Get Mystery Box with random crypto!

Brand watches and bags shop 2

የቴሌግራም ቻናል አርማ newsetv — Brand watches and bags shop 2 B
የቴሌግራም ቻናል አርማ newsetv — Brand watches and bags shop 2
የሰርጥ አድራሻ: @newsetv
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ሀገር: ኢትዮጵያ
ተመዝጋቢዎች: 19.00K
የሰርጥ መግለጫ

Europe standard watchs and bags with resonable price
We bring items directly from the place. Most not found in local market
Enjoy the fancy items
Shop adress: 22 Near golagol tower 100 meters on bole road hanan k plaza.
0993014846
@brand_suk text us

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 31

2020-11-21 18:12:57 የትግራይ ህዝብ የህወሃትን የጥፋት ቡድን እንደማይደግፍ በተግባር እያሳየ ነው...ብርጋዴር ጀኔራል ብርሄ ገብረመድህን

የትግራይ ህዝብ የህወሃትን የጥፋት ቡድን አለመደገፉን በተጨባጭ እያሰየ መሆኑን በአገር መከላከያ የሎጂስትክስ ዋና መምሪያ የሜንቴናንስ ሃላፊ ብርጋዴር ጀኔራል ብርሄ ገብረመድህን ተናገሩ።

የህወሃት ጽንፈኛ ቡድን በኢትዮጵያ የእርስ በርስ ግጭት ለመፍጠር አልሞ የነበረው የጥፋት መረብ እንደከሸፈበትም ነው የገለጹት።

ብርጋዴር ጄኔራል በርሄገብረመድህን ከአዜአ ጋር በነበራቸው ቆይታ እንዳሉት፤ የአገር መከላከያ ሰራዊት ለህዝብና ለአገር ደህንነት ሲል ራሱን አሳልፎ የሚሰጥ ሃይል መሆኑ ይታወቃል።

የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ከአገሩም አልፎ የአፍሪካ የሰላም ዋስትና ለመሆኑ ብዙዎች ምስክርነታቸውን እንደሚሰጡም ገልጸዋል።

የህወሃት ቡድን ጥቃት የፈፀመበት የሰሜን እዝ በተለይ የትግራይን ህዝብ ሰላም በመጠበቅና በተለያዩ ማህበራዊ አገልግሎቶች በመሳተፍ የህዝብ አለኝታነቱን ሲያሳይ ቆይቷል ብለዋል።

የኮሮናቫይረስ መከሰትን ተከትሎ ሰራዊቱ በክልሉ አቅመ ደካሞችን በመደገፍ፣ አዝመራ በመሰብሰብ፣ አንበጣ በመከላከልና ህፃናት እንዲማሩ በመደገፍ አለኝታነቱን ማሳየቱን ብርጋዴር ጄኔራል በርሄ ገልጸዋል።

የሰራዊቱ አባላት ከትግራይ ህዝብ ጋር በፈጠሩት ጠንካራ ቤተሰባዊ ትስስር ሳቢያ በጡረታ ሲገለሉ እንኳን ቤተሰባዊ ኑሯቸውን በክልሉ የሚያደርጉ በርካቶች እንደሆኑ ተናግረዋል።
የህወሃት ፅንፈኛ ሃይል ግን ይህንን ሁሉ የሰራዊቱን ውለታ በአንድ ምሽት "የክህደት ቋት ውስጥ ከቶታል" ብለዋል።

የጽንፈኛ ቡድኑ መሪዎች ልጆቻቸውን በተለያዩ አገራት አስቀምጠው የደሃውን የትግራይ ህዝብ ልጅ ለስቃይ እየዳረጉት መሆኑንም ነው የገለጹት።

በትግራይ ህዝብ ስም በመነገድ ለራሳቸው ጥቅም ብቻ ሲሰሩ መቆየታቸውን የገለጹት ብርጋዴር ጀኔራሉ፤የትግራይ ህዝብ ልማት እንጂ ጦርነት አይሻም ብለዋል።

