Get Mystery Box with random crypto!

ዛሬ ከተመረቁት ውስጥ የአንዱ ተመራቂ መልዕክት አባባ ዛሬ ከተለየኸን ዓመት ሊሞላ ሦስት ቀናት ቀ | Shega info

ዛሬ ከተመረቁት ውስጥ የአንዱ ተመራቂ መልዕክት

አባባ ዛሬ ከተለየኸን ዓመት ሊሞላ ሦስት ቀናት ቀሩት፤ በጣም ቆጨኝ ይህን ጉትጎታህን፣ምኞትህን፣ልፋትህን ባለማይትህ፤ ሆኖም ነፍስህ ከገነት ሆና እንደምትደሰት ቅንጣት አልጠራጠርም።

ነፍስህ ቅዱሳኖቹ ባሉበት የአምላክህን ፊት እየተመለከተች ሐሴት ታድርግ! ይህም ውጤት ለአንተ ነው የሚገባው።

ደግሞ የለበስኩትን ሸሚዝ አስታወስከው? ከመለየትህ ከሣምንት በፊት የሰጠኸኝ? እንደውም አልፈልገውም ብዬህ የነበረው የመጨረሻው ስጦታህ እኮ ነው።

በእጆችህ ስትነካካው ስለነበር በክብር አስቀምጬው ዛሬ ነው ያደረኩት እንዴት ደስ እንዳለኝ፣ ያቀፍከኝ ያህል ነው የተሰማኝ!እወድሃለሁ!ክብር ሁሉ ለቅድስት ሥላሴ እና ለድንግል ማርያም ይሁን !
የአባቴ አምላክ የተመሰገነ ይሁን!!!!!
@shegainfom