Get Mystery Box with random crypto!

የትግራይ ህዝብ የህወሃትን የጥፋት ቡድን እንደማይደግፍ በተግባር እያሳየ ነው...ብርጋዴር ጀኔራል | Brand watches and bags shop 2

የትግራይ ህዝብ የህወሃትን የጥፋት ቡድን እንደማይደግፍ በተግባር እያሳየ ነው...ብርጋዴር ጀኔራል ብርሄ ገብረመድህን

የትግራይ ህዝብ የህወሃትን የጥፋት ቡድን አለመደገፉን በተጨባጭ እያሰየ መሆኑን በአገር መከላከያ የሎጂስትክስ ዋና መምሪያ የሜንቴናንስ ሃላፊ ብርጋዴር ጀኔራል ብርሄ ገብረመድህን ተናገሩ።

የህወሃት ጽንፈኛ ቡድን በኢትዮጵያ የእርስ በርስ ግጭት ለመፍጠር አልሞ የነበረው የጥፋት መረብ እንደከሸፈበትም ነው የገለጹት።

ብርጋዴር ጄኔራል በርሄገብረመድህን ከአዜአ ጋር በነበራቸው ቆይታ እንዳሉት፤ የአገር መከላከያ ሰራዊት ለህዝብና ለአገር ደህንነት ሲል ራሱን አሳልፎ የሚሰጥ ሃይል መሆኑ ይታወቃል።

የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ከአገሩም አልፎ የአፍሪካ የሰላም ዋስትና ለመሆኑ ብዙዎች ምስክርነታቸውን እንደሚሰጡም ገልጸዋል።

የህወሃት ቡድን ጥቃት የፈፀመበት የሰሜን እዝ በተለይ የትግራይን ህዝብ ሰላም በመጠበቅና በተለያዩ ማህበራዊ አገልግሎቶች በመሳተፍ የህዝብ አለኝታነቱን ሲያሳይ ቆይቷል ብለዋል።

የኮሮናቫይረስ መከሰትን ተከትሎ ሰራዊቱ በክልሉ አቅመ ደካሞችን በመደገፍ፣ አዝመራ በመሰብሰብ፣ አንበጣ በመከላከልና ህፃናት እንዲማሩ በመደገፍ አለኝታነቱን ማሳየቱን ብርጋዴር ጄኔራል በርሄ ገልጸዋል።

የሰራዊቱ አባላት ከትግራይ ህዝብ ጋር በፈጠሩት ጠንካራ ቤተሰባዊ ትስስር ሳቢያ በጡረታ ሲገለሉ እንኳን ቤተሰባዊ ኑሯቸውን በክልሉ የሚያደርጉ በርካቶች እንደሆኑ ተናግረዋል።
የህወሃት ፅንፈኛ ሃይል ግን ይህንን ሁሉ የሰራዊቱን ውለታ በአንድ ምሽት "የክህደት ቋት ውስጥ ከቶታል" ብለዋል።

የጽንፈኛ ቡድኑ መሪዎች ልጆቻቸውን በተለያዩ አገራት አስቀምጠው የደሃውን የትግራይ ህዝብ ልጅ ለስቃይ እየዳረጉት መሆኑንም ነው የገለጹት።

በትግራይ ህዝብ ስም በመነገድ ለራሳቸው ጥቅም ብቻ ሲሰሩ መቆየታቸውን የገለጹት ብርጋዴር ጀኔራሉ፤የትግራይ ህዝብ ልማት እንጂ ጦርነት አይሻም ብለዋል።

የክልሉ ህዝብ ጽንፈኛ ቡድኑ መከላከያን እንዲወጉ ያስታጠቃቸውን መሳሪያ ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ማስረከባቸውም የቡድኑን እኩይ ተግባር እንደማይደግፉ ማሳያ ነው ብለዋል።

የትግራይ ህዝብ ጽንፈኛ ቡድኑን በመጋፈጥ ለአገር መከላከያ ሰራዊት ድጋፍ በማድረጉ የህግ ማስከበር እርምጃው በአጭር ጊዜ ውስጥ በርካታ ድሎች እየተመዘገቡበት መሆኑን ገልጸዋል።

ጽንፈኛ ቡድኑ ሰራዊቱን በማጥቃት የእርስ በርስ ግጭት ለመፍጠር እቅድ እንደነበረው ጠቅሰው፤ ኢትዮጵያውያን ለሀገር ሉዓላዊነት ያላቸው አቋም አንድ በመሆኑ ህልሙ ሳይሳካለት ቀርቷል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

እየተካሄደ ባለው ህግ የማስከበር እርምጃ ጽንፈኛው ቡድን በቅርቡ ለህግ እንደሚቀርብ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።

@newsetv