Get Mystery Box with random crypto!

#ውጤታማ_የሚያደርጉህ_3ቱ_ምላሾች የተፈጠረውን ነገር መቀየር ሲያቅትህ የምትሰጠውን ምላሽ እንዴት | Shega info

#ውጤታማ_የሚያደርጉህ_3ቱ_ምላሾች

የተፈጠረውን ነገር መቀየር ሲያቅትህ የምትሰጠውን ምላሽ እንዴት አድርገህ መቀየር ትችላለህ?

#1_ባለህበት_የምትችለውን_አድርግ

ባለህበት ቦታ ላይ ለመሆን የምትችለውን ሁሉ ነገር አድርግ፡፡ ምክንያቱም ብዙውን ጊዜ የደስታ እና የሠላም ምስጢሩ አሁን ያለውን ሁኔታ እንዲህ ነው ሊሆን የሚገባው ብሎ ከማሰብ ፈንታ እንደሆነ ይሁን ብሎ በመተው ከሁኔታው የቻሉትን ያህል መጠቀም ነው፡፡

#2_ፈጽሞ_አትጸጸት

ለተሳሳቱ ሰዎች ባሳየኻቸው ደግነት እና ክብር ሳቢያ ፈጽሞ እንዳትጸጸት፡፡ የአንተ ባህሪ ስለ አንተ ሁሉንም ነገር ሲናገር፣ የእነርሱ ባህሪ ስለ እነርሱ ከበቂ በላይ ይናገራል፡፡ በግርማ . . . ቀና ብለህ አንተ ወደፊት ቀጥል. . .

#3_መልቀቅን_ተማር፡፡

የተጋበዝከው ክርክር ላይ ሁሉ መታደም አይገባህም፡፡ ለጊዜህ፣ ለእውነተኛ ግንኙነቶችህ እና ከሀሉም በላይ ለአእምሮህ ሰላም ዋጋ የምትሰጥበትን ቦታ ለራስህ ስጥ፡፡ ምክንያቱም ሌላው ሌላው ነገር ውሎ አድሮ ብዙም ትርጉም የለውም፡፡

እውነቱ ይነገር ካልክ ያለፈ አጸፋዊ ምላሽ ያለመስጠት ችሎታ፣ ወይም ነገሮችን በግል እንደተቃጣ ጥቃት አድርጎ ባለመውሰድ፣ አእምሮን ሁሌም ንጹህ በማድረግ እና ልብን በሰላም ላይ በማሳረፍ ሊቆጣጠሯቸው በማይችሏቸው ሁኔታዎች ውስጥ ሳይቀር ጽኑ አቋምን እንደያዙ ለመዝለቅ ይረዳል፡፡

#የስኬት_አቡጊዳ መጽሐፍ