Get Mystery Box with random crypto!

ለመከላከያ ሠራዊት የሕክምና ድጋፍ ለመስጠት ወደ ጦር ግንባር ለሚያመሩ የሕክምና ባለሙያዎች አሸኛኘ | Brand watches and bags shop 2

ለመከላከያ ሠራዊት የሕክምና ድጋፍ ለመስጠት ወደ ጦር ግንባር ለሚያመሩ የሕክምና ባለሙያዎች አሸኛኘት ተደረገ


ለኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት የሕክምና ድጋፍ ለመስጠት ወደ ጦር ግንባር ለሚያመሩ የሕክምና ባለሙያዎች በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አሸኛኘት ተደርጓል።

በአሸኛኘቱ ላይ የከተማዋ ምክትል ከንቲባ አዳነች አበቤ፣ የከተማዋ ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ዮሐንስ ጫላን ጨምሮ በርካታ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ ሐኪሞቹ ለመከላከያ ኃይላችን ሙያዊ ድጋፍ ለማድረግ በመወሰናቸው አመስግነው፣ ለሕክምና ባለሙያዎችም ሆነ ለመከላከያ ሠራዊቱ አስፈላጊው ድጋፍ ሁሉ እንደሚደረግላቸው ገልጸዋል።

የጤና ባለሙያዎቹ ወደ 1.7 ሚሊዮን ብር የሚገመት የሕክምና ግብዓት ከአዲስ አበባ አስተዳደር ተረክበዋል።

የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ዮሐንስ ጫላ በዚህ ወቅት "የጤና ባለሙያች የመከላከያ ሠራዊቱን ለማገልገል ዕድል በማግኘታቹ እንኳን ደስ አላችሁ" ብለዋል።

የሕክምና ድጋፍ ለመስጠት የሚሄዱት ባለሙያዎች 10 ስፔሳሊስት ዶክተሮች፤ 24 ነርሶች፤ አንድ ማደንዘዣ የሚሰጥ ስፔሻሊስት ዶክተርን ጨምሮ 48 የሕክምና ባለሙያዎች በሁለት ቡድን ተከፍለው እንደሚጓዙ ተገልጿል።

በዋለልኝ ተዓምር

@newsetv