የክልሉ ህዝብ ጽንፈኛ ቡድኑ መከላከያን እንዲወጉ ያስታጠቃቸውን መሳሪያ ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ማስረከባቸውም የቡድኑን እኩይ ተግባር እንደማይደግፉ ማሳያ ነው ብለዋል።

የትግራይ ህዝብ ጽንፈኛ ቡድኑን በመጋፈጥ ለአገር መከላከያ ሰራዊት ድጋፍ በማድረጉ የህግ ማስከበር እርምጃው በአጭር ጊዜ ውስጥ በርካታ ድሎች እየተመዘገቡበት መሆኑን ገልጸዋል።

ጽንፈኛ ቡድኑ ሰራዊቱን በማጥቃት የእርስ በርስ ግጭት ለመፍጠር እቅድ እንደነበረው ጠቅሰው፤ ኢትዮጵያውያን ለሀገር ሉዓላዊነት ያላቸው አቋም አንድ በመሆኑ ህልሙ ሳይሳካለት ቀርቷል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

እየተካሄደ ባለው ህግ የማስከበር እርምጃ ጽንፈኛው ቡድን በቅርቡ ለህግ እንደሚቀርብ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።

@newsetv
16.8K views15:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-11-21 15:19:40 የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ባለፉት ጥቂት ቀናት ያስመዘገበው ድል የሚደነቅ ነው - ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ

በሕግ ማስከበር ተልዕኮው የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ባለፉት ጥቂት ቀናት ያስመዘገበው ድል የሚደነቅ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አስታወቁ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፌስ ቡክ ገጻቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ ሠራዊቱ ትናንት ምሽት በአዲግራት ዙሪያ ያሉትን አካባቢዎች ከተቆጣጠረ በኋላ፣ ዛሬ ደግሞ አዲግራትን ከሕወሓት ኃይል ሙሉ በሙሉ ነፃ አውጥቷል ብለዋል።

የፌደራል መንግሥት በተቆጣጠራቸው ከተማዎችና አካባቢዎች የሚገኙ ዜጎች፣ በጸጥታ ኃይሎች ጥበቃ እየተደረገላቸው ወደ ዕለት ተዕለት እንቅስቃሴያቸው መመለስ ጀምረዋልም ነው ያሉት።

ከመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር በመሆን፣ ሰብአዊና ማኅበራዊ ፍላጎቶች የሚሟሉበትን መንገድ እንደሚመቻቸም አስታውቀዋል፡፡

የሰብአዊ ድጋፍ ክንውኖችን ለመከታተል በፌደራል መንግሥት የተዋቀረው ከፍተኛ ኮሚቴ፣ ተመጣጣኝ እና ወቅታዊ ድጋፍ ለማቅረብ የሚያስችል መረጃን እንዲያሰባስቡ ተጨባጭ ሁኔታውን የሚያጣሩ ልዑካንን ወደ ስፍራው መላኩንም ገልጸዋል፡፡

በተጨማሪም ይህ ኮሚቴ ባለፉት ቀናት መኖሪያቸውን ጥለው የተሰደዱት ዜጎችን ወደ ቀያቸው ለመመለስ እና ለማቋቋም ከባለ ድርሻ አካላት ጋር መሥራቱን ይቀጥላልም ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።

የፌደራል መንግሥት ለትግራይ ሕዝብ አጠቃላይ ደኅንነት እና ጤንነት ከፍተኛ ዋጋ የሚሰጥ ስለሆነ፣ በትግራይ ክልል መረጋጋት እንዲሰፍን እና ዜጎች ከጉዳት እና እጦት ነፃ እንዲሆኑ አስፈላጊውን ሁሉ እንደሚያደርግም ጠቅሰዋል፡፡

@newsetv
13.6K views12:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-11-19 19:24:13 የተለያዩ የንግድ ህግ ጥሰቶችን በፈጸሙ 1ሺህ 973 የንግድ ተቋማት ላይ እርምጃ መውሰዱን የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ አስታወቀ
*********************

