉ ታደረሰዋለች
መፀሐፈ ሲራክ 26:1~3

በፍቅር ያማረ ትዳር ሠላም ያለው እውነተኛ ፍቅር ፈጣሪ ይስጠን! አሜን
@shegainfom
ፍቅር : ሰላም :ለምድራችን !
8.7K views13:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-16 21:46:41
ዛሬ ከተመረቁት ውስጥ የአንዱ ተመራቂ መልዕክት

አባባ ዛሬ ከተለየኸን ዓመት ሊሞላ ሦስት ቀናት ቀሩት፤ በጣም ቆጨኝ ይህን ጉትጎታህን፣ምኞትህን፣ልፋትህን ባለማይትህ፤ ሆኖም ነፍስህ ከገነት ሆና እንደምትደሰት ቅንጣት አልጠራጠርም።

ነፍስህ ቅዱሳኖቹ ባሉበት የአምላክህን ፊት እየተመለከተች ሐሴት ታድርግ! ይህም ውጤት ለአንተ ነው የሚገባው።

ደግሞ የለበስኩትን ሸሚዝ አስታወስከው? ከመለየትህ ከሣምንት በፊት የሰጠኸኝ? እንደውም አልፈልገውም ብዬህ የነበረው የመጨረሻው ስጦታህ እኮ ነው።

በእጆችህ ስትነካካው ስለነበር በክብር አስቀምጬው ዛሬ ነው ያደረኩት እንዴት ደስ እንዳለኝ፣ ያቀፍከኝ ያህል ነው የተሰማኝ!እወድሃለሁ!ክብር ሁሉ ለቅድስት ሥላሴ እና ለድንግል ማርያም ይሁን !
የአባቴ አምላክ የተመሰገነ ይሁን!!!!!
@shegainfom
2.9K viewsedited  18:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-16 19:24:18
ዛሬ በአዲስ አበባ ዮኒቨርስቲ የተመረቀው ልጅ እናቱ እንዴት እንዳስተማረችው ስለሚያውቅ ይህን አድርጓል::
@shegainfom
3.3K views16:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-16 15:35:53
3.5K views12:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-11 07:11:03 በ 2 ነገሮች ቀንህን ጀምር!

ሁሌም ቅድሚያ የምትሰጣቸው ነገሮች ህይወትህ ላይ ወሳኝ ናቸው። መጀመሪያ ለፈጣሪህ ቅድሚያ ስጥ ምክንያቱም እስካሁን እየተነፈስክ ነው፤ ስለዚህ ከእንቅልፍ እንደነቃህ አመስግነህ ፀሎትህን አድርስ።

ቀጥሎ ለራስህ ቅድሚያ ስጥ ምክንያቱም አንተ ስትኖር ነው ለምትወዳቸው ሁሉ የምትደርሰው፤ ስለዚህ ስለ ህልምህ በማሰብ፣ ስፖርት በመስራት፣ የሚጠቅምህን በማንበብ ቀንህን ጀምር።

በእነዚህ ሁለት ነገሮች ቀንህን ስትጀምር በዚህ አለም የሚገጥምህን የትኛውንም ችግር ታልፋለህ፤ ለምታውቃቸው ብቻ ሳይሆን ለማታውቃቸው ሁሉ ትተርፋለህ። ወዳጄ ቅድሚያ የምትሰጠውን እወቅ!

የተባረከ ሰኞ ተመኘንላችሁ
@shegainfom
ፍቅር : ሰላም : ለምድራች!
6.5K views04:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-10 20:42:26 አንተ አልችልም ስትል ~ እግዚአብሔር በሰው ዘንድ የማይቻል በኔ ዘንድ ይቻላል ይልሃል።

“እርሱ ግን፦ በሰው ዘንድ የማይቻል በእግዚአብሔር ዘንድ ይቻላል አለ።” ሉቃስ 18፥27

አንተ ደክሞኛል ስትል ~እግዚአብሔር አሳርፍሃለሁ ይልሃል።

" እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፥ ወደ እኔ ኑ፥ እኔም አሳርፋችኋለሁ።

ቀንበሬን በላያችሁ ተሸከሙ ከእኔም ተማሩ፥ እኔ የዋህ በልቤም ትሑት ነኝና፥ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ፤ቀንበሬ ልዝብ ሸክሜም ቀሊል ነውና።"
ማቴ. 11 ፡28-30

አንተ ማንም አይወደኝም ስትል ~ እግዚአብሔር እወድሃለሁ ይልሃል።
“በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም

ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና።”
ዮሐንስ 3፥16

አንተ አቅቶኛል መቀጠል አልችልም ስትል ~እግዚአብሔር ጸጋዬ ይበቃሃል ይልሃል።
“እርሱም፦ ጸጋዬ ይበቃሃል፥ ኃይሌ በድካም ይፈጸማልና አለኝ።

እንግዲህ የክርስቶስ ኃይል ያድርብኝ ዘንድ በብዙ ደስታ በድካሜ ልመካ እወዳለሁ።”
2ኛ ቆሮ 12፥9

አንተ መንገድ መለየት ከብዶኛል ስትል ~ እግዚአብሔር አስተምርሃለሁ በምትሄድበትም መንገድ እመራሃለሁ ይልሃል።”

