Get Mystery Box with random crypto!

አንተ አልችልም ስትል ~ እግዚአብሔር በሰው ዘንድ የማይቻል በኔ ዘንድ ይቻላል ይልሃል። “እርሱ | Shega info

አንተ አልችልም ስትል ~ እግዚአብሔር በሰው ዘንድ የማይቻል በኔ ዘንድ ይቻላል ይልሃል።

“እርሱ ግን፦ በሰው ዘንድ የማይቻል በእግዚአብሔር ዘንድ ይቻላል አለ።” ሉቃስ 18፥27

አንተ ደክሞኛል ስትል ~እግዚአብሔር አሳርፍሃለሁ ይልሃል።

" እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፥ ወደ እኔ ኑ፥ እኔም አሳርፋችኋለሁ።

ቀንበሬን በላያችሁ ተሸከሙ ከእኔም ተማሩ፥ እኔ የዋህ በልቤም ትሑት ነኝና፥ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ፤ቀንበሬ ልዝብ ሸክሜም ቀሊል ነውና።"
ማቴ. 11 ፡28-30

አንተ ማንም አይወደኝም ስትል ~ እግዚአብሔር እወድሃለሁ ይልሃል።
“በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም

ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና።”
ዮሐንስ 3፥16

አንተ አቅቶኛል መቀጠል አልችልም ስትል ~እግዚአብሔር ጸጋዬ ይበቃሃል ይልሃል።
“እርሱም፦ ጸጋዬ ይበቃሃል፥ ኃይሌ በድካም ይፈጸማልና አለኝ።

እንግዲህ የክርስቶስ ኃይል ያድርብኝ ዘንድ በብዙ ደስታ በድካሜ ልመካ እወዳለሁ።”
2ኛ ቆሮ 12፥9

አንተ መንገድ መለየት ከብዶኛል ስትል ~ እግዚአብሔር አስተምርሃለሁ በምትሄድበትም መንገድ እመራሃለሁ ይልሃል።”

"አስተምርሃለሁ በምትሄድበትም መንገድ እመራሃለሁ፤ ዓይኖቼን በአንተ ላይ አጠናለሁ።”
መዝሙር 32፥8

አንተ ማድረግ አልችልም ስትል ~ እግዚአብሔር ኃይልን በምሰጥህ በእኔ ሁሉን ትችላለህ ይልሃል ።

"ኃይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ። "
ፊልጵስዩስ 4፥13

አንተ ብቃት የለኝም ስትል ~ እግዚአብሔር ብቃት አለህ ይልሃል።

“በተነ፥ ለምስኪኖች ሰጠ፥ ጽድቁ ለዘላለም ይኖራል ተብሎ እንደ ተጻፈ፥ እግዚአብሔር፥ ሁልጊዜ በነገር ሁሉ ብቃትን ሁሉ አግኝታችሁ ለበጎ ሥራ ሁሉ ትበዙ ዘንድ፥ ጸጋን ሁሉ ሊያበዛላችሁ ይችላል።”
2ኛ ቆሮ 9፥8-9

አንተ ይህ ለኔ አይገባኝም ነበር፣ ለምን እኔ ላይ ሆነ ስትል ~ እግዚአብሔር ነገር ሁሉ ለበጎ ነው ይልሃል።

“እግዚአብሔርንም ለሚወዱት እንደ አሳቡም ለተጠሩት ነገር ሁሉ ለበጎ እንዲደረግ እናውቃለን።”
ሮሜ 8፥28

አንተ ራሴን ይቅር ማለት አልችልም ስትል ~ እግዚአብሔር ይቅር እልሃለሁ ይልሃል።

“በኃጢአታችን ብንናዘዝ ኃጢአታችንን ይቅር ሊለን ከዓመፃም ሁሉ ሊያነጻን የታመነና ጻድቅ ነው።”
1ኛ ዮሐንስ 1፥9

አንተ ኑሮ ከብዶኛል ስትል ~እግዚአብሔር የሚያስፈልግህን ሁሉ እምላልሃለሁ ይልሃል ።

“አምላኬም እንደ ባለ ጠግነቱ መጠን በክብር በክርስቶስ ኢየሱስ የሚያስፈልጋችሁን ሁሉ ይሞላባችኋል።”
ፊልጵስዩስ 4፥19

አንተ ፈርቻለሁ ስትል ~ እግዚአብሔር የፍርሃት መንፈስ አልሰጠሁህም ይልሃል።
“እግዚአብሔር የኃይልና የፍቅር ራስንም የመግዛት መንፈስ እንጂ የፍርሃት መንፈስ አልሰጠንምና።”
2ኛ ጢሞቴዎስ 1፥7

አንተ እጨነቃለሁ ስትል ~ እግዚአብሔር የሚያስጨንቅህን ሁሉ በኔ ላይ ጣል ይልሃል።

“እርሱ ስለ እናንተ ያስባልና የሚያስጨንቃችሁን ሁሉ በእርሱ ላይ ጣሉት።” 1ኛ ጴጥሮስ 5፥7

አንተ ብልሃት የለኝም ስትል ~እግዚአብሔር ጥበብን እሰጥሃለሁ ይልሃል።

“ነገር ግን፦ የሚመካ በእግዚአብሔር ይመካ ተብሎ እንደ ተጻፈው ይሆን ዘንድ፥ ከእግዚአብሔር ዘንድ ጥበብና ጽድቅ ቅድስናም ቤዛነትም በተደረገልን በክርስቶስ ኢየሱስ የሆናችሁ ከእርሱ ነው።”1ኛ ቆሮንቶስ 1፥30-31
አንተ ማንም የለኝም ብቻዬን ነኝ ስትል ~ እግዚአብሔር አለቅህም ከቶም አልተውህም ይልሃል።

“ አልለቅህም ከቶም አልተውህም።" ዕብራውያን 13፥5
@shegainfom