የአዲስ አበባ ከተማ ንግድ ቢሮ ወቅታዊ ሀገራችንን ሁኔታ መሰረት በማድረግ የተዋቀረው የንግድ ቁጥጥር ግብረ ኃይል እንቅስቃሴ አፈፃፀም በዛሬው ዕለት የገመገመ ሲሆን በየክፍለከተማው የተገኙ በምርት አቅርቦት፣ስርጭት፣ተደራሽነት እና የተወሰዱ እርምጃዎች ላይ በጥልቀት ውይይት አካሂደዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ንግድ ቢሮ ሓላፊ አቶ አብዱልፈታ የሱፍ፣ እስካሁን በተደረገው ቁጥጥር ስራም ከ48 ሺህ በላይ የንግድ ተቀማት ላይ የበር ለበር ምልከታ የተደረገ ሲሆን፣ ያለ ንግድ ፈቃድ በመነገድ፣ ምክንያታዊ ያልሆነ የዋጋ ጭማሪ በማድረግ፣ ማከማቸት እና መደበቅ፣ የምርት ጥራት ማጓደል እና በተለያዩ የንግድ ህግ ጥሰቶች በ1ሺህ 973 የንግድ ተቋማት ላይ አስፈላጊውን እርምጃ መወሰዱን ገልጸዋል፡፡

በተጨማሪም ምርቶችን ያለአግባብ በማከማቸት እና ያለፈቃድ የመጋዘን አገልግሎት ላይ በመሰማራት በ113 መጋዘኖች ላይ ተገቢው እርምጃ እንደተወሰደባቸው አቶ አብዱልፈታ ተናግረዋል፡፡

እስካሁን የተከናወኑት የቁጥጥር ተግባራት አበረታች መሆናቸውን፣ የተጀመረው ክትትል እና ቁጥጥር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ማስታወቃቸውን ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬታሪ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

@newsetv
11.6K views16:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-11-19 19:23:22 በመተከል ዞን በንጹሐን ዜጎች ላይ ጥቃት የሚፈጽሙ ሽፍታ ቡድኖችን ለማጥፋት በቅንጅት እየተሰራ ነው፦የቤንሻንጉል ጉሙዝ ርእሰ መስተዳደር አቶ አሻድሊ

በመተከል ዞን በንጹሐን ዜጎች ላይ ጥቃት የሚፈጽሙ ሽፍታ ቡድኖችን እስከወዲያኛው ለማጥፋት በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን የቤንሻንጉል ጉሙዝ ርእሰ መስተዳደር አቶ አሻድሊ ሀሰን ገለፁ፡፡

በዚህም በክልሉ መተከል ዞን በተደጋጋሚ በንፁሐን ዜጎች ላይ ጥቃት በሚፈጽሙ ፀረ-ሰላም ኃይሎች ላይ ከአጎራባች ክልል ዝና ከፌዴራል መንግስት ጋር በመሆን እርምጃ በመውሰድ ለህግ እንዲቀርቡ እየተደረገ እንደሆነ አቶ አሻድሊ ከኢቲቪ ጋር በነበራቸው ቆይታ ተናግረዋል፡፡

በዞኑ በተጣለው ኮማንድ ፖስት ከ100 በላይ ፀረ-ሰላም ኃይሎች ሲደመሰሱ በየደረጃው ባሉ መዋቅር የሚሰሩ አመራሮችን ጨምሮ በርካታ ሰዎች በህግ ቁጥጥር ስር እንዲውሉ መደረጉን ገልፀዋል ርዕሰ መስተዳድሩ፡፡

በአካባቢው ከፌዴራል መንግስት እና ከአጎራባች ክልል ጋር በመሆን ህግ የማስከበር እርምጃ እየተወሰደ ቢሆንም ከጉዳዩ ውስብስብነት አንፃር ችግሩን ሙሉ ለሙሉ መቅረፍ አለመቻሉን ተናግረዋል፡፡

