Get Mystery Box with random crypto!

የተለያዩ የንግድ ህግ ጥሰቶችን በፈጸሙ 1ሺህ 973 የንግድ ተቋማት ላይ እርምጃ መውሰዱን የአዲስ | Brand watches and bags shop 2

የተለያዩ የንግድ ህግ ጥሰቶችን በፈጸሙ 1ሺህ 973 የንግድ ተቋማት ላይ እርምጃ መውሰዱን የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ አስታወቀ
*********************

የአዲስ አበባ ከተማ ንግድ ቢሮ ወቅታዊ ሀገራችንን ሁኔታ መሰረት በማድረግ የተዋቀረው የንግድ ቁጥጥር ግብረ ኃይል እንቅስቃሴ አፈፃፀም በዛሬው ዕለት የገመገመ ሲሆን በየክፍለከተማው የተገኙ በምርት አቅርቦት፣ስርጭት፣ተደራሽነት እና የተወሰዱ እርምጃዎች ላይ በጥልቀት ውይይት አካሂደዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ንግድ ቢሮ ሓላፊ አቶ አብዱልፈታ የሱፍ፣ እስካሁን በተደረገው ቁጥጥር ስራም ከ48 ሺህ በላይ የንግድ ተቀማት ላይ የበር ለበር ምልከታ የተደረገ ሲሆን፣ ያለ ንግድ ፈቃድ በመነገድ፣ ምክንያታዊ ያልሆነ የዋጋ ጭማሪ በማድረግ፣ ማከማቸት እና መደበቅ፣ የምርት ጥራት ማጓደል እና በተለያዩ የንግድ ህግ ጥሰቶች በ1ሺህ 973 የንግድ ተቋማት ላይ አስፈላጊውን እርምጃ መወሰዱን ገልጸዋል፡፡

በተጨማሪም ምርቶችን ያለአግባብ በማከማቸት እና ያለፈቃድ የመጋዘን አገልግሎት ላይ በመሰማራት በ113 መጋዘኖች ላይ ተገቢው እርምጃ እንደተወሰደባቸው አቶ አብዱልፈታ ተናግረዋል፡፡

እስካሁን የተከናወኑት የቁጥጥር ተግባራት አበረታች መሆናቸውን፣ የተጀመረው ክትትል እና ቁጥጥር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ማስታወቃቸውን ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬታሪ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

@newsetv