Get Mystery Box with random crypto!

በመተከል ዞን በንጹሐን ዜጎች ላይ ጥቃት የሚፈጽሙ ሽፍታ ቡድኖችን ለማጥፋት በቅንጅት እየተሰራ ነው | Brand watches and bags shop 2

በመተከል ዞን በንጹሐን ዜጎች ላይ ጥቃት የሚፈጽሙ ሽፍታ ቡድኖችን ለማጥፋት በቅንጅት እየተሰራ ነው፦የቤንሻንጉል ጉሙዝ ርእሰ መስተዳደር አቶ አሻድሊ

በመተከል ዞን በንጹሐን ዜጎች ላይ ጥቃት የሚፈጽሙ ሽፍታ ቡድኖችን እስከወዲያኛው ለማጥፋት በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን የቤንሻንጉል ጉሙዝ ርእሰ መስተዳደር አቶ አሻድሊ ሀሰን ገለፁ፡፡

በዚህም በክልሉ መተከል ዞን በተደጋጋሚ በንፁሐን ዜጎች ላይ ጥቃት በሚፈጽሙ ፀረ-ሰላም ኃይሎች ላይ ከአጎራባች ክልል ዝና ከፌዴራል መንግስት ጋር በመሆን እርምጃ በመውሰድ ለህግ እንዲቀርቡ እየተደረገ እንደሆነ አቶ አሻድሊ ከኢቲቪ ጋር በነበራቸው ቆይታ ተናግረዋል፡፡

በዞኑ በተጣለው ኮማንድ ፖስት ከ100 በላይ ፀረ-ሰላም ኃይሎች ሲደመሰሱ በየደረጃው ባሉ መዋቅር የሚሰሩ አመራሮችን ጨምሮ በርካታ ሰዎች በህግ ቁጥጥር ስር እንዲውሉ መደረጉን ገልፀዋል ርዕሰ መስተዳድሩ፡፡

በአካባቢው ከፌዴራል መንግስት እና ከአጎራባች ክልል ጋር በመሆን ህግ የማስከበር እርምጃ እየተወሰደ ቢሆንም ከጉዳዩ ውስብስብነት አንፃር ችግሩን ሙሉ ለሙሉ መቅረፍ አለመቻሉን ተናግረዋል፡፡

ይህም የሆነው በክልሉ የሚንቀሳቀሱ ፀረ-ሰላም ኃይሎች በጣም ትልቅ አቅም ያላቸው ሆነው ሳይሆን አድፍጠው ጥቃት የሚፈጽሙ የሽፍታ ባህሪ ያላቸው በመሆኑ በህግ ቁጥጥር ስር ለማዋል አዳጋች ስለሆነ ነው ብለዋል፡፡

በቅርቡም ፀረ-ሰላም ኃይሎቹ በክልሉ በአውቶቡስ በሚጓዙ ሰላማዊ ዜጎች ላይ ዘግናኝ የሆነ ጭፍጨፋ ያደረጉ ሲሆን፣ በተለያዩ ቀበሌዎች በሚኖሩ ወገኖች ላይም ማንነትን መሰረት ያደረገ ጥቃት እንደፈፀሙ ተናግረዋል፡፡

እነዚህ ሽፍታ ኃይሎች ከጁንታው ህወሃት ጨምሮ በሌሎች ቦታዎች ከሚንቀሳቀሱ ፀረ-ሰላም ቡድኖች ጋር ግንኙነት ያላቸው እንደሆኑም ጠቁመዋል፡፡

ፀረ-ሰላም ኃይሎቹንም እስከመጨረሻው ለማጥፋት እና ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት በቅርቡ እቅድ ተዘጋጅቶ እየተሰራ እንደሆነም አመልክተዋል፡፡

@newsetv