ይህም የሆነው በክልሉ የሚንቀሳቀሱ ፀረ-ሰላም ኃይሎች በጣም ትልቅ አቅም ያላቸው ሆነው ሳይሆን አድፍጠው ጥቃት የሚፈጽሙ የሽፍታ ባህሪ ያላቸው በመሆኑ በህግ ቁጥጥር ስር ለማዋል አዳጋች ስለሆነ ነው ብለዋል፡፡

በቅርቡም ፀረ-ሰላም ኃይሎቹ በክልሉ በአውቶቡስ በሚጓዙ ሰላማዊ ዜጎች ላይ ዘግናኝ የሆነ ጭፍጨፋ ያደረጉ ሲሆን፣ በተለያዩ ቀበሌዎች በሚኖሩ ወገኖች ላይም ማንነትን መሰረት ያደረገ ጥቃት እንደፈፀሙ ተናግረዋል፡፡

እነዚህ ሽፍታ ኃይሎች ከጁንታው ህወሃት ጨምሮ በሌሎች ቦታዎች ከሚንቀሳቀሱ ፀረ-ሰላም ቡድኖች ጋር ግንኙነት ያላቸው እንደሆኑም ጠቁመዋል፡፡

ፀረ-ሰላም ኃይሎቹንም እስከመጨረሻው ለማጥፋት እና ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት በቅርቡ እቅድ ተዘጋጅቶ እየተሰራ እንደሆነም አመልክተዋል፡፡

@newsetv
10.3K views16:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-11-19 19:22:12 በትግራይ ክልል የተፈጸመ ከፍተኛ የሕግ ጥሰት የኢፌዴሪ መንግሥት ወደ አስገዳጅ ሕግ ማስከበር ተግባር እንዲገባ አድርጎታል-የኖርዌይ ምሁራን ለኖቤል ኮሚቴ በጻፉት ደብዳቤ


በኖርዌይ የሚኖሩ 28 ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮ-ኖርዌጂያን ምሁራን እና ባለሞያዎች ለኖቤል ኮሚቴ በጻፉት ደብዳቤ፣ የኢፌዴሪ መንግሥት በትግራይ ክልል የተፈጸመው ከፍተኛ የሕግ ጥሰት ወደ አስገዳጅ መጠነ ሰፊ ሕግ የማስከበር ተግባር እንዲገባ ማድረጉን አስታወቁ።

ምሁራኑ እና ባለሞያዎቹ ቀደም ሲል ሐምሌ ወር 2012 ዓ.ም ላይ በጠባብ ብሔርተኛ ቡድኖች እና ግለሰቦች አነሳሣሽነት ኢትዮጵያ ውስጥ እየታዩ ያሉ ፖለቲካዊ እና ሰብአዊ ቀውሶች አሳስቧቸው ለኮሚቴው ደብዳቤ መጻፋቸውን አስታውቀዋል።

የኢፌዴሪ መንግሥት በቅርቡ በትግራይ ክልል የተፈጸመ ከፍተኛ የሕግ ጥሰት ወደ አስገዳጅ ሕግ የማስከበር ተግባር እንዲገባ ማስገደዱንም ጠቅሰዋል።

ይሁን እንጂ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ እና የኖቤል ኮሚቴ በትግራይ ክልል እየተከናወነ ስላለው የሕግ ማስከበር ተግባር ሆነ ተብሎ የተሳሳተ ግንዛቤ እና የተዛባ መረጃ እንዲደርሳቸው እየተደረገ እንደሆነ እንደሚያምኑ ገልጸዋል።

የዓለም የሰላም ኖቤል ያሸነፉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በዚህ መሰል የሕግ ማስከበር እርምጃ ላይ መሰለፍ እንደሌለባቸው የሚገልጹ የተዛቡ ዘገባዎች ማየታቸውን ጠቅሰዋል።

ይህ በራሱ ፍጹም ስሕተት ነው ያሉት ምሁራኑ እና ባለሞያዎቹ፣ በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ ውስጥ ስላለው የፍትሕ ሁኔታ አያሳይም ሲሉ አመልክተዋል።

