Get Mystery Box with random crypto!

የመከላከያ ሰራዊት አላማጣንና አከባቢውን ከጁንታው የህወሓት ቡድን ነፃ አወጣ የመከላከያ ሰራዊት | Brand watches and bags shop 2

የመከላከያ ሰራዊት አላማጣንና አከባቢውን ከጁንታው የህወሓት ቡድን ነፃ አወጣ

የመከላከያ ሰራዊት አላማጣንና አከባቢውን ከህወሓት ጁንታ ታጣቂዎች በማስለቀቅ ነፃ ማውጣቱን አስታወቀ።

በመከላከያ ሰራዊት የደቡብ እዝ የሰው ሀብትና ሚዲያ አስተባባሪ ኮሎኔል ደጀኔ ፀጋዬ እንዳሉት፥ ህግ የማስከበር ዘመቻው በታቀደው ልክ እየተካሄደ ነው።

በዚህም በራያ ቆቦና አከባቢው ህግን ለማስከበር የተሠማራው የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊ ዋጃ፣ ጥሙጋ፣ አላማጣና አከባቢውን ከጁንታው የህውሀት ቡድን ነፃ አውጥቶ ተቆጣጥሯል።

በተጨማሪም ሠራዊቱ የግራካሶ ተራራና አከባቢውን ለመቆጣጠር እየገሠገሠ እንደሚገኝና በምስራቅ አላማጣ ፣ በጨርጨር አከባቢ የተሠማራው ሠራዊትም ድል እያስመዘገበ እንደሚገኝ ኮሎኔል ደጀኔ ፀጋዬ ገልፀዋል።

እንዲሁም ፅንፈኛው ቡድንን በዜጎች ላይ ጉዳት ሳያደርስ ለመቆጣጠር ሠራዊታችን በከፍተኛ ጥንቃቄ እየተራመደ እንደሚገኝ አብራርተዋል።

እንዲሁም ፅንፈኛው ቡድንን በዜጎች ላይ ጉዳት ሳያደርስ ለመቆጣጠር ሠራዊታችን በከፍተኛ ጥንቃቄ እየተራመደ እንደሚገኝ አብራርተዋል።

ነዋሪዎችም ፅንፈኛውና ዘራፊው ቡድን አካባቢውን ጥሎ በመሸሹ ደስታቸውን በተለያየ መንገድ በመግለፅ ላይ እንደሚገኙ ከኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

@newsetv