"አስተምርሃለሁ በምትሄድበትም መንገድ እመራሃለሁ፤ ዓይኖቼን በአንተ ላይ አጠናለሁ።”
መዝሙር 32፥8

አንተ ማድረግ አልችልም ስትል ~ እግዚአብሔር ኃይልን በምሰጥህ በእኔ ሁሉን ትችላለህ ይልሃል ።

"ኃይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ። "
ፊልጵስዩስ 4፥13

አንተ ብቃት የለኝም ስትል ~ እግዚአብሔር ብቃት አለህ ይልሃል።

“በተነ፥ ለምስኪኖች ሰጠ፥ ጽድቁ ለዘላለም ይኖራል ተብሎ እንደ ተጻፈ፥ እግዚአብሔር፥ ሁልጊዜ በነገር ሁሉ ብቃትን ሁሉ አግኝታችሁ ለበጎ ሥራ ሁሉ ትበዙ ዘንድ፥ ጸጋን ሁሉ ሊያበዛላችሁ ይችላል።”
2ኛ ቆሮ 9፥8-9

አንተ ይህ ለኔ አይገባኝም ነበር፣ ለምን እኔ ላይ ሆነ ስትል ~ እግዚአብሔር ነገር ሁሉ ለበጎ ነው ይልሃል።

“እግዚአብሔርንም ለሚወዱት እንደ አሳቡም ለተጠሩት ነገር ሁሉ ለበጎ እንዲደረግ እናውቃለን።”
ሮሜ 8፥28

አንተ ራሴን ይቅር ማለት አልችልም ስትል ~ እግዚአብሔር ይቅር እልሃለሁ ይልሃል።

“በኃጢአታችን ብንናዘዝ ኃጢአታችንን ይቅር ሊለን ከዓመፃም ሁሉ ሊያነጻን የታመነና ጻድቅ ነው።”
1ኛ ዮሐንስ 1፥9

አንተ ኑሮ ከብዶኛል ስትል ~እግዚአብሔር የሚያስፈልግህን ሁሉ እምላልሃለሁ ይልሃል ።

“አምላኬም እንደ ባለ ጠግነቱ መጠን በክብር በክርስቶስ ኢየሱስ የሚያስፈልጋችሁን ሁሉ ይሞላባችኋል።”
ፊልጵስዩስ 4፥19

አንተ ፈርቻለሁ ስትል ~ እግዚአብሔር የፍርሃት መንፈስ አልሰጠሁህም ይልሃል።
“እግዚአብሔር የኃይልና የፍቅር ራስንም የመግዛት መንፈስ እንጂ የፍርሃት መንፈስ አልሰጠንምና።”
2ኛ ጢሞቴዎስ 1፥7

አንተ እጨነቃለሁ ስትል ~ እግዚአብሔር የሚያስጨንቅህን ሁሉ በኔ ላይ ጣል ይልሃል።

“እርሱ ስለ እናንተ ያስባልና የሚያስጨንቃችሁን ሁሉ በእርሱ ላይ ጣሉት።” 1ኛ ጴጥሮስ 5፥7

አንተ ብልሃት የለኝም ስትል ~እግዚአብሔር ጥበብን እሰጥሃለሁ ይልሃል።

“ነገር ግን፦ የሚመካ በእግዚአብሔር ይመካ ተብሎ እንደ ተጻፈው ይሆን ዘንድ፥ ከእግዚአብሔር ዘንድ ጥበብና ጽድቅ ቅድስናም ቤዛነትም በተደረገልን በክርስቶስ ኢየሱስ የሆናችሁ ከእርሱ ነው።”1ኛ ቆሮንቶስ 1፥30-31
አንተ ማንም የለኝም ብቻዬን ነኝ ስትል ~ እግዚአብሔር አለቅህም ከቶም አልተውህም ይልሃል።

“ አልለቅህም ከቶም አልተውህም።" ዕብራውያን 13፥5
@shegainfom
5.9K views17:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-09 17:50:17 ኢትዮጵያዊ(ግዕዝ) ስሞች ለልጆት ማውጣት ይፈልጋሉ ይምረጡ እስከ ትርጉሙ