በመሆኑም በኢትዮጵያ መንግሥት እና በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ላይ እየተሰራጩ ያሉት የተሳሳቱ መረጃዎች እና የስም ማጥፋቶች አሳስቧቸው ደብዳቤ ለመጻፍ እንዳነሣሣቸው ገልጸዋል።

በኢትዮጵያ ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ እንደሚከታተል ትውልደ ኢትዮጵያዊ ምሁርነታችን፣ ለኖቤል ኮሚቴ ትክክለኛውን ገጽታ እና በአገሪቱ ያለውን እውነታ ማሳወቅ እንፈልጋለን ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ መጋቢት 2010 ዓ.ም ላይ ወደ ሥልጣን ከመጡ ጀምሮ ያደረጓቸውን ለውጦች ለ30 ዓመታት ገደማ የትግራይ ክልልን እየመሩ ያሉት የሕወሓት አመራሮች ለመቀበል ፈቃደኛ አለመሆናቸውን አመልክተዋል።

ይህም ከለውጡ በፊት የነበረው ሕወሓት መሩ ግንባር ኢትዮጵያ ውስጥ የተገነባው ግለሰብን በማግነን እና በራስ ፍላጎቶች ላይ እንደነበር ግልጽ ነው ብለዋል።

አብዛኞቹ አክራሪ ሕወሓቶች ዓለም “እኛ ሥልጣን ላይ ከሌለን ኢትዮጵያ አትኖርም” የሚለውን እንዲያምንላቸው የሚፈልጉ ናቸው ሲሉ ጠቅሰዋል።

የአገሪቱን ሥልጣን ለቅቀው ወደ ክልላቸው ተጠቃልለው ከገቡ በኋላ በድብቅ ሲያከናውኗቸው የነበሩ ተግባራት በተከታታይ የፌዴራል መንግሥቱን በመገዳደር ይህንን ትርክታቸውን እውን እንዲመስል ማድረግ ነበር ብለዋል።

በርካታ ምሁራን፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች እና ግለሰብ ዜጎች በሥልጣን ላይ ያለው መንግሥት በተልይም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የመንግሥት ተቀዳሚ ተግባር የሆነውን ሕግ እና ሥርዓት ማስከበር እርምጃ እንዲወስዱ ሲወተውቱ መቆታቸውን ጠቅሰዋል።

በዚህም ሕወሓት እና በርሱ የሚደገፉ ወንበዴ ቡድኖች ሲፈጥሩት በነበረ ዘር ተኮር ብጥብጥ እና ግጭቶች የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ መንግሥት የትችት ናዳ ሲወርድበት መቆየቱን ገልጸዋል።

በእነዚህም ዘር ተኮር ግጭቶች እና ብጥብጦች በሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ለሞት፣ ሚሊየኖችን ለመፈናቀል፣ ለሀብት ንብረት ውድመት እንዲሁም አገሪቱን መጠነ ሰፊ አለመረጋጋት ውስጥ ከትቷል እንደነበር አስታውሰዋል።

የአሁኑ ግጭት መንስኤም የሕወሓትኃይሎች በሰሜን የአገሪቱ ክፍል በሚገኘው የኢፌዴሪ መከላከያ ኃይል ላይ ጭካኔ የተሞላበት ጥቃት በመፈጸሙ የተከሰተ መሆኑን አብራርተዋል።

ይህንንም ተግባር በይፋ መፈጸማቸውን የሕወሓት ከፍተኛ ባለሥልጣን የሆነው ሴኮ ቴሬ ጌታቸው በክልሉ ቴሌቪዥን ባደረጉት ውይይት ማረጋገጣቸውን ጠቅሰዋል።

