Get Mystery Box with random crypto!

“ነገ ለራሱ ይጨነቃልና ለነገ አትጨነቁ፤ ለቀኑ ክፋቱ ይበቃዋል።” ማቴዎስ 6፥34 ብዙን ጊዜ በሕ | Shega info

“ነገ ለራሱ ይጨነቃልና ለነገ አትጨነቁ፤ ለቀኑ ክፋቱ ይበቃዋል።” ማቴዎስ 6፥34

ብዙን ጊዜ በሕይወታችን ጤናችንን ፣ሰላማችንን ......ከሚነሱን ፣ከሚወስዱብን ነገሮች ትልቁን ድርሻ የሚወስደው አንዱ ፋይዳ የሌለው ጭንቀት ነው ።

በሕይወታችን አለኝ የምንለው ነገር ሲሰበር አብረን አንሰበር ፣ሲወድቅ አብረን አንውደቅ ።

አንዳንዳንዶቻችን በሆነውም ባለሆነውም ገና ለገና ይሆናል ባልነው ነገር አብዝተን እንጨነቃለን ።

በሕይወታችን ስለሁሉም ነገር ማሰብ ተገቢ ሆኖ ሳለ ግን ውጥረት ውስጥ መግባት ግን ሞኝነት ነው ።ምክኒያቱም መፅሐፍ “ከእናንተ ተጨንቆ በቁመቱ ላይ አንድ ክንድ መጨመር የሚችል ማን ነው?” ማቴዎስ 6፥27 ይለንና አቅማችንን ሲነግረን እንዲህ ይላል

“እንግዲህ ትንሹን ነገር ስንኳ የማትችሉ ከሆናችሁ፥
ስለ ምን በሌላ ትጨነቃላችሁ?” ሉቃስ 12፥26
በእውነት እኛ ብርቱ መሆን አቅቶን እንጂ አምና፣ካቻምና ፣ድሮ .......በምንለው በሕይወታችን ያለፈው ይብዛም ይነስ አስተምሮን፣መክሮን አለፏል።

እኛ ትዕግስታችን ይብዛ እንጂ ያስጨነቀን ሲጨነቅ ስንፈልገው የነበረ ሲፈልገን ስንመኘው የነበረ እጃችን ላይ ገብቶ .......ምን አለፋቹህ ታሪክ ሆኖ ይቀራል ወሳኙ ትዕግስት ነው ።
ክርስቶስ ከጭንቀት ዓለም ይገላግለን።
@Shegainfom
ፍቅር: ሰላም: ለምድራችን