1ማዕዶት፦መሻገሪያ ማለት ነው
2 ኖላዊ፦ጠባቂ ማለት ነው።
3 ማኅቶት፦ብርሃን ማለት ነው
4 ኂሩት፦በጎነት ማለት ነው።
5 ሜላት፦የሐር ግምጃ ማለት ነው።
6 ኅሩይ፦ምርጥ የተመረጠ ማለት ነው።ለሴት ኅሪት
7 ሮዛ፦ጽጌረዳ ማለት ነው።
8 ቀጸላ፦አክሊል ማለት ነው።
9 አስካል፦ፍሬ ማለት ነው።
10 በጽሐ፦ደረሰ ማለት ነው።
11 መሐሪ፦ይቅር ባይ ማለት ነው።
12 መንክር፦ልዩ ማለት ነው።
13 ሥሙር፦የተወደደ ማለት ነው።
14 ሐመልማል፦ለምለም ማለት ነው።
15 ነጸረ፦አየ ተመለከተ ማለት ነው።
16 ቅድስት፦ልዩ ምስጉን ማለት ነው።ቅዱስ ለወንድ ነው።
17 ይኄይስ፦ይሻላል ማለት ነው።
18 ጥዑም፦ጣፋጭ ማለት ነው
19 ግሩም፦የተፈራ ማለት ነው።
20 ተቅዋም፦መቅረዝ ማለት ነው።
21 ጸገየ፦አበበ ማለት ነው
22 ደምፀ፦ተሰማ ማለት ነው።
23 ጎሐጽባሕ፦የንጋት ኮከብ ማለት ነው።
24 ሐዋዝ፦መልካሙ ማለት ነው።
25 ሠናይ፦መልካሙ ማለት ነው።ሰናይት ለሴት ነው።
26 ፈታሒ፦ፈራጁ ማለት ነው።
27 መዓዛ፦ጥሩ ሽታ ማለት ነው።
28 መራሒ፦መሪ ማለት ነው።
29 ነጋሢ/ንጉሥ፦የነገሠ ማለት ነው።
30 ስቡሕ፦የተመሰገነ ማለት ነው።
31 ስብሐት፦ምስጋና ማለት ነው።
32 ብሩህ፦የበራ ማለት ነው።
33 ብርሃን፦ያው በቁሙ ብርሃን ማለት ነው።
34 ትጉህ፦የተጋ ማለት ነው።
35 አምኃ፦እጅ መንሻ ማለት ነው።
36 ልዑል፦ከፍ ያለው ማለት ነው።
37 ከሀሊ፦የሚችል ማለት ነው።
38 ዳግም፦ዳግመኛ ማለት ነው።
39 ማዕረር፦አዝመራ ማለት ነው።
40 ክቡር፦የተከበረ ማለት ነው።
41 አዕምሮ፦እውቀት ማለት ነው።
42 ደብሩ፦ተራራው ማለት ነው።
43 ምሥራቅ፦የፀሐይ መውጫ ማለት ነው።
44 ይባቤ፦እልልታ ማለት ነው።
45 ጥበቡ፦ብልሀተኛው ማለት ነው።
46 ሃይማኖት፦ሃይማኖት ማለት ነው።
47 ትሕትና፦ትሕትና ማለት ነው።
48 ተከሥተ፦ተገለጠ ማለት ነው።
49 በየነ፦ፈረደ ማለት ነው።
50 መኮንን፦ገዢ ማለት ነው።
51 ሐዳስ፦አዲሱ ማለት ነው።
52 ትንሣኤ፦መነሳት ማለት ነው።
53 ሢራክ፦ብልሀተኛ ማለት ነው።
54 ቡሩክ፦ምስጉን የተመሰገነ ማለት ነው።
55 ህላዌ፦መኖር ማለት ነው።
56 ማኅደር፦መኖሪያ ማለት ነው።
57 ሕይወት፦መኖር ማለት ነው።
58 ቤዛ፦መድኃኒት ማለት ነው። ቤዛዊት ለሴት ነው።
59 ኄራን፦ደጋጎች ማለት ነው።
60 መርዓዊ፦ሙሽራ ማለት ነው። መርዓዊት ለሴት ነው።
61 ተስፋ፦ተስፋ ማለት ነው።
62 ዜናዊ፦ነጋሪ ማለት ነው።
63 ጸዐዳ፦ነጭ ማለት ነው።
64 ጸጋ፦ስጦታ ማለት ነው።
65 ብሥራት፦የምሥራች ማለት ነው።
66 ኅሊና፦ማሰቢያ፥ሀሳብ እውቀት ማለት ነው።
67 ማህሌት፦ምስጋና ማለት ነው።
68 ሐሴት፦ደስታ ማለት ነው።
69 ፍሥሓ፦ደስታ ማለት ነው።
70 ትርሲት፦ሽልማት ማለት ነው። በተጨማሪ ስርጉት ማለት የተሸለመች ያጌጠች ማለት ነው።
71 ምዕራፍ፦ማረፊያ ማለት ነው።
72 መቅደስ፦ማመስገኛ፥ መመስገኛ ማለት ነው።
73 ዋካ፦ብርሃን ማለት ነው።
74 ረድኤት፦ እርዳታ ማለት ነው።
75 ጽጌ፦አበባ ማለት ነው።
76 ሠረገላ፦መኪና ማለት ነው።
77 አማን፦እውነት ማለት ነው።
78 አሜን፦ይሁንልኝ ይደረግልኝ ማለት ነው።
79 ተንከተም፦ድልድይ ማለት ነው። ሰዋስው መሰላል ነው።
80 ጸዳሉ፦ብርሃኑ ማለት ነው።
@shegainfom
ፍቅር : ሰላም : ለምድራችን !
5.3K views14:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