ይህም ሕወሓት የኢፌዴሪ መንግሥት ወደ ሕግ ማስከበር ተግባር ተገድዶ እንዲገባ እንደገፋው ጠቅሰዋል፡፡

@newsetv
9.3K views16:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-11-17 19:26:47 የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት በትግራይ በምሥራቅና በምዕራብ ግንባሮች ወሳኝ ድሎችን ተቀዳጅቷል።

በምሥራቁ ግንባር ራያ ሙሉ በሙሉ ነጻ ወጥቷል፤ ጨርጨር፣ ጉጉፍቶ መሖኒን ሠራዊቱ ነጻ አውጥቷል። በየቦታው የነበሩ ወሳኝ የኮንክሪት ምሽጐችንም አፍርሷል። ሠራዊቱ በአሁኑ ጊዜ ወደ መቀሌ በመገሥገሥ ላይ ነው።

በምዕራብ ግንባር ደግሞ በአዲ ነብሪድና በአዲ ዳእሮ የሚገኙ ከባድ ምሽጎችን በማፍረስ ሽሬን ተቆጣጥሮ ወደ አኩስም በመገሥገሥ ላይ ይገኛል።

በውጊያው እጅግ ብዙ መሣሪያዎች ከመማረካቸውም በላይ ህወሓት ለክፉ ዓላማው ያሰለፋቸው የትግራይ ልዩ ኃይል አባላት በቁጥጥር ሥር ውለዋል።

የመከላከያ ሠራዊቱ የህወሓት ጁንታን በሕግ ቁጥጥር ሥር ለማዋል እየገሠገሠ ሲሆን የጁንታው ኃይል የመከላከያ ሠራዊቱን ክንድ መቋቋም አቅቶት ወደኋላ እየሸሸ መሆኑን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የመረጃ ማጣሪያ ያወጣው መረጃ ያመለክታል።

@newsetv
10.8K views16:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-11-17 08:22:31
“የተሰጠው የጊዜ ገደብ ስለተጠናቀቀ በቀጣይ ቀናት የመጨረሻው ሕግ የማስከበር ወሳኝ ተግባር ይከናወናል።”ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ
*************
የትግራይ ልዩ ኃይልና ሚሊሺያ የስግብግቡ ጁንታ እኩይ ዓላማ ማስፈጸሚያ ከመሆን ይልቅ እጁን ለመከላከያ በመስጠት ራሱንና ሕዝቡን እንዲያድን የተሰጠው የ3 ቀን የጊዜ ገደብ ዛሬ መጠናቀቁን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገልፀዋል።

በዚህ ጥሪ የተጠቀሙ የትግራይ ልዩ ኃይልና ሚሊሺያ አባላት፣ ለወሰዱት ኃላፊነት የተሞላው ሕዝባቸውን የማዳን ውሳኔ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አመስግነዋል።

አሁን ግን የተሰጠው የጊዜ ገደብ ስለተጠናቀቀ በቀጣይ ቀናት የመጨረሻው ሕግ የማስከበር ወሳኝ ተግባር እንደሚከናወን ነው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የገለፁት።

@newsetv
11.0K views05:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-11-16 16:30:06 ሞዴርና የተባለው ኩባንያ የሞከረው የኮሮና ቫይረስ ክትባት 94 ነጥብ 5 በመቶ ፈዋሽ መሆኑን አስታወቀ፡፡

ሞዴርና ይፋ ያደረገው ይህ ክትባት በአሜሪካ ሁለተኛውና ትልቅ ግኝት ተብሎለታል፡፡

የአሜሪካ የተላላፊ በሽታዎች ተቋም ኃላፊ አንቶኒዮ ፉቺ ግኝቱን አስመለክተው ይህ ትልቅ ዜና ነው ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

ሞዴርና ክትባቱን በስራ ላይ እንዲውል በቀጣዩ ሳምንት እንደሚያመለክትም ነው የገለጸው፡፡

በሙከራው ወቅት 30 ሺህ አሜሪካውያን መሳተፋቸውን ነው የተነገረው፡፡

በተጨማሪም በመጪዎቹ ሳምንታት 2 ሚሊየን መጠን ያለው ክትባት እንደሚያመርት ገልጾ በቀጣዩ የፈረንጆች ዓመት ደግሞ 1 ቢሊየን መጠን ያለው ክትባት በዓለም ዙሪያ ለማሰራጨት ዕቅድ መያዙን ይፋ አድርጓል፡፡

ከሳምንት በፊት የአሜሪካው ፋይዘር እና የጀርመኑ ባዮንቴክ ፈዋሽነቱ 90 በመቶ የተረጋገጠ የኮሮና ቫይረስ ክትባት ይፋ ማድረጋቸው የሚታወስ ነው፡፡

የሁለቱ ኩባንያዎች ክትባት የተለዩ ማቀዝቀዣዎችን ይፈልጋል የተባለ ሲሆን የሞዴርና በአንጻሩ በኔጌቲቭ 20 ዲግሪ ሴሊሺየስ ውስጥ ለስድስት ወራት እንዲሁም በመደበኛ ማቀዝቀዣ ውስጥ ደግሞ ለአንድ ወር ይቆያል ተብሏል፡፡

ከነዚህ ከሁለቱ ክትባቶች በተጨማሪ ባለፈው ሳምንት አጋማሽ ሩስያ 92 በመቶ ፈዋሽነቱ የተረጋገጠ ክትባት ይፋ አድርጋለች፡፡

ምንጭ፡-ቢቢሲ
@newsetv
9.9K views13:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-11-16 15:39:23
የሀገር መከላከያ ሰራዊት 'ህወሓት' ከሰሜን እዝ ወስዷቸው የነበሩትን አብዛኞቹን 'ታንኮቹን' እንዳስመለሰ ዛሬ አሳውቋል።

አንዳንዶቹ ታንኮች ደግሞ እንዲወድሙ መደረጉን ሰራዊቱ ገልጿል።

ፎቶውን ኢቢሲ ከስፍራው እንዳገኛቸው ገልጾ አሰራጭቷል።

@newsetv
9.0K views12:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-11-16 11:44:00 ለመከላከያ ሠራዊት የሕክምና ድጋፍ ለመስጠት ወደ ጦር ግንባር ለሚያመሩ የሕክምና ባለሙያዎች አሸኛኘት ተደረገ


ለኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት የሕክምና ድጋፍ ለመስጠት ወደ ጦር ግንባር ለሚያመሩ የሕክምና ባለሙያዎች በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አሸኛኘት ተደርጓል።

በአሸኛኘቱ ላይ የከተማዋ ምክትል ከንቲባ አዳነች አበቤ፣ የከተማዋ ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ዮሐንስ ጫላን ጨምሮ በርካታ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ ሐኪሞቹ ለመከላከያ ኃይላችን ሙያዊ ድጋፍ ለማድረግ በመወሰናቸው አመስግነው፣ ለሕክምና ባለሙያዎችም ሆነ ለመከላከያ ሠራዊቱ አስፈላጊው ድጋፍ ሁሉ እንደሚደረግላቸው ገልጸዋል።

የጤና ባለሙያዎቹ ወደ 1.7 ሚሊዮን ብር የሚገመት የሕክምና ግብዓት ከአዲስ አበባ አስተዳደር ተረክበዋል።

የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ዮሐንስ ጫላ በዚህ ወቅት "የጤና ባለሙያች የመከላከያ ሠራዊቱን ለማገልገል ዕድል በማግኘታቹ እንኳን ደስ አላችሁ" ብለዋል።

የሕክምና ድጋፍ ለመስጠት የሚሄዱት ባለሙያዎች 10 ስፔሳሊስት ዶክተሮች፤ 24 ነርሶች፤ አንድ ማደንዘዣ የሚሰጥ ስፔሻሊስት ዶክተርን ጨምሮ 48 የሕክምና ባለሙያዎች በሁለት ቡድን ተከፍለው እንደሚጓዙ ተገልጿል።

በዋለልኝ ተዓምር

@newsetv
8.9K views08:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